በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
Did you remember a film which encourages you not to have sex before marriage? click here.
ከላይ
እንደተመለከትነው ወጣቶች እስከዛሬ ከተመለከቷቸው ፊልሞች መካከል ከትዳር በፊት ከሚደረግ ጾታዊ ተራክቦ እንዲታቀቡ የሚመክሩ
ካሉ እንዲያስታውሱ ተጠይቀው ነበር፡፡ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ወጣቶች ሁሉ አንድ እንኳ ፊልም መጥቀስ ተቸግረው ግራ ሲጋቡ
መመልከት ስለሆሊውድ ፊልሞች መጠነኛ ግንዛቤ ላላቸው ሰዎች እምብዛም አስገራሚ አይሆንም፤ አንድም የለምና!
"… የሰራሁት ፊልም ሁሉን ይዟል ፤ ጭካኔ
ጾታዊ ግንኙነት ፤ በጣም ጸያፍና ዘግናኝ ትዕይንቶች ፤ ቀልብ የሚገዙና ልብ የሚሰቅሉ ፍልሚያዎች … ሁሉን አካቷል ፤ በቃ
ያልያዘው ነገር የለም ፤ ይህን ያደረኩት ታዲያ ሰዎች መጥተው እንዲያዩት ካለኝ ፍላጎት የተነሳ ነው…" ፍራንሲስ ፎርድ ኮፖላ ፤
የጎድ ፋዘር ፤ አሜሪካን ግራፊቲ ፤ ፍራንከንስታይን ፊልሞች ዳይሬክተር
"… ፊልም የመስራት ሞያ ፤ ተመልካቹ
ሳያስተውል እንግዳ አስተሳሰቦችን የማስረግ ጥበብ ነው ፤ በዚህ መልኩ ስናየው ወጣ ያለ ፊልም የመስራት ሂደት ፤ ሆን ብሎ
የተመልካችን አስተሳሰብ ከማዛባትና ከማዳከም ሴራ /ሰቨርዥን/ ጋር የተያያዘ ነው …" አለን ሩዶልፍ ፤ የሜድ ኢን ሄቨን ፤ ኢኩዊኖክስ ፤ ... ፊልሞች ዳይሬክተር
"… የፊልም ስክሪፕት በየአስራ አምስት ገጹ
እርቃን የሚያሳይ ትእይንት መያዝ አለበት ፤ … በየአስራ አምስት ገጹ ፤ ልብ አድርግ
… የተዋናይዋን እግሯን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል ፤ ወይም ሙሉ እርቃኗን ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን በየአስራ አምስት ገጹ የእርቃን ትእይንቶችን በማካተት የተመልካችን ቀልብ ገዝተህ ልትጓዝ ይገባሃል …" ማርቲን
ኮርሲስ የዘላስት ቴምፕቴሽን ኦፍ ክራይስት ፤ ጉድ ፌላስ ፤ ዘ ዲፓርትድ ፤ ... ፊልሞች ዳይሬክተር
ለመሆኑ
የፊልም አዘጋጆችና ዳይሬክተሮች ሕሊናቸውን ሸጠው በነቂስ በሰፊዋ የጥፋት መንገድ ለመንጎድና በፊልም ውጤቶቻቸው ዘግናኝና
አስጻያፊ የሆኑ ዝሙት ቀስቃሽ ትዕይንቶችን ለማካተት የፈቀዱበት ምክንያቱ ምን ይሆን? በርካታ ለዘርፉ ቅርበት ያላቸው ውስጥ
አዋቂ አጥኚዎች ለዚህ መንስኤ የሚሆኑና በበቂ መረጃ የተደገፉ በርካታ አመክንዮዎችን የሚጠቅሱ ሲሆን የተቀሩትን በይደር ትተን
ከእነዚህ መካከል አንዱን ማንሳት በቂ ይሆናል - ኢኮኖሚያዊ ትርፍን፡፡
ጥናቶች
እንደሚጠቁሙት የፊልም ኢንዱስትሪው ዋነኛ ሸማቾች ከሆኑት መካከል በግምባር ቀደምትነት የሚገኙት ከ12-18 የእድሜ ደረጃ ላይ
የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ናቸው፡፡ እኒህ በእድሜ ለጋ የሆኑ የፊልም ደምበኞች ፤ ስራ የመስራት ግዴታ የሌለባቸው ፤ ለዋዛ ፈዛዛ
የሚሆን በቂ ጊዜ ያላቸውና ወላጆቻቸው ወዛቸውን አንጠፍጥፈው የሚያገኙትን ገቢ በግድ የለሽነት ለመበተን የማያቅማሙ
እንደመሆናቸው መጠን በመዝናኛ ኢንዱስትሪው የወርቅ እንቁላል እንደምትጥል ዶሮ ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡
እንደእሳት
መያዣ መጨበጫ በሌለው አስቸጋሪ እድሜ ላይ ላሉት እኒህ ታዳጊዎች ምን አይነት ይዘት ያላቸው የፊልምና የሕትመት ውጤቶች በቀላሉ
በኪሳቸው የያዙትን ገንዘብ አሟጠው እንዲያራግፉ ይገፋፏቸው ይሆን? በቀላሉ ለመገመት እንደሚቻለው ዝሙት ቀስቃሽና የጭካኔ
ድርጊቶች ያሉባቸው ፊልሞች ናቸው፡፡
… Do you want what kids want? … well, this may sound silly to you … but
kids go completely aped if you do three things … 1. Defiey authority 2. Destroy
property and 3. Take people clothe off. …
በሚዲያዎች
በሚዘወተሩ ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች ላይ ያተኮሩ በርካታ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እኒህ አጸያፊ ትእይንቶች በታዳጊዎችና በወጣቶች
ብሎም በአጠቃላይ የዘመኑ ትውልድ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ በማስከተል ላይ ይገኛሉ፡፡ አስነዋሪ ትእይንቶች በትውልዱ ላይ
እያስከተሉት ያለውን ተጽእኖ ካጋለጡ ጥናቶች መካከል የተወሰኑትን እንደማስረጃነት ለአብነት እንመልከት፡-
… የአየር ሰአቱን ከተቆጣጠሩት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ሁለት ሶስተኛ (64%) የሚሆኑት ለዘብ ያሉ ዝሙት ቀስቃሽ ትዕይንቶች፣ አንድ ሶስተኛ (32%) የሚሆኑት ልቅ የፍትወት ተግባራት፤ አንድ ሰባተኛ (14%) የሚሆኑት ደግሞ ግልጽ ጾታዊ ተራክቦ ሲፈጸም ይታይባቸዋል … ከይዘር ፋሚሊ ፋውንዴሽን
… ከአንድ ሰአት ላነሰ ጊዜ የኤም ቲ ቪ የሙዚቃ ፕሮግራሞችን እንዲመለከቱ የተደረጉ የ7ኛ እና 9ኛ ክፍል ታዳጊዎች ፤ ካልተመለከቱት ታዳጊዎች በተለየ ‹ከትዳር በፊት ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ ምንም ችግር የለውም› የሚል አመለካከት ለማዳበር ይበቃሉ… ግሪንሰን እና ዊሊያምስ /1986
ካልፊን፣ ካሮልና ሽሚድት (1993) ባዘጋጁት ጥናታዊ ሪፖርት በተመሳሳይአንድ የሙዚቃ ቪዲዮ እንዲመለከቱ የተደረጉ የኮሌጅ ተማሪዎች ካልተመለከቱት በላቀ ሁኔታ ቅድመ-ትዳር ለሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት በጎ አመለካከት አንጸባርቀዋል፡፡
ግሪንበርግ የተሰኘ ተመራማሪ እንዲሁ በሁሉም አይነት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ በአማካይ በሰአት ሶስት ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች እንደሚተላለፉ በመረጃ በተደገፈው ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ በዚህም መሰረት ሰዎች በአዘቦት ቀናት በአማካይ በቀን አንድ ሰአት በእረፍት ቀናት ደግሞ በአማካይ ለሁለት ሰአታት ቴሌቪዥን ይመለከታሉ በሚል እሳቤ (ይህ ስሌት እንግዲህ በአመዛኙ ቴሌቪዥን የማየት ሱስ ለተጠናወተው የምዕራቡ አለም ተመልካች እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ልብ ይሏል) ያሰላው ግሪንበርግ አንድ ተመልካች በአማካይ በሳምንት 27 ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶችን በአመት ደግሞ 1400 ትእይንቶችን በትንሹ እንደሚመለከት ዘግቧል፡፡
ሃዋርድ በ 1985 ወደ 1000 በሚደርሱ ታዳጊዎች ላይ ባካሄደው ሌላ ጥናት ቴሌቪዥን ታዳጊዎች ጾታዊ ተራክቦ አለጊዜያቸው እንዲጀምሩ ከሚያደርጓቸው ተጽእኖዎች መካከል ዋነኛውና ከፍተኛው እንደሆነ ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡
የታይም/ሲ. ኤን. ኤን የሕዝብ አስተያየት ውጤት ላይ ተመስርቶ ስትሮጅሂል በ 1998 ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከአሜሪካውያን ታዳጊዎች መካከል 29 በመቶ የሚሆኑቱ ቴሌቪዥንን ስለጾታዊ ተራክቦ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ እንደሆነ ጠቅሰዋል፤ ይህም በ1986 11 በመቶ ብቻ እንደነበር ሲታሰብ በተለይ ታዳጊዎች ምን ያህል ከጊዜ ወደ ጊዜ በቴሌቪዥን ተጽእኖ ስር እየወደቁ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ወደ 45 በመቶ የሚሆኑት ታዳጊዎች ደግሞ ስለ ጾታዊ ተራክቦ አብዛኛውን መረጃ የሚያገኙት ከጓደኞቻቸው እንደሆነ ሲገልጹ ስለዚህ ጉዳይ የመረጃ ምንጮቻችን ወላጆቻችን ናቸው ያሉ ግን 7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ እንግዲህ የወላጅ ምክር ተዘንግቶ በምትኩ የሚዲያዎች ተጽእኖ ምን ያህል የልጆቻችንን አኗኗር እየቀረጸ እንደሆነ ከዚህ በላይ መረጃ አያሻንም፡፡
… የአየር ሰአቱን ከተቆጣጠሩት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ሁለት ሶስተኛ (64%) የሚሆኑት ለዘብ ያሉ ዝሙት ቀስቃሽ ትዕይንቶች፣ አንድ ሶስተኛ (32%) የሚሆኑት ልቅ የፍትወት ተግባራት፤ አንድ ሰባተኛ (14%) የሚሆኑት ደግሞ ግልጽ ጾታዊ ተራክቦ ሲፈጸም ይታይባቸዋል … ከይዘር ፋሚሊ ፋውንዴሽን
… ከአንድ ሰአት ላነሰ ጊዜ የኤም ቲ ቪ የሙዚቃ ፕሮግራሞችን እንዲመለከቱ የተደረጉ የ7ኛ እና 9ኛ ክፍል ታዳጊዎች ፤ ካልተመለከቱት ታዳጊዎች በተለየ ‹ከትዳር በፊት ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ ምንም ችግር የለውም› የሚል አመለካከት ለማዳበር ይበቃሉ… ግሪንሰን እና ዊሊያምስ /1986
ካልፊን፣ ካሮልና ሽሚድት (1993) ባዘጋጁት ጥናታዊ ሪፖርት በተመሳሳይአንድ የሙዚቃ ቪዲዮ እንዲመለከቱ የተደረጉ የኮሌጅ ተማሪዎች ካልተመለከቱት በላቀ ሁኔታ ቅድመ-ትዳር ለሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት በጎ አመለካከት አንጸባርቀዋል፡፡
ግሪንበርግ የተሰኘ ተመራማሪ እንዲሁ በሁሉም አይነት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ በአማካይ በሰአት ሶስት ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች እንደሚተላለፉ በመረጃ በተደገፈው ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ በዚህም መሰረት ሰዎች በአዘቦት ቀናት በአማካይ በቀን አንድ ሰአት በእረፍት ቀናት ደግሞ በአማካይ ለሁለት ሰአታት ቴሌቪዥን ይመለከታሉ በሚል እሳቤ (ይህ ስሌት እንግዲህ በአመዛኙ ቴሌቪዥን የማየት ሱስ ለተጠናወተው የምዕራቡ አለም ተመልካች እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ልብ ይሏል) ያሰላው ግሪንበርግ አንድ ተመልካች በአማካይ በሳምንት 27 ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶችን በአመት ደግሞ 1400 ትእይንቶችን በትንሹ እንደሚመለከት ዘግቧል፡፡
ሃዋርድ በ 1985 ወደ 1000 በሚደርሱ ታዳጊዎች ላይ ባካሄደው ሌላ ጥናት ቴሌቪዥን ታዳጊዎች ጾታዊ ተራክቦ አለጊዜያቸው እንዲጀምሩ ከሚያደርጓቸው ተጽእኖዎች መካከል ዋነኛውና ከፍተኛው እንደሆነ ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡
የታይም/ሲ. ኤን. ኤን የሕዝብ አስተያየት ውጤት ላይ ተመስርቶ ስትሮጅሂል በ 1998 ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከአሜሪካውያን ታዳጊዎች መካከል 29 በመቶ የሚሆኑቱ ቴሌቪዥንን ስለጾታዊ ተራክቦ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ እንደሆነ ጠቅሰዋል፤ ይህም በ1986 11 በመቶ ብቻ እንደነበር ሲታሰብ በተለይ ታዳጊዎች ምን ያህል ከጊዜ ወደ ጊዜ በቴሌቪዥን ተጽእኖ ስር እየወደቁ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ወደ 45 በመቶ የሚሆኑት ታዳጊዎች ደግሞ ስለ ጾታዊ ተራክቦ አብዛኛውን መረጃ የሚያገኙት ከጓደኞቻቸው እንደሆነ ሲገልጹ ስለዚህ ጉዳይ የመረጃ ምንጮቻችን ወላጆቻችን ናቸው ያሉ ግን 7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ እንግዲህ የወላጅ ምክር ተዘንግቶ በምትኩ የሚዲያዎች ተጽእኖ ምን ያህል የልጆቻችንን አኗኗር እየቀረጸ እንደሆነ ከዚህ በላይ መረጃ አያሻንም፡፡
ኢፍ ዩ ሲክ ኤሚ -
የሆሊውድ ዘፈኖች ውስጥ የተመሰጉ የርኩሰት መልዕክቶች አንዱ ማሳያ
ሊዮኒ
ባርሰንባች የተሰኘች በሲድኒ የምትኖር አንዲት የቤት እመቤት ዘፈን ውስጥ የተመሰጉ ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች ጓዳዋን እንዴት
እንዳወኩት እንደሚከተለው ትገልጻለች፤ ‹የ5 እና የ7 አመት ልጆቼ በቤታችን እየተዘዋወሩ (ለጆሮ የሚቀፍ የዝሙት ቃል) እየጠሩ
ሲዘፍኑ ስሰማ በጣም ነው የደነገጥኩት፤ ድርጊቱን ለማመን ከብዶኛል… ምን እያሉ እንደሆነ ስጠይቃቸው የብሪትኒ ስፒርስ (ዘፈን)
እንደሆነ ነገሩኝ፡፡ በጣም ነው የዘገነነኝ… በጣም ክብር የሚነካ ነገር ነው፡፡ እንደተጭበረበርኩ ተሰምቶኛል፡፡›
ከላይ
ከላይ ሲታይ ‹ኢፍ ዩ ሲክ ኤሚ› የተሰኘው የብሪትኒ ዘፈን ኤሚ
ስለተሰኘች አንዲት ምናባዊ ገጸ ባሕርይ የሚያጠነጥን ይመስላል፡፡ ይህ ግን የዘፈኑ ሰም ነው፡፡ የምስጢር መልእክቱ እጅግ
አስነዋሪ ከመሆኑ የተነሳ ድርጊቱን ታዋቂነት ከመቀዳጀትአልያም የአልበም ሽያጭ ከማሳደግ አንጻር ብቻ ለመተነተን አዳጋች
ይሆናል፡፡ ኢፍ ዩ ሲክ ኤሚ የተሰኘው የዘፈኑ አዝማች የመጀመሪያ ፊደላት ድምጸት ኤፍ ዩ ሲ ኬ ሚ (FUCK ME) የሚል
አስነዋሪ የዝሙት ጥሪ ነው፡፡ እንግዲህ ይህን ለመድገም እንኳ የሚያጸይፍ መልእክት ትውልዱ በምን አይነት ርኩሰት እየተበከለ
እንደሆነ የጉዳዩን አንገብጋቢነት ለማሳየት ስንል ጠቅሰነዋል፡፡
‹የወደድነውን
መዝፈን መብታችን ነው፤ ልጆቻቸውን ማሳደግም ሆነ ምግባር ማስተማር የኛ ሓላፊነት ሳይሆን የወላጆች ነው› ትላለች ትውልድ አጥፊ
የሆኑ መርዛማ አስተምህሮዎችን በዘፈኖቻቸው አማካኝነት ከሚነዙት ዘፋኞች መካከል የሆነችዋ ክሪስቲና አጉሌራ፡፡
በዚህ
የማያባራና መቋጫ በሌለው እሰጥ አገባ መካከል ግን እምቦቃቅላዎች ሳይቀር በነዚህ ወደረኞች ዘፈን አዚም አእምሯቸው ናውዞ
ግጥሞቻቸውን በደመነፍስ እያቀነቀኑ ወደአይቀሬው የጥፋት ጎዳና በመንጎድ ላይ ናቸው…
በአገራችንም
በ60ዎቹ አነኤልቪስን በሚኮርጁ አቀንቃኞች መሪነት የተጀመረው የባሕል አብዮት በሕብረተሰቡ ስር ሰዶ ከፍተኛ የሆነ የአኗኗር
ለውጥ አስከትሏል፡፡
ይህን
ተከትሎም… በአንድ ወቅት እንደነውር ይታይ የነበረው ከጋብቻ ውጪ ጾታዊ ግንኙነት መፈጸም የተለመደ ከመሆን አልፎ ቀስ በቀስ
በድንግልና ጸንተው በሚቆዩት ላይ ሽሙጥና ስላቅ መሰንዘር የተጀመረበት፤ … ቅጥ ያጣ
ልቅ ዝሙት የሚያስከትለውን ያልተፈለገ እርግዝና ጉዳይ መፍትሔ ለመስጠት ምግባርን ከማስተማር ይልቅ ኮንዶም አጠቃቀምና የውርጃ
መፈጸሚያ ማእከላትን አድራሻ ለሕጻናት ሳይቀር ማመላከት የተመረጠበት … ይህን ተከትሎም በአገራችን በአስር ሺዎች በአለም አቀፍ
ደረጃ ደግሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናት ከማሕጸን ሳይወጡ የሚፈጁበት፤ … በጾታዊ ፍላጎት አለመጣጣምና ሌሎች መሰል ቁንጽል
ምክንያቶች ትዳር በቀላሉ የሚፈርስበትና የትዳር ጓደኛን እንደልብስ መለዋወጥ የተዘወተረበት ፤ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡
እንደ ዳቪንቺ ኮድ ያሉ ፍጥጥ ያሉ ጸረ ክርስቶሳዊ ፊልሞች የቦክስ ኦፊስ የደረጃ ሰንጠረዥን መቆጣጠር
ሲጀምሩ ነበር አሸልበው የነበሩት ክርስቲያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ጠንከር ያሉ የተቃውሞ ድምጾችን በሆሊውድ የፊልም ኢንዱስትሪና በሚዲያ ተቋማት ላይ ማሰማት የጀመሩት፡፡
ነገር ግን በዚህም ወቅት እንኳ ድርጊቱን አልፎ አልፎ የሚከሰትና በአንዳንድ ክርስትና ላይ ግላዊ ጥላቻን በሚያንጸባርቁ የፊልም
ዳይሬክተሮች/ፕሮዲዩሰሮች ከስንቴ አንዴ በተናጠል ከሚፈጸም ተግባር የዘለለ አድርገው አልተመለከቱትም፡፡ እናም የኒህን
የክርስትናን መሰረተ እምነት ጭቃ የሚቀቡ የፊልም ውጤቶች ተጽእኖ ለመቃወም ያደረጓቸው ጥረቶች አልፎ አልፎ ፊልሞቹን ከማሳገድ
አልያም በሕዝብ የሲኒማ ቤቶች እንዳይታዩ ከማስወሰን… ከዚያም ወደሞቀ እንቅልፋቸው መመለስ… በቃ ጥረታቸው ከዚህ የዘለለ
አልነበረም፡፡
እነዚህን አወዛጋቢ ፊልሞች የጥቂቶች ግላዊ ጥላቻ ውጤት አድርገው መመልከታቸው በራሱ ክርስቲያኖች ምን
ያህል ስለችግሩ ጥልቀትና ስፋት ያላቸው አመለካከት የተገደበ እንደሆነ ነው የሚያሳየው፡፡ የችግሩን ሁለንተናዊ ገጽታ ማየት
ስለተሳናቸው በማሕበረሰቡ ውስጥ የሰረጹ ክርስቲያናዊ እሴቶችና አስተምህሮዎች በሆሊዉድ የአመጻና የጽርፈት ላንቃ ጥላሸት
እንዳይቀቡና ክብራቸው እንዳይነወር በቡድን ተደራጅተው ያካሄዷቸው ጥረቶች ግባቸውን ሊመቱ አልቻሉም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ
እንደተለመደው ሆሊዉድ አዲስ ክርስትናን የሚያንቋሽሽ ፊልም ባስተዋወቀ ቁጥር የሚነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ከጥቂት ሳምንታት… ቢበዛ
ከወራት አያልፍም፤ ትንኮሳውም ሆነ ተቃውሞው አንዳች ትርጉም ያለው እልባት ሳይሰጠው ሌላ ተመሳሳይ አወዛጋቢ ፊልም አልያም
መጽሐፍ እስኪወጣ ድረስ ከናካቴው ይረሳል፡፡
በሆሊውድና በአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን እልፎ አልፎ የሚሰራጩት በክርስትና ላይ ያነጣጠሩ ለጆሮ የከበዱ
ስድቦችና ትችቶች የግለሰቦች አመለካከቶች እንጂ ተቋማቱን አይወክሉም የሚለው እሳቤ ከእውነት በእጅጉ የራቀ ነው፡፡ በተጨባጭ
ያሉትን መረጃዎች ሊመረምር ለፈቀደ ሁሉ ፍንትው ብሎ የሚታየው አሳዛኝ እውነታ ሆሊውድና የምእራቡ አለም ሚዲያና የመዝናኛ ኢንዱስትሪ
የከርስትና አስተምህሮዎችና በሕብረተሰቡ የሰረጹ የክርስትና መሰረት ያላቸው ያኗኗር እሴቶችን ለመሸርሸር ብሎም በባእድ
አስተሳሰቦች ለመተካት የተቀናጀ እንቅስቃሴ ላለፉት 50 አመታት እያደረጉ መሆኑ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እኒህ ክርስትና
ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ይበልጥ እየፈጠጡ መምጣታቸው ነው የአሁኑን ሁኔታ ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው፡፡
ላለፉት 50 አመታት የተላለፉ የሚዲያ ውጤቶችን ዋቢ በማድረግ የተደረጉ ጥናቶች ከየትኛውም ሐይማኖት
በተለየ የክርስትና መሰረተ እምነት ከምእራቡ አለም ሚዲያ የሚሰነዘሩ … ቅኔያዊ ይዘት ካላቸው ስውር ነቀፋዎች … ፍጥጥ እስካሉ
ማንጓጠጦችና ጸያፍ ስድቦች ድረስ … የበርካታ ትችቶችና የማጥላላት ዘመቻዎች ሰለባ እንደነበረ ያመላክታሉ፡፡
የሆሊውድ ልሂቃን ክርስትና ላይ ያላቸው አሉታዊ አመለካከት በርካታ የፊልምና የሚዲያ ፈርጦቻቸው በሚሰጧቸው መግለጫዎች
ወቅት በድፍረት በሚሰነዝሯቸው የመረረ ጥላቻን የጸነሱ ጽርፈትና ትችቶቻቸው በግልጽ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ‹ኧ ፊው ጉድ ሜን›
የተሰኘውን ታዋቂ ፊልም ጨምሮ በርካታ ሌሎች ፊልሞችን ዳይሬክት በማድረጉ የምናውቀው ሮብ ሬይነር አሌ ኤ ታይምስ ለተሰኘው
መጽሔት በሰጠው ቃለ ምልልስ ክርስቲያኖችን እንዲህ በማለት ያንቋሽሻል፤
“This kind of sanctimonious [***]… these right
wing, moral majority, these people are [***] destroying the country ... አጉል ቅዱስ እንሁን እያሉ የሚመጻደቁ
(...) እኒህ የቀኝ ክንፍ ወግ አጥባቂ (ክርስቲያኖችን ማለት ነው)፤ እኒህ ሰዎች ናቸው (…) ይህችን አገር
እያወደሟት/እያጠፏት ያሉት" ... Rob Reiner Director of A Few Good Men. LA Times 12/6/92
ተዋናይና ዳይሬክተር የሆነው ዝነኛው ስቴቨን
ሴጋል ለክርስትና ያለውን ንቀት ከመርዝ ጋር በማነጻጸር ይገልጸዋል፤ በኦሪትና ክርስትና ትውፊት ላይ የተመሰረተውን ባሕልና
አኗኗር… ስቴቨን ሴጋል … "(አለውዴታችን) ወደተወለድንበትና
እየተመገብነው ባደግነው በዚህ መርዝ በሆነው የአይሁድና የክርስትና ባሕል… … poisons that we as human beings are born with
and are indoctrinated into through our Judeo-Christian culture." በማለት አንቋሾታል፡፡
እኒህ ማስረጃዎች ላላሳመኗቸውና አሁንም
የሆሊውድ አቋም ግልጽ ላልሆነላቸው ተመልካቾች… ዋን ፈሊው ኦቨር ዘ ኩኩስ ኔስት የተሰኘውና… ጃክ ኒክልሰን መሪ ተዋናይ
የሆነበትን ፊልም ዳይሬክት ያደረገው የኬን ኪዚ ቀጣይ ንግግር
የማያወላዳ ምላሽ ይሰጣል፡፡ የአርቲስቱ ዋነኛ ተግባር ይላል ኬን ኪዚ…
“The job of the artist is to say [***] you God.
[***] you and the old Testament you rode in on! ... የአርቲስቱ ዋነኛ ተግባር አምላክን
(መስደብና) የተገለጥክበትን ብሉይ (እና አዲስ) ኪዳን
(መርገም) ነው" ... Ken Keasey, the creator of Jack Neckelson’s ‘One
flew over the Kuku’s Nest
የቀድሞ የሲ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ባለቤትና
አስተዳዳሪ የነበረው ቴድ ተርነር ክርስትናን የውዳቂዎች ሐይማኖት በማለት አብጠልጥሎታል፡፡ ከዚህ አልፎም የሚከተለውን ስላቅና
ስድብ የተሞላውን ንግግር በይፋ አድርጓል፤
"… እምነቴ መሠርሠር ጀመረ … አዎ አሁን
አማኝ አይደለሁም … እውነቱን ንገረን ካላችሁ … ይበልጥ እየካድኩ በሄድኩ ቁጥር ይበልጥ ጥሩ ስሜት ይሰማኝ ዠመር ..
(ኢየሱስ) ወደዚህ ወደታች ወርዶ ለኛ ሲል በመስቀል ላይ መከራ ሊቀበልና ሊሞት በቃ! … ለማመን ይከብደኛል! …" Ted Turner
ታይም ማሺን፣ ዋር ኦፍ ዘ ወርልድስ፣ እና
ዘ ኢንቪዚብል ማን የተሰኙ ፊልሞችን በመድረሱ በፊልም አፍቃርያን ዘንድ ታዋቂነትን ያተረፈው ኤች ጂ ዌልስ የአምላክን ሕላዌ
የሚገልጹ አስተምህሮዎችን ከምድረ ገጽ ማጥፋት የሕይወት ዘመኑ ዋነኛ አላማ አድርጎ ይንቀሳቀስ እንደነበረ ገልጾ ጽፏል፤ እንዲህ
ይላል ኤች ጂ ዌልስ፤
“Never had I hated God so intensely… I have a
sort of love for most living things, but cannot recall any time in my life when
I had the faintest shadow of an intimation or love for any one of the persons
of the Holy Trinity… But God, you are not much of a man. Leave me alone at any
rate. Else I will canvass against you. I will make your position unbearable. I
will jeer and make a mock of you. ... ለፈጣሪ ያለኝ ጥላቻ ገደብ የለውም…
ለአብዛኛዎቹ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ከሞላ ጎደል ፍቅርና አዘኔታ እንዳለኝ አምናለሁ፤ ነገር ግን ከሶስቱ ስላሴ ለአንዳቸውም
አንዳችም አይነት ፍቅር በሕይወት ዘመኔ የነበረበት አጋጣሚ ፈጽሞ አልነበረም… ፈጣሪ ሆይ… ወደ አጠገቤ እንዳትደርስ፤
አለበለዚያ በአንተ ላይ አመጻን አሴርብሐለሁ፤ … እሳለቅብሐለሁ" ... H. G. Wells creator of Time Machine, War of the
Worlds & The Invisible Man. Desperately Mortal, 1980, p. 216
ክርስቶስ
በመስቀል ላይ የተቀበለውን መከራ የሚያሳየው ፓሽን ኦፍ ዘ ክራይስት በአገራችን ሳይቀር በበርካታ ሰንበት ት/ቤቶች ለመታየት የበቃ ሲሆን የፊልም ኢንዱስትሪው ለክርስቲያኖች ያበረከተው
መልካም ስጦታ ተደርጎ በብዙዎች ይታያል፡፡ ነገር ግን የእርቃንና የግልጽ ዝሙት ላይ የሚተውኑ እንደሞኒካ ቤሉቺ (በፊልሙ ላይ
ማርያም መቅደላዊትን ሆና የተወነችው ማለት ነው ፤ የጲላጦስን ሚስት ሆና
እንደተወነችው ክላውዲያ ጌሪኒ ፤ እንዲሁም ዲያቢሎስን ሆና እንደተወነችው ሮሳሊንዳ ሴሌንታኖ) ያሉ በርካታ የፖርን ፊልም ተዋንያን በዚህ ስለቅድስና፣ ስለንጽሕናና ራስን
ስለመካድ በሚሰብከው የክርስቶስ የመስቀል ላይ መከራን የሚያሳይ ፊልም ላይ እንዴት ሊተውኑ በቁ? በፊልሙ ላይ ክርስቶስ
ለመግለጽ የሚከብድ ድብደባና ውርደት ሲቀበል የሚያሳየው ይሄ ፊልም ትንሳኤውንና መክበሩንስ ለምን ሳያሳይ ቀረ? የሚሉት
ጥያቄዎች የሆሊዉድ የፕሮፖጋንዳ ኢንዱስትሪ ሕቡእ አላማ ምን እንደሆነ ያሳብቃሉ፡፡
የሬዲዮ
ፕሮግራም አዘጋጅና የፊልም ሐያሲ የሆነው ማይክል ሜድቬድ ከሙያው ጋር በተያያዘ ብዙዎቻችን የማየት እድሉ የማያጋጥመንን
የሆሊውድ ኢንዱስትሪ ከመድረክ በስተጀርባ ያለውን እውነተኛ ገጽታ ለማየት የበቃ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡ ማይክል ሜድቬድ ታዲያ
በበርካታ አጋጣሚዎች ከፊልም ኢንዱስትሪው ዝነኛ ተዋንያንና ዳይሬክተሮች ጋር ባደረጋቸው ግንኙነቶች ወቅት በአብዛኞቹ
የኢንዱስትሪው ልሂቃን ላይ የሚስተዋለውን ለክርስትና ያላቸውን ገደብ የለሽ ጥላቻ ለመታዘብ በቅቷል፡፡
"በሆሊውድ
ልሒቃን ዘንድ የሚስተዋለው በአማኞች ላይ ያነጣጠረ የፈጠጠና ዘግናኝ ጥላቻ ያስገርማል ፤ ሁሌም በሆሊውድ ፊልሞች ላይ ባሁኑ
ዘመን ያሉ ሃይማኖተኞችን እንዲወክሉ የሚደረጉት ገጸ ባህሪያት ወይ እብዶች ፤ አልያም ሞኛሞኞች ፤ ጥቅም አሳዳጅ ሌቦች ፤
አንዳች ግድፈት ያለባቸውና ወራዶች ተደርገው ይቀረጻሉ…" Micheal Medved
ሚስተር
ሜድቬድ አያይዞም በአብዛኞቹ የሆሊውድ ፊልሞች ላይ ክርስቲያን እምነት ያላቸው ገጸ ባሕርያትን ሁሌም ወይ እብዶች፣ አልያም ሞኛ
ሞኞች፣ ወይም ጥቅም ፈላጊ (ሌቦች) ወይም አንዳች ግድፈት ያለባቸውና ወራዶች አድርገው ማቅረባቸውን ከዚህ ከጸነሱት ጥልቅ ጥላቻ
ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ያሰምርበታል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የሚዲያ ተቋማት እንደቀድሞው ተመልካቾች ተመራምረው የሚደርሱባቸውን ስውርና ቅኔያዊ የሆኑ
ጸረ ክርስትና ፕሮፓጋንዳዎችን በማሰራጨት ብቻ አልተወሰኑም፡፡ ሕብረተሰቡ ያለው ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ንቃቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየወረደ ፣ የሚዲያ ውጤቶች ይዘት ምን ይሁን ምን ይበልጡን ግድ የለሽ እየሆነ በመሄዱ በሚዲያ ውጤቶች ላይ የሚስተዋሉት ርኩሰቶችና
ስድቦች ይበልጥ እየጎሉና እየፈጠጡ ሄደዋል፡፡
የክርስቲያኖችን አስተምህሮና የአምልኮት መገለጫዎችን ለማንቋሸሽ ፣ ጭቃ
ለመቀባትና ለማስነወር የመዝናኛ ኢንዱስትሪው ለሕጻናት የሚዘጋጁ ፊልሞችን እንኳ ከመጠቀም ወደኋላ አላሉም፡፡
የገና
በአል አከባበርን የሚያሳየው (ከላይ የተመለከትነው) የሕጻናት ፊልም የጌታችን በበረት መወለድ የሚተርከው የታሪክ ክፍሉ ላይ
አሳፋሪ በሆነ መልኩ በተወከሉት ገጸ ባሕርያት አማካኝነት ሲሳለቁ ይታያል፤ ሕጻኑ ክርስቶስን ለማምለክ ከመጡት ሶስቱ የጥበብ
ሰዎች መካከል አንዱ ስራውን ረስቶ በእጣን ፋንታ ኩኪዝ ይዞ ሲቀርብ፣ እጣን ማምጣት እንደሚገባው ሲነገረው ኩኪሱን ሲበላው፣
በመሀል ሕጻኑ ክርስቶስ ከተኛበት ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ፣ ሲያጡት ፕሮግራሙ እንዳይቋረጥ ሌላ ሕጻን በምትኩ ተክተው ሲቀጥሉ፣
በሆነው ባልሆነው ፕሮግራሙ ሲበላሽና ሁሉም የሚጠበቅበትን ዘንግቶ
ሲደናበር ይታያል፡፡
የክርስትና አስተምህሮዎችን፣ ቀኖናዎችን፣ ባህላዊና ትውፊታዊ እሴቶችን እንዲሁም ግብረገባዊ መርሆዎችን የሚተቹና
የሚያንቋሽሹ ሌሎች ተጨማሪ የሚዲያ ውጤቶችን እስኪ ለአፍታ እንመልከት፤
ክርስቲያኖችን ደም የጠማቸውና ስለስልጣኔ
አንዳችም ግንዛቤ የሌላቸው ቡትቶ ለባሽ ደንቆሮዎች አድረጎ የሚስለው አጎራ የክርስቲያን ምእመናን እንደወሮበሎች ቤተ መጻሕፍትን
ሲያፈርሱ፣ መጻሕፍትን ሲያቃጥሉ፣ ፈላስፎችና ተመራማሪዎችን በሐይማኖት ስም ሲጨፈጭፉ ያሳያል፡፡ ክርስቲያኖቹ አይሁዳውያኑን
ሲጨፈጭፉ የሚያሳየው የፊልሙ ትእይንት ሆን ተብሎ በአውሽዊትዝ የአይሁድ እስረኞች ጣብያ (Aushwitz) ላይ የጀርመን ናዚዎች
የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ከሚያሳዩ ፊልሞች ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎ መሰራቱ ሕብረተሰቡ ናዚዎችን በሚያይበት አተያይ ክርስቲያኖችን
እንዲያይ የታቀደ ስነልቦናዊ ታክቲክ መሆኑን አንዳንድ ምሁራን ጠቁመዋል፡፡
ዘ ዳቪንቺ ኮድ (The Davinci Code): - ብዙዎቻችሁ
ተመልክታችሁት ይሆናል … ያም ሆኖ ጥቂት ማብራሪያ የሚያስፈልገው ነው … የፊልሙ ዋና ሀሳብ … ክርስቶስ በመስቀል ላይ አልሞተም
… ከመግደላዊቷ ማርያምም ጋር ጋብቻ መስርቶ ወደ ፈረንሳይ ሄዶ ይኖር ነበር … ልጆችም ነበሩት … የዘር ሀረጉም እስካሁን በዚያ
ይገኛል … የሚል በሬ ወለደ አይነት ነጭ ውሸት ነው … (ክርስቲያኖች ሆይ … እንዲህ አምላክ ሲሰደብና የአምላክ ስም ጭቃ ሲቀባ
ከማየት የሚበልጥ ምን በሀዘን የሚያደማ ነገር ይኖር ይሆን?)
ጁዳስ የተሰኘው የሌዲ ጋጋ የዘፈን ቪዲዮ:- በዚህ
የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ ክርስቶስና ደቀ መዛሙርቱ ሐዋርያት ሞተር ሳይክል እንደሚነዱ ጋንግስታሮች ተደርገው ቀርበዋል … ሌዲ ጋጋም ሴተኛ
አዳሪ ሊያስመስላት በሚችል መልኩ ተቀርጻ ክርስቶስን እንዲወክል ካስቀመጡት ወሮበላ ጀርባ ተቀምጣ ትታያለች … (ይህም ሆሊውድ እያቀነቀነው
የሚገኘው … ክርስቶስና ማርያም መግደላዊት ጾታዊ ግንኙነት ነበራቸው የሚለው ስድብ አካል ነው) … በክርስቶስ ላይ ማሾፍና መሳደባቸውን
ሲቀጥሉም … ሌዲ ጋጋ ክርስቶስን ወክሎ የቀረበውን የእሾህ አክሊል መሰል ጉንጉን አናቱ ላይ ያስቀመጠ ተዋናይ ትታ ከሀዲውን የአስቆሮቱ
ይሁዳ ወደ ወከለው ጋንግ/ተዋናይ ስትሄድና ለርሱም ውዳሴን ስታቀርብ ያሳያሉ … የሙዚቃ ቪዲዮው ርዕስም ‘Judas’
የመሆኑ
ምክንያት ይኼው ነው::
ጁዳስ - ትሬይተር ኦር ፍሬንድ ፡-
ይሁዳ ከሃዲ ወይስ የልብ ወዳጅ በሚል ርእስ የቀረበው የሂስትሪ ቻነል ታሪካዊ ዶክመንተሪ ይሁዳ የክርስቶስ የልብ ወዳጅ እንጂ
ከሀዲ እንዳልሆነ፣ ከሀዋርያት ሁሉ በተለየ የክርስቶስ አስተምህሮ እሱ ብቻ እንደገባውና፣ ጌታውን አሳልፎ የሰጠው የክርስቶስን
ፈቃድ ለመፈጸም እንደሆነ፣ እናም ሊሞገስ እንጂ ሊወነጀልና ሊረገም እንደማይገባው… የሚገልጹና ይህን የመሰሉ እጅግ አስጸያፊ
መከራከሪያዎችን በማቅረብ ተመልካችን ለማሳምን ይጥራል - ጥናታዊ ዘገባው፡፡
ዘ ኢንቬንሽን ኦፍ ላዪንግ፣ ብሩስ ኦልማይቲ፣ ኢቫን ኦልማይቲ፣ ኤጅ ዋን፣ ጁዳስ፣
ኪንግደም ኦፍ ሄቨን፣ ሊጅን የክርስትናን አስተምህሮ ከሚያንቋሽሹ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችና በቅዱሳን አባቶች ላይ ከሚያላግጡ
ፊልሞችና የሙዚቃ ቪዲዮዎች መካከል እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
ለመሆኑ መቼ ይሆን ዘወትር የሚያደነቁሩን ፊልሞችና ዘፈኖች ክርስትና ላይ
የተነጣጠሩ ጽርፈቶችና ማንቋሸሾች እንደሆኑ ተረድተን የክህደቱ ተባባሪ ከመሆን ራሳችንንና ወገናችንን የምንጠብቀው?
ይቆየን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።
ለመሆኑ መቼ ይሆን ዘወትር የሚያደነቁሩን ፊልሞችና ዘፈኖች ክርስትና ላይ የተነጣጠሩ ጽርፈቶችና ማንቋሸሾች እንደሆኑ ተረድተን የክህደቱ ተባባሪ ከመሆን ራሳችንንና ወገናችንን የምንጠብቀው?
ReplyDeleteam proud to be ur friend abelo