በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
“ወበከመ ኢሐለይዎ
ለእግዚአብሔር በልቦሙ ከማሁ እግዚአብሔርኒ ወወሀቦሙ ልበ እበድ ፤ … እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር
ይህን የማይገባውን ይሰሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው”
ሮሜ 1፡-28-29
" … I may not get there with you. But some day we shall enter the promise
land where men and women will not be judged by their sexual desires but by the content of their character.... (ያችን ቀን )… በሕይወት ኖሬ … አብሬያችሁ ላላያት እችላለሁ ፤ ነገር
ግን … አንድ ቀን … ወንዶችና ሴቶች … ባላቸው ጾታዊ ፍላጎት ሳይሆን … በስብዕናቸው ጥንካሬ ወደሚመዘኑባት የቃል ኪዳን
ምድር እንገባለን" ... ይህ የንግግር ክፍል … ከዛሬ ሃያ አመት በፊት … ሌሪ ክሬመር የተባለ … የግብረ ሰዶማውያን መብት ተሟጋች … ዋሽንግተን ዲ.ሲ. በሚገኘው … የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ተገኝቶ … ካሰማው ንግግር ላይ የተወሰደ ነው። … በወቅቱ … ይህ የሚ/ር ክሬመር ንግግር
… ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግር በቀጥታ የተቀዳ … የተውሶ ንግግር እንደነበረ … ከበርካታ ታዳሚዎቹ የተሸሸገ አልነበረም። … ያም ሆኖ … ሌሪ … የዶ/ር ማርቲንን ንግግር … ሆን ብሎ በማዛባት … " የቆዳ ቀለም" በሚለው ፋንታ "ጾታዊ ፍላጎት" የሚለውን ቃል መተካቱን ግን ያስተዋሉ ጥቂቶች ነበሩ:: … እንግዲህ በዚህ እሳቤ ነበር … (እ.ኤ.አ) በ1993 ዓ.ም
የተካሄደውና ‘ማርች ኦን ዋሺንግተን’ የተሰኘው … ታላቁ የግብረ ሰዶማውያን ሰላማዊ ሰልፍ … ዓላማውን … የወንድና የሴት ግብረሰዶማውያንን ፤
ፆታቸውን
በህክምና ያስቀየሩ ግለሰቦችንና ፤
የባይሴክሺዋሎችን መብት ማስከበር ላይ አድርጎ … ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው::
‘ማርች ኦን ዋሽንግተን’ የተሰኘው … ይህ የግብረ ሰዶማውያን ሰላማዊ ሰልፍ ከመካሄዱ ከ30 ዓመታት በፊት … ጥቁር አሜሪካውያን … በታዋቂው የጥቁሮች መብት ተሟጋች
… ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እየተመሩ … ባካሄዱት ከፍተኛ የትግል እንቅስቃሴ … የዘር መድልዎን ለማስቀረት በእጅጉ አስፈላጊ
የነበረው … ‘የማሕበራዊ መብት ረቂቅ’ (Civil Rights Act) … (እ.ኤ.አ) በ1964/65 እንዲተላለፍ ማድረግ ችለው
ነበር ፤ … በተመሳሳይ መልኩ … የግብረ ሰዶማውያኑና የሌሎች ጾታዊ ጠባይ ግድፈት ያለባቸው ግለሰቦች ጥምረት … የዶ/ር ማርቲንን ንግግር ከመኮረጃቸውና ፤ ከሌሎች
መሰል ጥረቶቻቸው እንደተስተዋለው … ዋና ፍላጎታቸው … የ1964ቱን የጥቁር አሜሪካውያን የሰብአዊ መብት የትግል ፈለግ በመከተል
… ጥቁሮች ያሳኩትን ግብ … ይኸውም … በአናሳ ማሕበረሰብነት የሕግ እውቅና የማግኘት ድል … መቀዳጀት ነበር:: … እዚህ ላይ
ታዲያ ልብ ሊባል የሚገባው ነጥብ … ጥቁር አሜሪካውያኑ … በአናሳ ማሕበረሰብነት የመታወቅ ሕገ መንግስታዊ መብት ለማግኘት የቻሉት
… በቀድሞ ታሪካቸው ከደረሰባቸው የዘር መድልዎና ጭቆና የተነሳ መሆኑን ነው፡፡
ባንጻሩ … የግብረ ሰዶማውያንና የሌሎች ጾታዊ ጠባይ ግድፈት ያለባቸው ግለሰቦች መብት ተሟጋቾች … በአናሳ ማሕበረሰብነት ለመታወቅ ሽተው … አደባባይ የወጡት ግን
… እንደ ጥቁር አሜሪካውያኑ … የእኩልነት መብትን ለማስከበር አልነበረም ፤ …
ምክንያቱስ … በሀገሪቱ ሕግ …
በ1ኛ እና 14ኛ የሕግ ማሻሻያዎች (ammendments) … እንዲሁም … በእያንዳንዱ የአሜሪካ ክፍለ ግዛት ሕገ መንግስት ላይ … ይህ የእኩልነት መብት ከተረጋገጠላቸው ቆይቶ ነበርና ነው:: … እውነተኛውና እኩዩ ዓላማቸው ግን …
የተለየ እውቅና ፣ መብትና የሕግ ከለላን በማግኘት … በአብዝሃው ሕብረተሰብ ዘንድ እንደጋጠወጥነት የሚታየውን
የአኗኗር ዘያቸውን … አለአንዳች እንቅፋት … እንደልባቸው ማስፋፋት ነበር::
ለመሆኑስ … ይህን በአናሳ ማሕበረሰብነት የመታወቅ
ልዩ ቸሮታ ሊያገኙ … በእርግጥ ይገባቸው ነበርን? … እውንስ … በነቂስ ወደ ዋሽንግተን የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ያወጣቸው ጉዳይ … ጥቁሮች እንደደረሰባቸው አይነት ያለ ግፍና መድልዎ ደርሶባቸው ነበርን? … ጥቁር አሜሪካውያኑ ለዘመናት ተሸከመውት የኖሩትስ … ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ የጭቆና ቀንበር .. በግብረ ሰዶማውያኑ ጫንቃ ላይ በርግጥ አርፎ ነበርን? … እንዲያውም!! … በአሜሪካ … ይህን ዘመቻ ያካሄዱ … የእነዚህን
ግብረ ሰዶማውያን እውነተኛ የኑሮ ገጽታ ስንመለከት … ‘ተጨቁነናል’ የሚለው እሮሯቸው ግልፅ የወጣ ውሸትና ተራ ጩኸቴን ቀሙኝ እንደሆነ እንረዳለን። … ይህም
… እነዚህ ወገኖች በእኛም ሀገር … ጆሮ የሚሰጣቸው ቢያገኙና የፖለቲካ መዘውሩን ቢቆጣጠሩ … ምን ሊከሰት እንደሚችል የሚጠቁም
ጥሩ ማሳያ ነው:: … ለአብነት በዎል ስትሪት ጆርናል ላይ የተዘገበንና ፤ በግብረ ሰዶማውያንና አፍሪካ አሜሪካውያን (ጥቁሮች)
መካከል የተደረገን … የንፅፅር ዳሰሳ ጥናት ውጤት እንመልከት፦
ቁጥር
|
ጠቋሚዎች
|
ግብረ ሰዶማውያን
|
አፍሪካ አሜሪካውያን/ጥቁሮች/
|
1
|
አማካይ የነፍሰ ወከፍ ገቢ
|
$ 55,430
|
$12166
|
2
|
የኮሌጅ ተመራቂዎች /በፐርሰንት/
|
60%
|
5%
|
3
|
በሹመት/በእልቅና መደብ ላይ/ ያሉ በፐርሰንት/
|
49%
|
1%
|
4
|
ለመዝናናት ባሕር ማዶ ወዳሉ አገሮች የተጓዙ
|
66%
|
1%
|
5
|
የመምረጥ መብት ተነፍጓቸው ነበርን?
|
አልተከለከሉም
|
አዎ
|
6
|
ማሕበራዊ ሽንት ቤቶችን እንዳይጠቀሙ ታግደው ነበርን?
|
አልተከለከሉም
|
አዎ
|
7
|
በንግድ ቤቶችና ምግብ ቤቶች እንዳይገለገሉ ተከልክለው ነበርን?
|
አልተከለከሉም
|
አዎ
|
ከጥናቱ ውጤት በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው … ወንዶችም ይሁኑ ሴት ግብረሰዶማውያን … እንደጥቁሮቹ መኖርያ ያጡ … በየስርቻው መጠለያ ድንኳን ቀልሰው የሚኖሩ … አልያም እርጥባን ፍለጋ በየእርዳታ ድርጅቶች በራፍ ላይ … ረጃጅም ሰልፍ ሰርተው የምናገኛቸው አይደሉም:: … እነዚህ ሰዎች ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ፣ ከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ የሆኑና ፤ ሀብትና ስልጣን የሚያስገኘውን የቅምጥል ኑሮ የሚኖሩ ናቸው። … ብቸኛ አላማቸውም … የሚከተሉትን ተፈጥሯዊ ያልሆነ የአኗኗር ሁኔታና ጾታዊ ተራክቦ … በአብዛሃኛው የሕብረተሰብ ክፍል ላይ ማስረጽና ተቀባይነት እንዲኖረው ማስቻል ነበር … በሌላ አነጋገር … የባሕልና የአመለካከት የበላይነት መቀዳጀት ነበር።
ግብረ ሰዶማውያኑና ሌሎች የተዛባ ጾታዊ ግንኙነት ፈጻሚዎቹ … ይህን ተፈጥሯዊ ያልሆነ ባህልና
አመለካከታቸውን በአብዘሃው ላይ ለማስረጽ ካደረጓቸው የዘመቻ እንቅስቃሴዎች አንዱ በሆነውና ‘ማርች ኦን ዋሽንግተን’ በተሰኘው የ1993ቱ
ሰልፍ ላይ … ቁጥራቸው 300,000 የሚደርሱ ሰዎች የተካፈሉ ሲሆን ፤ … በወቅቱ … የሰልፉ አዘጋጆች የተሳታፊውን ቁጥር ለማብዛት … በግብረ ሰዶማውያኑ የሕትመት ውጤቶች ላይ የሙሉ ገጽ ማስታወቂያዎችን መስራታቸው የሚታወስ ነው:: … ማስታወቂያዎቹን ተከትሎም
… በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ግብረሰዶማውያን እና ሌሎች የተዛባ ጾታዊ ግንኙነት ፈጻሚዎች በዋና ከተማዋ ተገኝተው የነበር ሲሆን ፤ … አብዘሃኛዎቹም ከሰልፉ ጋር ተያይዞ የሚኖረውን
ልቅ የግብረ ስጋ ግንኙነት ተስፋ በማድረግ የመጡ ነበሩ:: …
ሰልፉ … ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት በአለ ሲመት አዘጋጅ ኮሚቴ በተገኘ የገንዘብ
ድጋፍ … ከፊል ወጪው የተሸፈነለት ሲሆን … ዋነኛ አላማው የነበረውም … የሕግ አርቃቂው ተቋም ላይ ጫና በማሳደር … ለጆሮ የሚከብዱት የግብረ ሰዶማውያኑ ጥያቄዎች ምላሽ
እንዲያገኙ ማድረግ ነበር::
የሰልፉ አዘጋጆች … በስራቸው 55 ንዑሳን ጥያቄዎችን ያካተቱ 7 ዓበይት የግብረ ሰዶማውያንና ሌሎች መሰል የተዛባ ጾታዊ ጠባያት ያሏቸው ጎራዎችን ፍላጎት የሚያስተጋቡ ጥያቄዎችን ይዘው የቀረቡ
ሲሆን ፤ … ያቀረቧቸው ጥያቄዎችም የሚከተሉት ነበሩ፦
1. ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያግዱ ማናቸውም አይነት ሕግጋት እንዲሻሩና ሁሉም አይነት ጾታዊ ተራክቦዎች በሕግ የተፈቀዱ እንዲሆኑ (በዚህ ጥያቄ ስር ‘ይስተካከሉ’ ያሏቸውን በርካታ ጉዳዮች
ያካተቱ ሲሆን … ከእነዚህም መካከል)
1.1. ጾታዊ ግንኙነት የሚፈቀድበት የእድሜ ገደብ እንዲቀየር፤
1.2. የአለባበስ ስርአትን የሚገድበው ሕግ ተሸሮ ማንኛውንም አይነት ልብስ የመልበስ
ነጻነት እንዲኖር፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል። … ይኸውም
… እርቃን መሄድና ከሕጻናት ጋር ዝሙት መፈጸምን (pedophilia) የመሰሉ
እኩይ ፍላጎቶቻቸው እንዲፈቀዱላቸው በማሰብ የጠየቁት ለመሆኑ አይጠረጠርም።
2. ግብር ተሰብስቦ ከተገኘው ገቢ ላይ ፤ ለኤድስ ታማሚዎች የሕክምና ወጪ ለመሸፈን
የሚውል በጀት
እንዲያዝ፤ (በዚህ ከላይ ሲታይ ሰብአዊና አግባብ
የሆነ በሚመስለው ጥያቄያቸው ስር ሌሎች አጸያፊ ጉዳዮችን ያካተቱ ሲሆን … ለአብነትም)
2.1. ከግብር የሚገኘው ገቢ ፤ ጾታቸውን የሚቀይሩ ግለሰቦች ለሚያካሂዷቸው ቀዶ ጥገናዎች ወጪ ፈሰስ እንዲደረግ፤
2.2.ከግብር የሚገኘው ገቢ ፤ እጽ ተጠቃሚዎች ለሚያስፈልጋቸው መርፌ መግዣ እንዲውል፤ የሚሉት ይገኙበታል።
3. ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ግለሰቦች መካከል የሚከናወን ጋብቻ በሕግ ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው፤ ልጆችንም በማደጎነት የማሳደግ መብት እንዲኖር፤
4. ግብረሰዶማውያንና ማንኛውንም አይነት ጾታዊ ተራክቦ የሚፈጽሙ ግለሰቦች በት/ት ቤቶች፣
በሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከላት እና በት/ቤት የምክር አገልግሎት ፕሮግራሞች ውስጥ አለገደብ እንዲሰማሩ እንዲፈቀድ፤
5. በማንኛውም የእድሜ ደረጃ ያሉ ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ አቅርቦቶች እና ልቅ የውርጃ አገልግሎቶች እንዲያገኙ፤
6. መንግስት ከግብር ከሚያገኘው ገቢ ፤ … የሴት ግብረ ሰዶማውያን … ሰው ሰራሽ የጽንስ የማሳደር ዘዴ (artificial insemination) ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ የሕክምና ወጪያቸው እንዲሸፈን፤ በተጨማሪም ሃይማኖታዊ መርሆዎችን መሰረት ያደረጉና በግብረ ሰዶማውያን ላይ የሚሰነዘሩ ተቃውሞዎች በሕግ እንዲታገዱ፤
ሁሉም ድርጅቶች
(የግልም ይሁኑ የመንግስት) ግብረ ሰዶማውያን ሰራተኞችን የመቅጠር ግዴታ እንዲኖርባቸው፤
የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን … ይህ … ከመነሻው ጀምሮ ተገቢነት የጎደለውና ቅጥ ያጡ ጥያቄዎች የቀረቡበት … ‘ማርች
ኦን ዋሽንግተን’ የተሰኘ ዘመቻ … የተካሄደው ከ20 አመታት በፊት … እ.ኤ.አ. በ1993 ዓ.ም መሆኑን ተከትሎ … በአንድ ወቅት
እንደተከሰተ ቅጥያ አልባ ግንጥል ታሪካዊ ስህተት አድርገን ልንወስደው እንችል ይሆናል ፤ … እውነታው ግን … ከዚያም በኋላ ቢሆን እነዚህ እኩይ አጀንዳ ያነገቡ ግብረ ሰዶማውያን … እጃቸውን አጣጥፈው አለመቀመጣቸው ነው ፤ … በ2000
ዓ.ም በአሜሪካ ብቻ የ1993ቱን የመሰለ …
ግዙፍ ሰላማዊ ሰልፍን ያደረጉ ሲሆን ፤ … በዚህ ሳይወሰኑም
… በገንዘብ በመደለል ፤ የተለያዩ የፕሮፓጋንዳ መጻሕፍትንና የሕትመት ውጤቶችን በማሰራጨት ፤ እንዲሁም ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ ፤ የመገናኛ ብዙሃንን በመቆጣጠር ፤ … በተቀረውም አለም ጭምር … በተለይም በምዕራቡ አለም ማህበረሰብ ዘንድ … የግብረ ሰዶማውያን አኗኗር … አስነዋሪነቱ ተዘንግቶ … አወንታዊ ፋይዳ እንዳለው ድርጊት … ቅቡል እንዲሆን ከማድረግ አንጻር ብዙ ርቀት ተጉዘዋል:: … እንዲያውም ይህ እንቅስቃሴያቸው … ስም በማጥፋት ፤ በማዋከብና ፤ የአንደበትና የጉልበት ዛቻዎችን በመሰንዘር የታጀበ
ለመሆኑ እማኝ አያሻውም ፤ … ይህን ተከትሎም በውጤቱ … በበርካታ ሀገራት ግብረ ሰዶምን መፈጸም ሕጋዊ የተደረገ ሲሆን ፤ … በግብረ ሰዶማውያን መካከል የሚደረግን ጋብቻ የፈቀዱ ፤ ተቃውሞ
የሚያቀርቡ አካላትንም ለመቅጣት ሕግ ያወጡ ሀገራት ቁጥር ትንሽ አይደለም።
እስኪ አሁን ደግሞ … ግብረ ሰዶማውያኑ እያደረሷቸው ካሉ … ፈርጀ ብዙ አሉታዊ ተጽዕኖዎች መካከል … ለአብነት ያህል የተወሰኑትን አንጻራዊ በሆነ ጥልቀት
ለመመልከት እንሞክር፤
የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም እያደረሱት ያለ የባሕል ወረራ
የውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚጠቁሙት … የአለምን የፖለቲካና የኢኮኖሚ
ስርአት በመቀመር ፤ ቅኝቱን በማስተካከልና ፤ ሚዛኑን በመጠበቅ ረገድ … ወሳኝ ሚና ከሚጫወቱ ልሂቃን መካከል በርካታዎቹ … ግብረ
ሰዶማውያን ናቸው:: … እነዚህ ሃያላን ታዲያ … የግብረ ሰዶማውያን አጀንዳ … በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲስፋፋ … የማይፈነቅሉት
ድንጋይ የለም ፤ … በመዳፋቸው ያለውን ሀብትና ሥልጣን እንኳን ለመጠቀም … ማቅማማት አይታይባቸውም። … ይህንኑ አላማቸውን ከግብ
ለማድረስ ታዲያ … በርካታ መዋእለ ንዋይ ካፈሰሱባቸው መስኮች … ዋነኛውና ተቀዳሚው … የመዝናኛ ኢንዱስትሪው ነው:: … በዚህ
የመዝናኛ ኢንዱስትሪ መስክ … ማንኛውንም ዓይነት የምስል ወድምጽ ውጤት … ክፉና ደጉን ለማይለዩ ሕጻናት ከሚዘጋጁ የካርቶንና አኒሜሽን
ፊልሞች አንስቶ … የአፍላ ወጣቶችንና ጎልማሶችን ቀልብ እስከሚገዙት … ፊልሞች … ሙዚቃዎች … የሙዚቃ ቪዲዮዎች … ቃለ መጠይቆችና
… የማሕበራዊ ቶክ ሾው ዝግጅቶች ድረስ … ብትመለከቱ … ግብረ ገባዊ ፣ ባህላዊና ፤ ሃይማኖታዊ
እሴቶችንና ትምህርቶችን በሚንዱ … ባጠቃላይም … የግብረ ሰዶማውያን አኗኗር ተቀባይነት እንዲያገኝ ብቻ ሳይሆን
… ተመራጭ የሕይወት መንገድ እንዲሆን በሚሰብኩ … ፕሮፖጋንዳዎች የተሞሉ እንደሆኑ … በቀላሉ መረዳት
ትችላላችሁ። … ግብረ ሰዶማዊቷ መምህርት
… ዶ/ር ቨርጂኒያ ዩሪብ … ‘“This is war… As far as I am concerned, there’s no room for
conscientious objectors. We’ve got to be involved in this war. … ያለነው ጦርነት ውስጥ ነው… እስከሚገባኝ ድረስ … በጦርነት ውስጥ ለሕሊና ቦታ የምንሰጥበት አንዳችም ምክንያት የለም ፤ ግብረ ሰዶማውያን ሁላችን … በዚህ ጦርነት ውስጥ ልንሳተፍ ይገባል::’ በማለት በማያወላዳ ሁኔታ እንዳስቀመጠችው ፤ … የግብረ ሰዶማውያኑ ጥምረት … በተቀረው ማሕበረሰብ ላይ ግልጽ የሆነ ጦርነት ያወጀበት ዘመን ላይ እንገኛለን ፤ … መገናኛ ብዙሃኑንም እንደ አንድ መሳሪያው
እየተጠቀመበት ይገኛል። … ከዚህ በመቀጠል … በግብረ ሰዶማውያኑ እየተሰነዘረ ያለው ጥቃት … ምን ያህል የከፋ እንደሆነ መረዳት ይቻል ዘንድ … የተወሰኑ የምስል ወድምፅ ውጤቶችን ለአብነት እናቀርባለን…
[BERT & ERNIE]
ይህ … ‘ሲሰሚ ስትሪት’ (Sesame Street) የተሰኘ ካርቶን ፊልም … በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን … የልጆች ክፍለ ጊዜ … ለረጅም ጊዜ ይተላለፍ የነበረ … ተከታታይ ፕሮግራም ነው።
… ታዲያ በዚህ የካርቶን ፊልም ላይ … ኧርኒ የተሰኘና የወንድ ጾታ የተላበሰ አሻንጉሊት … በርት የተሰኘን የሌላ ወንድ አሻንጉሊት የሰውነት ክፍሎች በጨዋታ አመካኝቶ ሲዳስሰው … በስተመጨረሻም ሀፍረቱን እንደዳሰሰው በአንደበቱ ሲገልጽ ይታያል ፤ … ይህም አድራጎት … መልካምና ክፉውን በማያመዛዝኑት ጨቅላ ሕጻናት አእምሮ … አንዱ የሌላውን የአካል ክፍል መዳሰስ ይችላል የሚል መልእክትን የሚያስተላልፍና … ፍጻሜውም በወንዶች መካከል ሊፈጠሩ ወደሚችሉ አሳፋሪ ግብራት የሚመራ የጭቃ እሾህ መሆኑን ለመገንዘብ አያዳግትም ::
[OPRAH - The Oprah Winfrey Show]
በዚህ ዝነኛ ቶክ ሾው … አንድ … የግብረ ሰዶማዊነት ፍትወት በውስጡ የተጸነሰ … ነገር ግን በሕሊና ወቀሳ ምክንያት
ለመወሰን ግራ የተጋባ ወጣትን አስመልክቶ … ሁለት የፕሮቴስታንት ፓስተሮች … ከዝነኛዋ ኦፕራ ዌንፍሬይ ጋር በሚያደርጉት ውይይት
…. የግብረ ሰዶማዊነትን ኢ-ተፈጥሯዊነት በመካድ … እንሰብከዋለን በሚሉትም መጽሐፍ … በመጽሐፍ ቅዱስ … የተቀመጡትን ትእዛዛት ወደጎን በመተው … አለአንዳች ሀፍረት … ግብረሰዶማዊነት ከአምላክ የተሰጠ ልዩ ስጦታ እንደሆነ ሲናገሩ እናያቸዋለን። … ውድ አንባብያን ወገኖቻችን …. ይህን የተነወረ ጾታዊ
ተራክቦ በተመለከተ … አላማቸው ግራ የሆነ ሰዎች … ብዥብዥታን ለመፍጠር የማይፈነቅሉት ድንጋይ … የማይምሱትም ጉድጓድ የለም
… ለመሆኑ ቅዱሱ መጽሐፍ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የሚያስቀምጠው ነገር ሁለትና ሦስት ትርጉም የሚያስከትል … ያልተገለጠ የሚብራራ
ነውን? … በጭራሽ!! … ለአብነት የተወሰኑትን ጥቅሶች እናስታውሳችሁ …
“ጽራሖሙ ለሰዶም ወለገሞራ በጽሐ ኀቤየ
ወኀጢአቶሙኒ በዝኃት ጥቀ ፤ … የሰዶምና የገሞራ ጩኸት በእኔ
ዘንድ በዛ ፤ ሐጢአታቸውም እጅግ ከበደች”
ዘፍ 18፡-20
“ወምስለ ተባዕት ኢትስክብ ከመ አንስት እስመ ርኩስ ውእቱ ፤ … ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ ፤ ጸያፍ
ነገር ነውና።’’
ዘሌ 18፦22
“ወለእመቦ ዘሰከበ ምስለ ተባዕት ከመ
አንስት ርኩሰ ገብሩ ሞተ ለይሙቱ ክሌኤሆሙ ጊጉያን እሙንቱ ፤ …. ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ
ጸያፍ ነገር አድርገዋል ፤ ፈጽመው ይገደሉ በደለኞች ናቸውና” ዘሌ 20፡-13
“ወከማሁ እደዊሆሙ ኀደጉ አንስቲያሆሙ ወነዱ በፍትወቶሙ ወገብኡ በበይናቲሆሙ
ብእሲ ላዕለ ብእሲ ኀሣሮሙ ገብሩ ወባሕቱ ይረክቡ ፍዳሆሙ ወይገብእ ጌጋዮሙ ዲበ ርሶሙ ወበከመ ኢሐለይዎ ለእግዚአብሔር በልቦሙ ከማሁ እግዚአብሔርኒ ወወሀቦሙ ልበ እበድ ፤ … ስለዚህም እግዚአብሔር
ክፉ መቅሰፍትን አመጣባቸው ፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባቸውን ትተው ለባሕርያቸው የማይገባውን ሰሩ … ወንዶች በወንዶች ላይ
የሚያዋርዳቸውን ነውር ሰሩ ፤ ነገር ግን ፍዳቸውን ያገናሉ ፤ ፍዳቸውም በራሳቸው ይመለሳል ፤ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን
እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሰሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው”
ሮሜ 1፡-26-29
[HOMIES OVER HOES]
ሆሚስ ወቨር ሆ(ር)ስ … በካርቶን ምስል የታጀበ የሙዚቃ ቪዲዮ ሲሆን … በውስጡም ዘፋኝ ራፐሮቹ … ሴቶችን ከክለባቸው እያወጡ ሲወረውሯቸውና … ከነርሱ ጋር ከመሆን ይልቅ ከወንድ ጓደኞቻቸው ጋራ መጫወትን እንደሚመርጡ ሲያውጁ ያሳያል:: … የዘፈኑ ርእስ … የሙዚቃ ቪዲዮውን ዋና መልእክት ግልጽ አድርጎ እንደሚናገረው ፤ … ሆሚስ ወቨር ሆ(ር)ስ ማለት … ከሴት አዳሪዎች ጋር ከምሆን … ከሰፈር
የወንድ ባልንጀሮቼ ጋር መሆን ይሻለኛል እንደማለት ሲሆን
፤ … በቪዲዮው ላይ … ወንዶቹ … እርስ በርሳቸው ደረት ለደረት ሲጋጩ የሚታዩበት ትዕይንት … የወጣቶቹ የእርስበርስ ግንኙነት ከተራ ወዳጅነት የዘለለና … ጾታዊ ግንኙነት ሊባል የሚችል እንደሆነ የሚጠቁም … የእጅ አዙር መልዕክት
ነው ፤ … ከዚህ በተጨማሪም …. አንዱ ወጣት … ዘሩን በሚያፈስ መልኩ … የሻምፓኝ ጠርሙስ እየናጠ ፤ መክደኛውንም ከፍቶ … ከጓደኞቹ ጋር በሻምፓኝ ሲራጭ ይታያል … እንዲህ
ያለው … አስጸያፊና
ባህሪያዊ ያልሆነ … ግበረ ሰዶማዊ ርኩሰት … መልካም ቅብ ተቀብቶ … ለህጻናት ተመልካቾች እንኳ ሳይቀር መቅረቡን ሲመለከቱ …
እየተሰነዘረ ያለው ጥቃት ምን ያህል የገዘፈ እንደሆነ ይረዳሉ። … ሌላው ቀርቶ … ህጻናት ይህን መሰል የሙዚቃ ቪዲዮ … ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመለከቱ … ግራ የመጋባት ስሜት እንደሚስተዋልባቸው … በጊዜ ሂደትም
እንደሚቀበሉትና እንደሚዋሃዳቸው … ደስ ተሰኝተውበትም ከሙዚቃው ጋራ አብረው ወደመጨፈር እንደሚደርሱ … እስከማሳየት የሚደርስ ድፍረት
የሚታይበት የሙዚቃ ቪዲዮ ነው ፤ … ከዚህ በተረፈ … ስለዚህ ቪዲዮ ምን መጨመር ያስፈልጋል ይሆን?
[HOLLYWOOD/MADONNA]
በዚህ የዘፈን ክሊፕ ደግሞ … ማዶና ፣ ክሪስቲና አጉሌራና ብሪትኒ ስፒርስ … በመላው አለም በተላለፈና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
ሳይቀር በታየ … የኤም ቲቪ አመታዊ የሙዚቃ የሽልማት ዝግጅት ላይ … አለአንዳች ሀፍረት እርስ በርስ ሲሳሳሙ ይታያሉ:: … እዚህ
ላይ ታዲያ … እነዚህ … ዝሙትንና ፤ በሴቶች መካከል የሚፈጸምን
ባህሪያዊ ያልሆነ … ጾታዊ ግንኙነት … ሌዝቢያኒዝምን … የሚያሻሽጡ … ታዋቂ ሴት ዘፋኞች … በአብዛሃኞቹ የአገራችን የከተማ ታዳጊዎች
ዘንድ … ከፍተኛ ተወዳጅነት እንዳላቸው ፤ ልብ ይበሉ:: … ታዳጊዎቻችን … እነዚህን የጥፋት ግብረ አበሮች … ከማድነቅና ከመውደድ አልፈው ... የዘፈን ግጥሞቻቸውን ለመሸምደድ ይደክማሉ
፤ በቃላቸውም የሚያንጎራጉሯቸው ዘፈኖች ቁጥር ጥቂት አይደለም … ይህን ተከትሎም … ዘፈኖቹ በውስጣቸው የቋጠሯቸው የርኩሰት አጀንዳዎች
… ቀስ በቀስ በውስጣቸው መስረጹ … የማይቀርና የማይጠረጠር ነው:: … እንዲያውም … ከሚያደርሱት ተፅዕኖ አንጻር ሲታይ … ልጆቻችን
… የእነዚህን ዘፋኞች … የአለባበስ … የጸጉር አሰራር ፤ የአነጋገር ፤ የአረማመድ ፤ ባጠቃላይ የአኗኗር ስርዓት የሚከተሉትን
ያህል … የቅርብ ወላጆቻቸውና ዘመዶቻቸው የሚነግሯቸውን
ግማሹን እንኳን አይከተሉም።
[I KISSED A GIRL/KATY PERRY]
ቀጥሎ የምንሰማውን ዘፈን የተጫወተችው … ካቲ ፔሪ ነች ፤ … በዘፈኗ አዝማች ላይ የሚከተለውን ትለናለች …
“I kissed a girl & I liked it አንዲት ኮረዳን ሳምኳት ይህንን መፈጸሜም ደስ አሰኘኝ፤
Hope my good friend don’ mind it ወዳጄ ቅር እንደማይልህ ተስፋ አደርጋለሁ::”
አዝማቹ በራሱ … ተጨማሪ ማብራሪያ በማያስፈልገው ሁኔታ … በሴቶች መካከል የሚፈጸምን ባህሪያዊ ያልሆነ … ጾታዊ ግንኙነት … የሚደግፍ … አልፎም ደስ የሚያሰኝ ድርጊት እንደሆነ የሚሰብክ ነው።
[SAVED BY THE BELL]
‘ሴቭድ ባይ ዘ ቤል’ … ከ10 ዓመት ግድም በፊት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን … ቲቪ አፍሪካ ከተሰኘ የደቡብ አፍሪካ የቲቪ ኔትወርክ ጋር በመተባበር … በተከታታይ ያቀርበው የነበር
… አስቂኝ የታዳጊዎች የሃይ ስኩል ፊልም ነው:: … በዚህ … ለለጋ ታዳጊ ተመልካቾች ታቅዶ በተዘጋጀ … ተከታታይ ፊልም ላይ … ሁለት ወጣት ወንዶች … በትምህርት ቤታቸው ውስጥ የጀመሩት ገራገር ቀረቤታ … ቀስ በቀስ አድጎ … አብረው አዘውትረው ከመታየት አንስቶ … በይፋ በጓደኞቻቸው ፊት በትምህርት ቤቱ ኮሪደሮች እስከመሳሳምና ፤ ግብረ ሰዶም እስከመፈጸም ሲደርሱ የምንመለከትበትን ትዕይንት እናገኛለን። … አስገራሚ በሆነ ሁኔታ … የፊልሙ አዘጋጆች … የወጣቶቹን ግንኙነት … ተቀባይነት ያለውና ፤ መሳጭ ቃና እንዲላበስ አድርገው ያቀረቡት ሲሆን … ይህም … በቀላሉ … በፊልም ተፅዕኖ ለሚጠቁ ለጋ ተመልካቾች … ሊያደርስ
የሚችለው ጉዳት ሳይታለም የተፈታ ነው::
በትምህርት ዘርፉ ላይ እያሳደሩት ያለ ተፅዕኖ
ግብረ ሰዶማውያኑ … የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም … መጠነ ሰፊ የሆነ
የጥቃት ዘመቻ ውስጥ እንደመገኘታቸው ሁሉ … በትምህርቱ መስክም የተፅዕኗቸውን አሻራ ለማሳረፍ ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም:: የኤች
አይ ቪ ኤድስ ግንዛቤ መፍጠሪያ ፣ የህብረ-ባሕል ማስተዋወቂያ … multi-culturalism
፤ የጉልበት
ትንኮሳ መከላከያ ፤ ወ.ዘ.ተ … የሚሉ ክፍለ ጊዜያትንና መሰል ዝግጅቶችን
እንደጭምብል በመጠቀም … በየትምህርት ቤቱ በትምህርት ገበታ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች … ለአጸደ ሕጻናት ጨቅላዎች ሳይቀር ጸያፍ የሆነ ምግባራቶቻቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ:: … በአሜሪካ ብቻ እንኳን
… የግብረ ሰዶማውያንን ኢ-ባህሪያዊ ጠባይ .. መልካምና ተቀባይነት ያለው አድርገው የሚያቀርቡት … ‘ሄተር ሐዝ ቱ ማሚስ’ እና
‘ዳዲስ ሩሜት’ … የተሰኙ መጻሕፍት .. በበርካታ የግልና የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ቤተ መጻሕፍት ውስጥ … ወላጆች ባላወቁበት ሁኔታ
የትምህርት ማጣቀሻ መጻሕፍት በመሆን ግልጋሎት ላይ መዋል ከጀመሩ ዋል አደር ብሏል:: … በተጨማሪም … ‘ዘ ፕሌይ ቡክ ፎር ኪድስ
አባውት ሴክስ’ የተሰኘና ፤ አላማውን ግብረ ስጋ ግንኙነትን ለሕጻናት ማስተዋወቅ ያደረገ መጽሐፍ … በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
የሚማሩ ሕጻናትና ተዳጊዎች በተለያዩ መንገዶች እንዲያገኙት እየተደረገ ሲሆን … በውስጥ ገጾቹም … ዘርን የማፍሰሻ ዘዴዎች … ማስተርቤሽን
ሜትድስ እና ሌሎች መሰል አስጸያፊ የዝሙት ግብራት የሚፈጸሙባቸውን መንገዶች
በዝርዝር የሚያስረዱ በርካታ ጽሑፎች ተካተውበታል::
‘‘we shall sodomize your sons, emblems of your feeble
masculinity; we shall seduce them in your schools, in your dormitories, in your
gymnasiums, in your locker rooms, in your sports arenas, in your seminaries, in
your youth groups. …የደካማ ወንዳወንድነታችሁ መገለጫ የሆኑ ወንዶች ልጆቻችሁን በግብረ ሰዶም እናጠቃቸዋለን ፤
በትምህረት ቤቶቻችሁ ፣ በዶርሚተሪዎቻችሁ ፣ በጂምናዝየም አዳራሾቻችሁ ፣ በስፖርት ማሳያ ስፍራዎቻችሁ ፣ በካህናት ማሰልጠኛዎቻችሁና
በወጣት ማኅበራቶቻችሁ ሳይቀር … ፍትወታችንን እንፈጽምባቸዋለን …’ Michael Swift, Gay
Community News, Feburuary 15-21
1985
ከዚህ የማን አለብኝነት መገለጫ የሆነ ንግግር እንደምንረዳው
… ከአጠቃላይ ማሕበረሰቡ አንጻር ፤ እዚህ ግባ የሚባል ቁጥር የሌላቸው … እነዚህ የጥፋት ሰራዊት አባላት … አብዝሃውን ወደ ተያያዙት
የርኩሰት ጎዳና ለመክተት ምን ያሕል ርቀት እየተጓዙ እንደሆነ ነው::
ፕሮጀክት ቴን … እ.ኤ.አ በ1984 ዓ.ም በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ የተቋቋመ የግብረ
ሰዶማውያን ማስፋፊያ ማሕበር ነው:: … ማኅበሩ … ግብረ ሰዶማዊቷ የማኅበሩ መስራች …መምህርት ዶ/ር ቨርጂኒያ ዩሪብ በግልፅ እንዳስቀመጠችው
… ‘ከአጸደ ሕጻናት አንስቶ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች የሚገኙ ተማሪዎች … የግብረ ሰዶማውያንን ጾታዊ ጠባይ ተፈጥሯዊ እና ተመራጭ
እንደሆነ እንዲቀበሉ ግንዛቤ መፍጠር’ን ተቀዳሚ አላማው አድርጎ የሚንቀሳቀስ ማኅበር ነው:: … ዶ/ር ዩሪብ … አስገራሚ በሆነ
ሁኔታ … ናሽናል ኢዱኬሽን አሶሴሽን ከተሰኘ ተቋም … ‘ለሰዎች መብት መጠበቅ ፤ በታየ አፍላቂ የአመራር ችሎታ’ ዘርፍ … ሽልማትን
የወሰደች ሲሆን … በሽልማቱ ወቅት ያደረገችው ንግግር ፤ የወገኖቿን የወደፊት ዕቅድ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነበር። … ዶር ዩሪብ
እንዲህ ነበር ያለችው …
‘“the state courts must be used to force the school districts to
disseminate accurate information about homosexuality. They need to hear this;
kids need to hear the latest scientific information on the subject of
homosexuality and that’s something that all kids need to hear, not just gay and
lesbian kids. Starting from kindergarten, again and working its way all the way
through high school. This idea of talking about it one time in high school…
well we know that doesn’t work. We need to start tackling this at the very
early ages. … የክልል ፍርድ ቤቶችን ተጠቅመን ፤ የወረዳ ትምህርት ተቋማት ስለ ግብረ ሰዶማውያን አኗኗር
ወቅታዊ መረጃዎችን ለተማሪዎቻቸው እንዲያሰራጩ ልናስገድዳቸው ይገባል ፤ ሕጻናት ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ዘመኑ የደረሰበትን ወቅታዊና
ሳይንሳዊ መረጃ ሊያውቁ ይገባል ፤ ይህ ደግሞ ግብረ ሰዶማውያን ሕጻናት ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች የዕድሜ እኩዮቻቸው ሁሉ ሊያውቁት የሚገባ
መረጃ ነው ፤ ከአጸደ ሕጻናት አንስቶ በየደረጃው እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እስኪደርሱ … አመለካከታቸው ላይ ተጠንክሮ ሊሰራባቸው
ይገባል:: … ሁለተኛ ደረጃ
ሲደርሱ አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሰሙት የማድረጉ አካሄድ
… እንደማይሰራ ተገንዝበነዋል ፤ እጅግ
ዝቅተኛ የእድሜ ደረጃ ሳሉ አንስተን ‘ይህንን’ የተዛባ አመለካከተ ልንፋለመው ይገባል::’
እነዚህ ግብረ ሰዶማውያን … በትምህርቱ መስክ
እያሳደሩ ያሉትን ፈርጀ ብዙ ተፅዕኖ በውል መረዳት ይቻለን ዘንድ … እግረ መንገድም በአሜሪካ የትምህርት ስርዓት ላይ ተፅዕኗቸው ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘ ለመገንዘብ ይረዳን ዘንድ … በሜይ 2009 ዓ.ም ሳን ፍራንሲስኮ ውስጥ በአላሜዳ ካውንቲ ወረዳ በሚገኝ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ … ሕጻናትን ከጉልበት ትንኮሳ ራሳቸውን እንዲከላከሉ ለማስተማር በሚል ሰበብ የግብረ ሰዶም አጀንዳ በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ እንዴት ሊካተት እንደበቃ
… የፎክስ የዜና
ማሰራጫ የዘገበውን ዘገባ
ቀጥለን እንመልከት፦
[GAY
AGENDA IN SCHOOLS]
በዘገባው ላይ በግልጽ እንደምንመለከተው፦
·
የትምህርት ቤቱ የአስተዳደር ቦርድ … የግብረ ሰዶማውያኑን አጀንዳ በስርዓተ ትምህርታቸው ውስጥ እንዲካተት ለማድረግ … የትምህርት ቤቱን በጀት ፈሰስ አድርጎ ለስብሰባ የሚያስፈልገውን ወጪ ከመሸፈን ጀምሮ … ወላጆችን ጠርቶ እስከ መሰብሰብና ፤ ድምጹን ሰጥቶ አጀንዳውን እስከ ማጽደቅ የደረሰ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
·
የግብረ ሰዶማውያኑ ጥምረት አጀንዳቸውን የሚደግፍ ትምህርት
በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ
እንዲካተት ለማድረግ ይቻሉ እንጅ ፤ በልጆቻችን ላይ እየደረሰ ነው የሚሉትን ትንኮሳና መገለል የሚደግፍ መስረጃ … በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ጥናቶች ላይ አልተገኘም።
·
በዚህ ውሳኔ መሰረት የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ሕጻናት … የግብረ ሰዶማውያንን አኗኗር ተመራጭ አድርገው የሚያቀርቡ መጻህፍትን … ለአብነትም ሁለት ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ፔንጊዩኖች ሕጻን ፔንጊዩን ሲያሳድጉ የሚተርከውን ‘ታንጎ ሜክስ ስሪ’ … የግብረ ሰዶማውያን ቤተሰብ ኑሮ መልካምና
ተመራጭ አድርጎ የሚያሳየውን ‘ዛት ኢዝ ኤ ፋሚሊ’ የተሰኙ መጻሕፍት … በንባብ ክፍለ ጊዜያቸው እንዲያነቡ ይገደዳሉ።
·
ከዚህ ጋር በተያያዘ … በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ 11 ክፍላተ ሀገራት … የጸረ ትንኮሳ ትምህርትን በስርዓተ ትምህርታቸው ውስጥ
እንዲካተት ያደረጉ ሲሆን … በዚህ ትምህርት ውስጥም ከ2ኛ ክፍል ጨቅላዎች አንስቶ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ድረስ ስለጾታዊ የሩካቤ ፍላጎትና ስለ ተመሳሳይ ጾታ ሩካቤ ተፈጥሯዊነት እንዲማሩ ይደረጋል::
ግብረ ሰዶማውያን በኢትዮጵያ
በሀገራችን ኢትዮጵያ ስለሚገኙ ግብረ ሰዶማውያንና ሕቡዕ ስለሆነው እንቅስቃሴያቸው ጥናት ለማድረግ ተጨባጭና የጠራ መረጃ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው:: … ለዚህም ዋነኛው ምክንያት … ነባራዊውና ለቀደሙ መልካም እሴቶች ቀናኢ የሆነው ሃይማኖታዊና ባህላዊ ዳራ ፈፅሞ ባለመጥፋቱ … በግብረ ሰዶማውያኑም ተፅዕኖ ስር ሙሉ በሙሉ ባለመውደቁ … እነዚህ የጥፋት ሀይሎች እኩይ የሆነ ግብራቸውን በይፋ ለመፈጸም ባለመድፈራቸውና … አመቺ ሁኔታዎች ተፈጥረው
አንገታቸውን ካደቡበት ብቅ እስኪያደርጉ ድረስ … ከሕብረተሰቡ አይን ተሸሽገው
ምስጢራዊ በሆኑ የግለሰብ ቤቶችና እነርሱው ብቻ በሚያውቋቸው የምሽት ክበቦችና
መሸታ ቤቶች ለመፈጸም በመገደዳቸው ነው:: … ይህም ሆኖ ግን ድምጻቸውን አጥፍተው … ውስጥ ለውስጥ ግብረ ሰዶማዊነትን በማስፋፋት የበላይነቱን ለመያዝ የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች አልጠፉም:: … በተለይ በከተሞች አካባቢ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግብረሰዶማውያን
መገኘታቸውን ይፋዊ ያልሆኑ የዳሰሳ ጥናቶች ያመለክታሉ::
የኢንተርኔትና
የዲሽ ተጠቃሚዎች በከተማዎች አካባቢ
መበራከት
… የግብረ ሰዶማውያን የኑሮ ዘይቤ የነገሰባቸው የምዕራብ አለም ሀገራት የባህል ተፅዕኖ በሕብረተሰቡ ዘንድ እንዲሰርጽ ከማድረግ አንጻር … ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል:: … በተጨማሪ … ወላጅ አልባ ሕጻናትን በማሳደግና መሰል በሆኑ የግብረ ሰናይ ስራዎች በተሰማሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አካባቢ የሚፈጸሙ ሕጻናትን የመድፈር ተግባራት
ግብረ ሰዶማዊነትን ለማስፋፋት የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል::
በከተሞቻችን አካባቢ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግብረ ሰዶማውያን መገኘታቸውን ተከትሎ … የግብረ ሰዶማውያን መብት አቀንቃኝ የሆኑ ማሕበራት … የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ለመሳብና የመብትና የእኩልነት
ጥያቄን ለማንሳት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ሲሆን ፤ ለአብነትም እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ … በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብረ ሰዶማውያን ፊርማ አሰባስበው የእኩልነት
መብትን ለመጠየቅ የሞከሩበትን … በጊዜውም ማመልከቻቸው ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ሳይደርስ ሊጨናገፍ የበቃበትን አጋጣሚ ማውሳት ይቻላል:: …
በዛኑ አመት … በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ይፋዊ ያልሆነ የግብረ ሰዶማውያን የጋብቻ ስነ ስርዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል … በሁለት ኢትዮጵያውያን ወንዶች መካከል መፈጸሙም የሚጠቀስ ነው:: …
ይህንና ይህን የመሰሉ አወዛጋቢ የግብረ
ሰዶማውያን ይፋዊ ያልሆኑ
ሕቡዕ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ብሎም ለማስቆም በማሰብ … በሕዳር 2008 ዓ.ም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፣ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና ፤ የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ … የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስብሰባ ተቀምጠው የነበረ ሲሆን ፤ የእኩይ ግብራት ሁሉ ቁንጮ በማለት የጠሩትን የግብረ ሰዶማውያኑን
እንቅስቃሴ አስመልክቶ የአንድነት አቋምና የጋራ መግለጫ አውጥተዋል:: … በዚህ የጋራ መግለጫቸው ላይ ፤ የሃይማኖት መሪዎቹ … ለሀገሪቱ ፓርላማ የሚከተሉትን
አበይት ጥያቄዎች አቅርበዋል።
· የተመሳሳይ ጾታ ተዋስቦ ፤ የትውልድን ቀጣይነት የሚጻረርና ሕገ መንግስቱ እውቅና የሚሰጣቸውን የቤተሰብ እሴቶች የሚንድ ፤ እኩይ ግብር በመሆኑ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያግድ ሕግ በሕገ መንግስቱ
ውስጥ እንዲካተት፤
· በግብረ ሰዶም ለተጠቁ ግለሰቦች ፤ የስነ ልቦና እርዳታና የምክር አገልግሎት የሚሰጡ የማገገሚያ ማዕከላት እንዲቋቋሙ፤
· ግብረ ሰዶማዊነትንና ሌሎች አስነዋሪ
ድርጊቶችን በማዛመት ፤ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ የሚገኙት የኢንተርኔት ድረ ገጾች
ሳንሱር እንዲደረጉ፤ (ማሞ፣ 2009፣ ገጽ 28)
የሚሉት ናቸው፡፡
ያም ሆኖ … ይህ … የሃይማኖት መሪዎቹ መግለጫ ፤ … በታኅሳስ 2009 ዓ.ም ፤ … በከፊል ይፋዊ የሆነ … የመጀመሪያው የግብረ ሰዶማውያን ማኅበራዊ መድረክ … በአዲስ አበባ ከተማ … እንዳይዘጋጅ የሚከላከል
ሳይሆን ቀርቷል።
ይፋዊ ያልሆኑ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአዲስ አበባ ብቻ ቢያንስ 50 000 የሚደርሱ ፤ ጎዳና ላይ ገላቸውን በመሸጥ
የሚተዳደሩ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስይ 5000 የሚሆኑት ግብረ ሰዶማውያን ወንደኛ አዳሪዎች ናቸው ፤ ወንደኛ አዳሪዎቹ
ቱሪስቶች በሚያዘወትሯቸው ኢንተርናሽናል ሆቴሎች ዙሪያ ባሉ ጎዳናዎች ፤ ታዋቂ ናይት ክለቦች ፤ የማሳዥና የቤተሰብ መታጠቢያ ማዕከላት
አዘውትረው የሚታዩባቸውና ከደምበኞቻቸው ጋር የሚቃጠሩባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡
ግብረ ሰዶማዊነት … በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያደርገውን መስፋፋት ለመግታት ፤ የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ ከሚያደርጉት ምክንያቶች ዋነኛው ፤ ለጉዳዩ የሚሰጠው ዝቅተኛ ግምት ነው።
… የሃይማኖት መሪዎችና ሌሎች ተቆርቋሪ አካላት ፤ ችግሩን ሀገር በቀልና ፤ በአንዳንድ አእምሯቸውን ያጡ ፤ ቅንጡ ግለሰቦች የሚፈጸም
ተራ ጋጠወጥነት አድርገው ስለሚመለከቱት መዘናጋት ይስተዋልባቸዋል ፤ እውነታው ግን … ግብረ ሰዶማዊነት … ፈጣሪን ከማክበርና ከመፍራት ወጥተው ፤ ሊገዳደሩት
በሚሞክሩ ምዕራባውያን ፤ በተለይም አዋቂና ታዋቂ በሚባሉት ግለሰቦች
የሚፈጸም ፤ በአለም አቀፍ ደረጃ ሕቡዕ የሆነ መረቡን ዘርግቶ ፤ በተደራጀ መልኩ መስፋፋትን የሚያደርግ ፤ ተፈጥሯዊ ያልሆነ አስነዋሪ
ድርጊት መሆኑ ነው።
ባጠቃላይ ባለፉት አስርት አመታት የተካሄዱትን የጌይ ፕራይድ እንቅስቃሴዎችን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት ግብረ ሰዶማዊነትንና
ሌሎች መሰል የተመሳሳይ ጾታ ተራክቦን መፍቀድ ከዴሞክራሲና ከመብት ጥያቄዎች ጋር በስፋት በመያያዝ ላይ ናቸው፡፡ አስቀድሞ በግብረ
ሰዶማውያን ላይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ የሚታወቁ ሀገራት ሳይቀሩ የዜጎችን መብት ለማክበርና የሰብዓዊ መብትን ለማስጠበቅ በሚል
አመክንዮ አቋማቸውን በመቀየር ላይ ናቸው፡፡
የተባበሩት መንግስታትን ፣ የአለም ባንክን ፣
የአለም ገንዘብ ድርጅትን ፣ የኒዎርኩ ዎልስትሪትን ፣ የአለም ጤና ድርጅትን ፣ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶን
፤ … በመሳሰሉ ፤ አለም አቀፍ
የፖለቲካና የኢኮኖሚ መድረኮች ውስጥ ፤ ቁልፍ የስልጣን መንበሮችን ከተቆናጠጡት ፤ ተፅዕኖ ፈጣሪ ልሂቃን መሃል ፤ … በርካቶቹ … ግብረ ሰዶማውያን መሆናቸውን ተከትሎም ፤ በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ
ጽኑ እርምጃን በመውሰድ የሚታወቁ ሀገራት ፤ የሕግ ማሻሻያ እንዲያደርጉ ፤ አልፎ ተርፎም ለግብረ ሰዶማውያኑ እውቅናና የሕግ ከለላ
እንዲሰጡ ፤ ተፅዕኖ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ (በቅርቡ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የግብረሰዶማውያንን መብት ለማያከብሩና
ለማያስከብሩ የአፍሪካ ሀገራት የሚደረግን እርዳታ እንደሚያግድ ማስጠንቀቂያ ብጤ ማስተላለፉን ልብ ይሏል ፤ ሰሞኑንም የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ የጸረ
ግብረሰዶም ህግ መፈረማቸውን ተከትሎ የተከሰተው እንኪያስላንቲያ … የዚሁ ተጽዕኖ አንዱ ማሳያ
ነው፡፡)
ልብ ያለው ልብ ይበል!! ይቆየን...
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።
No comments:
Post a Comment