Pages

Saturday, March 1, 2014

ቴክኖሎጂ ያዘመነው የእኛ ትውልድና ፤ ሚዲያ መራሹ ማሕበራዊ ምስቅልቅል Part 1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡


ቴክኖሎጂ ያዘመነው የእኛ ትውልድና ፤ ሚዲያ መራሹ ማሕበራዊ ምስቅልቅል



Nowadays it is considered a self-evident and undoubted fact that we are living at a unique time in history where mankind is enjoying supreme technological progress and man-made heaven on earth is soon to be within our reach.

But many people deviate from this popular perception. They claim that we are in the middle of social and cultural turmoil which will inevitably bring civilization into utter destruction and total collapse.
These informed critics point towards:

F Increasing display of nerve wrecking violence and despicable sexual imagery on medias and its subsequent impact in producing a generation preoccupied with sexual lust and rebelliousness;
F The rejection of traditional religious and moral values and the increasing acceptance of abominable vices such as homosexuality, pedophilia, trans-sexuality, and sado-masochism;
F The spread of Satanism, witchcraft and an obsession with what is evil and unrighteous; and
F The subsequent growth of audio-visual products that blaspheme God and make a mockery of Christianity thereby making obscenity and blasphemy a cultural and behavioral norm…

as evidence that illuminates the severity of the problem.
The social and historical critics go further and claim that the current chaos and social upheaval is not spontaneous but the result of meticulous planning and malicious conspiracy.

Could secret societies behind the scenes have possibly orchestrated the most outrageous deception that fooled most of us into becoming willing participants of our own destruction?

Stay with us as we examine in detail
F all the available information,
F explore the evidence,
F analyze official documents
F and inspect credible sources.
 You be the judge as we ask you to maintain an unbiased attitude until you have all the available evidence.



ከ20ኛው መ.ክ.ዘ መገባደጃ አንስቶ ባሉት ጥቂት አስርት አመታት የአለምን ምስል ፈጽመው የለወጡ ሁለት አስደናቂና ቅጽበታዊ የሆኑ ለውጦች በተመሳሳይ ጊዜ ተከስተዋል ፤ አንደኛው ለውጥ ለማመን በሚያዳግት ሁኔታ የሰው ልጅ ያስመዘገበው የቴክኖሎጂ ምጥቀት ሲሆን ፤ ሌላኛው ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ በስነ ምግባር፣ በሃይማኖትና በሰብአዊ እሴቶች ዙሪያ እየተስተዋለ የመጣው ሁለንተናዊ ዝቅጠት ነው፡፡ እነዚህ ሁለት እርስበርስ ተመጋጋቢ ነገር ግን ፍጹም ተጻራሪ የሆኑ ክስተቶች ያለንበት ትውልድ መገለጫዎች ለመሆን በቅተዋልም ማለት ይቻላል፡፡

ተንጠልጣይ ድልድዮች፣ ከድምጽ የፈጠኑ አውሮፕላኖች፣ ተንሳፋፊና ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች፣ የጠፈር መንኮራኩሮች፣ የሕዋ ሳታላይቶች፣ ሰው አልባና ከራዳር እይታ የተሰወሩ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ እጅግ የረቀቁ የሕክምና የቴክኖሎጂ ውጤቶች … በርግጥም ከአእምሮ በላይ የሆኑ አስደማሚ ግኝቶች ናቸው፡፡

የሰው ልጅ ለደረሰበት የጥበብ ከፍታ ቋሚ ምስክሮች የሆኑት እነዚህ የቴክኖሎጅ መራቀቆች ታዲያ በርካቶችን በሰው ልጅ ጥበብ ወደ መመካት ሲያደርሷቸው ፤ አንዳንዶችንም ጥልቅ ወደ ሆነ የአግራሞትና የመደመም ስሜት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም የሰው ልጅ  ቁሳዊ ፍላጎቶቹን እንዳያሟላ ለዘመናት የተፈጥሯዊ ተግዳሮቶች ምርኮኛ ሆኖ መኖሩን በማስታወስ ባለንበት ክፍለ ዘመን አእምሮውን ተጠቅሞ ባስገኛቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመታገዝ ከእነዚህ ማነቆዎች ራሱን ነጻ አውጥቶ የምቾት ኑሮ ለማጣጣም መብቃቱን የሚያወሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ እንደነዚህ ወገኖች እምነት የሰው ልጅ በትክክለኛው የእድገትና የብልጽግና ጎዳና ላይ ለመገኘቱ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ አያስፈልግም፡፡ ይህንን በነሱ አተያይ የማያሻማ፣ አገር ያወቀውና ፀሐይ የሞቀው የፈጠጠ ሐቅ ተአማኒነት መጠርጠርም ከጤናማና ከተማረ ሰው እንደማይጠበቅ በልበ ሙሉነት ያሰምሩበታል፡፡

ያም ሆኖ ከእነዚህ ወገኖች አመለካከት በተቃራኒ የቆሙና ቁሳዊ ፍላጎቶችን ከማሳካት አንጻር ‹ዘመናዊው› አለም በቴክኖሎጂ በኩል ያስመዘገባቸው ስኬቶች ተደርሶበታል ለሚባለው ከፍተኛ ስልጣኔና ብልጽግና መገለጫ ነው ብለው ለመቀበል የሚያንገራግሩ አካላት ቁጥርም ጥቂት የሚባል አይደለም፡፡ እኒህ ወገኖች ትውልዱ ቁሳዊ ፍላጎቶቹን ከማሟላት አንጻር እጅግ ርቆ መጓዙን ባይክዱም ቁሳዊ መሻሻል የእድገትና የስልጣኔ መስፈርት ነው የሚለው አስተሳሰብ ግን አይዋጥላቸውም፡፡

ይህ ከተለመደው ወጣ ያለ እይታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋና እየዳበረ የሌሎች መስኮችንም በር በማንኳኳት ላይ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ያህል አፍሮ ሴንትሪክ ቲዮሪ በመባል የሚታወቀውን ፍልስፍና የሚያራምዱ ምሁራን የስነ ሕንጻ ጥበብን የሚመሰክሩ የአርኪዮሎጂ ግኝቶች በአመዛኙ የሌሏት አህጉራችን አፍሪካን በስልጣኔ ኋላ ቀር አድርጎ የሚፈርጃትን ቁሳዊ ብልጽግና ላይ ብቻ ያነጣጠረ ምእራባዊ መነጽር አውልቆ መጣል እንደሚያሻ ይገልጻሉ፡፡ እኒህ አፍሪካውያንና አፍሪካ አሜሪካውያን ምሁራን በትውፊት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር የበለጸገ ስነ ቃል፣ ባሕላዊ፣ ማሕበራዊና ግብረ ገባዊ እሴቶች ያሏቸው ማሕበረሰቦች የነበሯት አፍሪካ ባልካበቻቸው ግንቦችና ባልጠረበቻቸው ሐውልቶች፣ ባልገነባቻቸው ሕንጻዎች ልትሸማቀቅ፣ ራሷን እንደኋላቀር ቆጥራ በድንጋይ ላይ ድንጋይ ላነባበረችው አውሮፓ ልትሰግድ እንደማይገባ፤ ባንጻሩ በመጠቀው ማሕበራዊ እሴቷ ልትኮራና አፍሪካዊ የስልጣኔ እይታ ልታዳብር እንደሚገባ ይሞግታሉ፡፡ እዚህ ላይ ታዲያ ስለ አፍሮ ሴንትሪክ ቲዮሪም ሆነ ጽንሰ ሐሳቡን ስለሚያራምዱ ምሁራን መጥቀሳችን አስተሳሰቡን ደግፈን ለማስተጋባት ሳይሆን የአንድን ሕብረተሰብ መበልጸግ/መሰልጠን/ ለመገምገም የሚቀመጡት ቁሳዊ ስኬትን መሰረት ያደረጉት መስፈርቶች አንደምናስበው በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው እንዳልሆኑና ይልቁን የአንድ ጎራ እይታዎች ብቻ መሆናቸውን ለማስመር ነው፡፡

እነዚህ የዚህ ‹ዘመናዊ› ስርአት ሐያስያን የሆኑት ምሁራን ታዲያ የብልጽግና መገለጫ አድርገን እየተመለከትነው የመጣነውን ቁሳዊነትን በመንቀፍ ብቻ አይወሰኑም፡፡ ከዚህ አልፈው ከፊታችን ቴክኖሎጂ አንጥፎልናል በምንለው ወርቃማ የስኬት ጎዳና ላይ የጥፋት ጭለማና የውድቀት ጭጋግ እንዳጠላ ጭምር በጽኑ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን በራችንን በማንኳኳት ላይ ነው ስለሚሉት አይቀሬ ጥፋትና ማሕበራዊ መንኮታኮት (Social Cataclysm) የሚያሰሙት ይህ ስጋት ታላላቅ ከተሞችን ባጨናነቁ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ተከልሎ፣ እንደንፋስ በሚከንፉት መኪኖችና ባቡሮች ጩኸት ውስጥ ሰጥሞ፣ በሚዲያዎች አለማቋረጥ በሚስተጋቡ ዘመናዊ ሙዚቃዎችና የመዝናኛ ዝግጅቶች ተውጦ ሰሚ ጆሮ አጥቷል፡፡

በዘመኑ ትውልድ በተለይም በወጣቱ ማሕበረሰብ ላይ የሚስተዋለው ስርአት አልበኝነት፣ ግለኝነት፣ አመጻና ጠብ፣ ከፍተኛ የሱስ ተጠቂነት፣ የግብረሰዶም መስፋፋት፣ ለማሕበረሰባዊና ግለሰባዊ የስነ ምግባር እሴቶች ደንታ  የሌለው… ለገንዘብ ሕሊናውን የሸጠና… ለቀኑ ብቻ የሚኖር ሰው ቁጥር መበራከት፣ የውርጃ የፍቺ እንዲሁም የሴትና የወንድ አዳሪነት ቁጥር ማሻቀብ… ወዘተ እኒህ ወገኖች ላለንበት ዝቅጠት እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡዋቸው ጠቋሚ መለኪያዎች ናቸው፡፡ ሰዎች በአንዱ ጎን ቁሳዊ ፍላጎቶቻቸውን ሊያሟሉ በሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ቢከበቡም ፤ ነገር ግን በሌላው ጎን ሕሊናቸውን አጥተው እንስሳዊ ኑሮን ከተላመዱ እየተጓዙበት ያለውን መንገድ በርግጥ የስልጣኔ፣ የብልጽግናና የስኬት ነው ልንለው እንዴት እንችላለን? … ይጠይቃሉ የ‹ዓለም-ዘምናለች› አስተሳሰብ ተቃዋሚ የሆኑት እነዚህ ምሁራን፡፡

እነዚህ ከሚነጉደው ጋር አብረው ከመንጎድ ይልቅ እየገሰገስንበት ያለውን ጎዳና ቆም ብለው ለማጤን የሚደፍሩ ወገኖች ታድያ የአሁኑን ዘመን ትውልድ በታሪክ አድማስ-ማዶ ተሰናብተነው ከመጣነውና በአመዛኙ ‹ኋላቀር› የሚል ታርጋ ከለጠፍንበት ካለፈው ትውልድ ጋር በማነጻጸር እየተመለከትነው ያለነው ለውጥ የእድገት ይሁን የዝቅጠት እንድንመረምር ይጋብዙናል፡፡ አገርን፣ ባንዲራን፣ እምነትንና… መሰል የማሕበራዊ እሴቶችን ሕልውና ለማስጠበቅ ሕይወቱን ሳይቀር ለመክፈል የማያቅማማ ትውልድ፤ ቢር ለእውነት ዘብ በመቆም ቢት ደግሞ እምነትን ሳያስደፍሩ የጀግና ሞት ለመሞት ይናፈቅ የነበረበት ዘመን ፤ ከግል ምቾቱ ይልቅ ለሀገራዊና ሃይማኖታዊ ራእዮች ይተጋ የነበረ ማሕበረሰብ…  አልፎ …  ስስትና ራስ ወዳድነት ያሳወረው… ከቁሳዊ ፍላጎቱ አርቆና አሻግሮ ማየት የተሳነው… የሚሞትለት ቀርቶ የሚኖርለት ዘላቂ አላማ የሌለው… ነገር ግን በድንቃድንቅ የቴክኖሎጂ ግኝቶች የተከበበ ትውልድ የተተካበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡

ይህ ገለጻ በእርግጥ ያለንበትን ትውልድ ሁኔታ በትክክል ያሳያልን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚሉት የጨለምተኝነት አመለካከት ውጤት ይሆን?

በመቀጠል አይኖቻችን እንዲገለጡ… የተዘፈቅንበትን አዘቅት ጥልቀት በቅጡ እንድንረዳ… እንዴት እንዲህ ወዳለ ክፉ ማጥ ውስጥ ልንገባ እንደበቃን እንድንገነዘብና… አልፎም ‹ምን ይበጃል›ን አስከትለን መፍትሔ ለማግኘት እንድንንቀሳቀስ በፈርጅ  በፈርጁ የገባንበትን ማሕበራዊ ምስቅልቅል በመረጃ አስደግፈን እንቃኛለን… ማስተዋሉን ያድለን ይከታተሉን፡፡




በአገራችን ኢትዮጵያ ትምህርት የቀመሱና ኑሯቸውን በከተሞች ያደረጉ ወላጆች ልጆቻቸው የምእራቡን አለም ፊልሞችና ዘፈኖችን እንዲመለከቱ ሲፈቅዱ ማየት የተለመደ ነው… ድርጊቱን የስልጡንነት መገለጫ አድርገው የሚቆጥሩም አይታጡም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ወላጆች ይህን የሚያደርጉት ልጆቻቸው አለም አቀፋዊ ቋንቋ የሆነውን እንግሊዝኛን አቀላጥፈው ሲናገሩ ለማየት ካላቸው ጉጉት የመነጨ ነው፡፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችና መንፈሳውያን ከሆኑ ወላጆች መካከል እንኳ ሳይቀር ልጆቻቸው በቲቪ ሲተላለፍ ልክ እንዳዩት አስመስለው የእንግሊዝኛ ሙዚቃን ለማቀንቀን ሲኮላተፉ በሚመለከቱበት ወቅት በፈገግታ ማለፍ የሚቀናቸው አሉ፡፡ መጥፎ አርአያ ከሆኑ እኩዮቻቸው ተጽእኖ ለማራቅ በማሰብ ልጆቻቸውን ከቤት እንዳይወጡ የሚከላከሉ… በቀን ለ24 ሰአታት ያለማቋረጥ የሆሊዉድ ፊልሞችን የሚያስተላልፍ ዲሽ ለመትከል ግን ለአፍታ እንኳ የማያቅማሙ ወላጆችም ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በነሱ እይታ በቴሌቪዥኖች የሚተላለፉት የመዝናኛ ስርጭቶች እዚህ ግባ የሚባል ጉዳት አያስከትሉም፡፡

በርካታ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ወላጆች ገቢያቸውን ለማሳደግ ከስራ ሰአት በተጨማሪ ከልጆቻቸው ጋር ሊያሳልፉት በሚገባቸው ጊዜ ሳይቀር ሲባክኑና ደፋ ቀና ሲሉ የሚውሉ ናቸው፡፡ በመሆኑም በስራ መደራረብና በጊዜ ማጣት የተወጠሩት ወላጆች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቴሌቪዥንን ፋታ የምትሰጣቸው ሞግዚት አድርገው ከመቀበልም አልፈው የወላጅ ብቸኛ መብትና ሐላፊነት የሆነውን ልጆችን የማስተማርና የመገሰጽ ተግባርን ሳይቀር ለፊልሞችና ለዘፈኖች አሳልፈው ሲያስረክቡ ይታያል፡፡ የሚዲያዎችን በተለይም በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ምእራባዊ ቃናን የተላበሱ ፕሮግራሞችን ጎጂነት በመጠኑም ቢሆን የተገነዘቡ ወላጆች እንኳ ቴሌቪዥን የልጆቻቸውን ቀልብ ገዝቶ በመያዝ እነርሱን ፋታ እንዲያገኙ ስለሚያግዛቸው እልፍ ሲሉ የሚያዩዋቸውን መልካም ያልሆኑ ድርጊቶች እንኳ አይተው እንዳላዩ ቸል ለማለት አያቅማሙም፡፡

ነገር ግን የሕልውናችን ፈርጦች የሆኑ ልጆቻችንን አስረክበናት እየሄድን ያለነውና የሳሎኖቻችን ሞገስ ያደረግናት አዲሷ ሞግዚት በርግጥ የምትታመንና ለአደራ የምትበቃ ናትን? ብዙዎቻችን እንደምናምነውስ የቴሌቪዥን አሉታዊ ተጽእኖ ዘላቂ ጉዳት የማያደርስ ቀላል ጉዳይ ነውን? ከዚህ በታች በመረጃ አስደግፈን እንደምንመለከተው መልሱ ከምንገምተው ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡

በሊችተር፣ ሊችተርና ሮትማን የተከናወነና ለ4 አስርት አመታት በዘለቀው የቴሌቪዥን ተጽእኖ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የጥናት ሪፖርት እንደሚያመለክተው በአማካይ በሰአት እስከ 50 ወንጀሎችና ከደርዘን በላይ የሚደርሱ የነፍስ ግድያዎች በምእራባውያን ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ይታያሉ፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት አንድ ሰው የ17 አመት እድሜ ላይ ሲደርስ ከ800 ሺ እስከ 1.5 ሚሊዮን የሚደርሱ የጭካኔ ድርጊቶችና ከሩብ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ነፍስ ግድያዎችን ይመለከታል ማለት ነው፡፡

ከ1955 ዓ.ም አንስቶ ባሉት አመታት የፊልም ገጸ ባሕርያት በገሀዱ አለም ከሚሆነው አንድ ሺ እጥፍ በላቀ ሁኔታ በቴሌቪዥን ስክሪኖች ሲገደሉ ይታያሉ፡፡ በፊልሞች የሚታየው ግድያ በገሀዱ አለም ቢፈጸም የሀገራችን ሕዝብ በስምንት ቀናት ውስጥ ያልቅ እንደነበር ማስተዋል ጉዳዩ ምን ያህል አንገብጋቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ያሳያል፡፡

ላለፉት 7 አስርት አመታት ያለማቋረጥ በአሜሪካ ሕዝብ ላይ የወረደው የፊልሞች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና የዘፈን አልበሞች ጎርፍ ለማያባራ የዝሙት ፣ የጭካኔ ድርጊትና ጥንቆላ ሱስ ዳርጓቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በ21ኛው መ.ከ.ዘ. መባቻ አገሪቱና (ወደምትገሰግስበት ገደል በጭፍን የሚከተላት የተቀረው ዓለም) ለማመን በሚያዳግት ሁኔታ አቻ ወደሌለው የጥፋትና የጭካኔ ማጥ ውስጥ ለመዘፈቅ በቅተዋል፡፡

ታዋቂው ጋዜጠኛ ስቲቭ አለን ለስኬትና ዝና ባበቁት የሚዲያ ተቋማት ላይ ጣቱን በመቀሰር በሚያስተላልፏቸው ፕሮግራሞች ላይ የተቃውሞ ድምጹን ያሰማል፤ ‹‹ቴሌቪዥን ሕጻናትን ወደ ሞራል ዝቅጠት እየመራ ነው›› ይላል ሚስተር አለን፡፡ የሚዲያ ከበርቴው ቴድ ተርነርም በተመሳሳይ ፊልሞች የጭካኔ ተግባራትን  እንደሚቀሰቅሱ አይክድም፡፡

‹‹ጆሮ ሰጥተን ያደመጥነው (በጄ በለን የተከታተልነው) ነገር ሁሉ ተጽእኖ እንደሚያሳድርብን የታወቀ ነው… እኒህ (በአመጻ/ጭካኔ ድርጊቶች የተሞሉ) ፊልሞችና የቲቪ ፕሮግራሞችም ተጽእኖ ያሳድሩብናል፡፡ ቤተሰብህ ጽኑ መሰረት የሌለው ከሆነ ደግሞ (የሚዲያ ውጤቶች) የሚያሳድሩብህ ተጽእኖ በዚያው ልክ ይጨምራል… በከተሞቻችን የሚኖሩ ቤተሰቦች ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ከባባድ ችግሮች ተጋርጦባቸዋል - በሕይወት ዘመናቸው የቤተሰብ ፍቅር ያላገኙና ብስጭትና በብሶት የተሞሉ  ሰዎች በጭካኔ ድርጊቶች የተሞሉትን ፕሮግራሞች እንዲመለከቱት ካደረክ ውጤቱ እሳት ላይ ነዳጅ የመጨመር ያህል ይሆናል፡፡››
ኤል ኤ ታይምስ 4/3/94 ካሌንደር ኮሌክሽን

ከመጠን በላይ በጭካኔ ድርጊቶች፣ አሳፋሪ የዝሙት ተግባራት እና ጸያፍ ስድቦች የተሞሉ የቲቪ ፕሮግራሞችን በመመልከት ሱስ በርካቶች መለከፋቸው በራሱ አሳሳቢ ቢሆንም ችግሩ ግን በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ከጥፋት ልኡካኑ ወገን የሆነው ቴድ ተርነር በግልጽ እንዳመነው በጭካኔና ጎጂ ተግባራት የተሞሉት የመዝናኛ ፕሮግራሞች በተመልካቾቻቸው ላይ ተጨባጭ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እያመጡ ሲሆን እያስከተሉት ያለው ጉዳትም በበርካታ የማሕበራዊ ሕይወት ገጽታዎች ላይ በግልጽ እየታየ ይገኛል፡፡

የሬዲዮ ፕሮግራሞች አዘጋጅና የፊልም ሐያሲ የሆነው ማይክል ሜድቬድ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በገሀዱ አለም ላይ እየተበራከቱ ለመጡት የጭካኔና የአመጻ ድርጊቶች ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እንዲህ ያጋልጣል፡፡

‹‹በ1982 የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ የጤና ዘረፍ ጠቅላይ ጽ/ቤት ባወጣው 5 ዶሴ ሙሉ መረጃ የያዘ ሪፖርት ለተራዘመ ጊዜ የጭካኔ ድርጊት የተሞሉ የቴሌቪዥን ዝግጅቶችን መመልከት ለአመጻና ጭካኔ ተግባራት እንደሚገፋፋ በማያወላዳና በሳይንሳዊ መረጃ በተደገፈ ሁኔታ ደምድሟል፡፡ የኤቢሲ ቴሌቪዥን ግን ለዚህ ሪፖርት ባወጣው ኢፋዊ ምላሽ ‹የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በገሀዱ አለም በሰዎች ጠባይ ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ የሚያስረግጥ አንዳችም ሳይንሳዊ ማስረጃ አላገኘንም› ብሏል፡፡ የኤቢሲ ቴሌቪዥን በርግጥ ይህን የሚያምን ከሆነ ምርቶቻቸውን ለሚያስተዋውቁ ድርጅቶች ካሳ ሊከፍል ይገባዋል፤ ምክንያቱም የቴሌቪዥን ስርጭቶች በሰዎች ጠባይ ላይ አንዳችም ተጽእኖ የማያሳድሩ ከሆነ ታዲያ ምርት ማስተዋወቂያ የአየር ሰአት ለምን ይሸጣሉ?››
ማይክል ሜድቬድ፣ የፊልም ሐያሲና የሬድዮ ፕሮግራሞች አዘጋጅ

ናሽናል ኢንስቲትዩት ኦፍ ሜንታል ሔልዝ የተሰኘ ተቋም በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች የሚተላለፉ በጭካኔ ድርጊት የተሞሉ ፊልሞችና በገሀዱ አለም የሚታዩ የአመጻ ተግባራት ተመጋጋቢ መሆናቸውን ባካሄዳቸው ከአንድ ሺ የሚበልጡ ጥናቶች አረጋግጧል፡፡ የነሱ ማስጠንቀቂያ ግን በአሜሪካ ብቻ 50 000 የሚደርሱ ቴሌቪዥኖች በየቀኑ ከመሸጥ አላገዳቸውም፡፡

ይህን ተከትሎም የፊልሞች ሰለባ የሆኑ በርካታ ወጣቶች አቅላቸውን እየሳቱና እንስሳዊ ባሕርይን እየተላበሱ ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ አጥኚዎች የኮምፒውተር ቀመር ተጠቅመው በነደፉት መላምታዊ ሞዴል ላይ በመመስረት በቀጣይ ጥቂት አመታት ከፍተኛ የሆነ የወንጀል ማእበል እንደሚመጣ ሙያዊ ትንታኔያቸውን ይሰጣሉ፤ የጥናት ውጤታቸውን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ከወንጀል ፈጻሚዎቹ አብዛሃኛዎቹ ወንበዴዎችና ስርአት አልበኞች ሳይሆኑ ቀጪ ያጡና ፊልም ላይ ያዩትን ትወና በገሀዱ አለም ከመድገም ወደኋላ የማይሉ ለጋ ታዳጊዎች መሆናቸው ነው፡፡

መቀመጫውን በኖርዝ ዌስት ዩኒቨርስቲ ያደረገው የወንጀል ምርመራ ሳይንስ ዲፓርትመንት ባለሙያ የሆነው ጄምስ ፎክስ ታዳጊዎች ከአዋቂ ሰዎች በበለጠ አደገኞችና የወንጀል ድርጊቶች ለመፈጸም የተጋለጡ መሆናቸውን ከነምክንያቱ እንዲህ ያስቀምጣል፡-

‹‹… በዘመናችን ሰው መግደል በቀደሙት ዘመናት እንደነበረው ነውርና የማይታሰብ አይደለም፡፡ ይህ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ የቴሌቪዥን ተጽእኖ ነው፡፡ አሁን ሕጻናትና (ታዳጊዎች) ሞትና ነፍስ ግድያን መመልከት ተላምደውታል፡፡ ፊልሞችን ተከራይተው ሲያበቁ የሚወዷቸውን የፊልም ክፍሎች (በተለይ በጭካኔ የተሞሉትን) ይመርጡና ደግመው ደጋግመው ይመለከቱታል፡፡ ስለ ጾታዊ ግንኙነት አንዳችም ግንዛቤ ያልነበረው አንድ ታዳጊ ለመጀመሪያ ጊዜ እንስሳዊ በሆነ ሁኔታ ሴቶች በጉልበት ሲደፈሩ ፊልም ላይ ሲመለከት ሰቅጣጩ ትእይንት ምን አይነት ተጽእኖ ሊያስከትልበት እንደሚችል መገመት ትችላለህ? በጣም አስከፊ ምስል ነው… ሕጻናት ደግሞ እጅጉን ለተጽእኖ የተጋለጡ ናቸው፡፡››
ሚዲያ ዋይዝ፣ ቴድ ባኤህር፣ ገጽ 107

ይህን ሁሉ ግምት ውስጥ ስናስገባ… ከ22 እስከ 34 በመቶ የሚሆኑ ጭካኔ የተመላባቸውን ወንጀሎች በመፈጸማቸው ወሕኒ የወረዱ ወጣት ታራሚዎች ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ ያዩዋቸውን የወንጀል አፈጻጸም ዘዴዎች ሆን ብለው መኮረጃቸውን እንዳመኑ የኤቢሲ ቴሌቪዥን በቅርቡ መዘገቡ እምብዛም አይደንቀንም፡፡

ይቆየን

        


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።

No comments:

Post a Comment