Pages

Friday, July 19, 2013

ያልተመለሰው ጥያቄ፡ የጃዋር መሃመድ ‘በአክሱም መስጊድ ይሰራ’ ጥያቄ በኦርቶዶክሱ ማኅበረሰብ ላይ ያልተመለሰውን ጥያቄ ሲጎትት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ያልተመለሰው ጥያቄ፡ የጃዋር መሃመድ ‘በአክሱም መስጊድ ይሰራ’ ጥያቄ በኦርቶዶክሱ ማኅበረሰብ ላይ ያልተመለሰውን ጥያቄ ሲጎትት 


A new reality has dawned upon us Christians. The French revolution has introduced a new type of government previously unheard of during the middle ages. During the medieval world, monarchy and Christianity were inseparable part of the same whole. Monarchs were considered divinely instituted with the blessing of the church. The post-French revolution world, however, taking as a prototype the atheistic and secular revolution of France, waged war on religion and sought, if possible, to eradicate if not sideline it to an impotent status. Consequently, the church and state as distinctly separate entities came to the fore.

ይህ … የቤተክርስቲያንና የመንግስት ፍጹም የመለያየት ሀሳብ(እውነት) … በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ዘንድ … በተለያየ አተያይ የታየ የነበረ ሲሆን ፤ የምዕራቡ አለም ክርስቲያኖች … ሀገራቶቻቸው የተገነቡባቸውን ክርስቲያናዊ መሠረቶች የሚያፈልስ … ሃይማኖታዊ እሴቶችን የሚያጠፋና ፤ መንፈሳዊ ልዕልናቸውን የማያስጠብቅ አፍራሽ ክስተት አድርገው ሲመለከቱት … ለብዙ ምዕተ ዓመታት … በሙስሊም መንግስታት አገዛዝ ስር የነበሩት የምስራቁ ዓለም መሰሎቻቸው ባንጻሩ ግን … በሃይማኖታቸው ምክንያት … በገዥዎቻቸው ይደርስባቸው ከነበረ ጭቆና ፤ ይጣልባቸው ከነበረ ከፍተኛ ግብር ፤ … ፤ እንዲሁም ይህን ከመሰል የግፍ አገዛዝ ሁሉ የተነሳ … ክስተቱን (የመንግስትንና የቤተክርስቲያንን ፍጹም መለያየት) ፤ … አንዳች እኩልነትንና የሃይማኖት ነጻነትን ይዞላቸው እንደሚመጣ … ጥሩ አጋጣሚ/ተስፋ … እጃቸውን ዘርግተው ነበር የተቀበሉት። It is with this hope in mind that Coptic Christians welcomed Napoleonic conquest of Egypt and British colonial rule; and Turkish Christians for the secularization of the Turkish government following the fall of the Ottoman Empire.

In Ethiopia, however, the situation has been very similar to the Holy (Christian) Roman Empire. Both civil and religious affairs were heavily intertwined and up until recently (& for those who still choose to shroud themselves with the dream of the Mighty Ethiopia), for the average Christian, the word ‘Ethiopia’ is synonymous with the term ‘Christian’. The monarchs themselves, although they frequently quarreled with the church, have often received strong education in clerical and theological training, many of those who put on the crown having been priests themselves. ለዚህም ሀቅ እንደ ማስረጃ  … ኢትዮጵያዊው ንጉስ … ንጉስ አጼ ካሌብ ፤ የየመን ክርስቲያኖች ጭቆናና እንግልት ግድ ብሎት ወደ የመን መዝመቱን ፤ ንጉስ ገላውዲዎስ ከኢየሱሳውያኑ ጋራ በተደረጉ ሃይማኖታዊ ክርክሮች/ጉባኤዎች ፤ ዋና ተከራካሪ ሆኖ መሳተፉን ፤ ንጉስ አጼ ሚኒሊክ ሀገራዊ ወራሪ ፤ ሀገር በወረረ ጊዜ የእግዚአብሔርን ታቦት ከፊት አስቀድመው ጦርነት መዝመታቸውን ፤ … ወ.ዘ.ተ. ማንሳት ይቻላል። (The Jesuits, who were learned men, were betrayed into long theological disputes. The abuna and the native clergy could not stand up against them, but the king (ንጉስ ገላውዲዎስ), as they freely admit in their own dispatches, often drove Oviedo into a corner.) – A.H.M. Jones, E. Monroe, (1935). The History of Abyssinia. The Clarendon Press, New York.

The seeds of the divorce between church and state were first sown in 1974 when the Derg regime came to power, where the state became officially atheistic and the church was frowned upon even to the point of castigation (Death of Abuna Teklahaimanot; closing of the Trinity Church; burning and closing of several churches; appointing of pro-government patriarch). However, the church community as a whole and the individual Christian, more or less, were able to tolerate the ‘new reality’ because of the hostile attitude of the Derg towards ‘alien’ religions and because compared to other religious organizations, the church was relatively favored (for being ‘አገር በቀል’). Moreover, the church was content with the pan-nationalistic agenda (as contrasted to the ethnic-based reorganization of the EPRDF era) of the Derg believing deep down that as long as the pro-Ethiopian agenda is carried forward, she (the church) would have a stake to claim (for Ethiopian nationalism is ultimately founded on the church).

ኢህአዴግ በበኩሉ … ይህንን … የመንግስትና የቤተክርስቲያን ፍቺ/መለያየት … አንድ እርምጃ ወደፊት አራመደው። … አዲሱ መንግስት … የመለያየቱን ጽንሰ ሃሳብ … የህገ መንግስቱ መሰረታዊ ይዘት ከማድረግ ባለፈ … ሁሉም ሃይማኖቶች በህግ ፊት እኩል መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን/እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። … አብያተ ክርስቲያናትን መዝጋት ፤ የቤተክርስቲያን አባቶችን ማንገላታት/ማሰቃየት ፤ እምነት የለሽነትን ማወጅ ፤ እነዚህና መሰል ጥቃቶች ማድረስ አንድ ነገር ነው … (እጅጉን የሚያም ፈተና ቢሆንም … የቅድስት ቤተክርስቲያንና የልጆቿ ጫንቃ ሊሸከመው የማይችለው ተግዳሮት ግን አይደለም … ለአሁኗ ኢትዮጵያ የዋለችውን ውለታ የሚዘነጋ … ለሀገሪቱ የታሪክና የማንነት መሰረት መሆኗን አጥፍቶ ያልነበረ አዲስ ታሪክ የሚጽፍ አይደለምና) … ነገር ግን … በሺህ በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ አምጣ በወለደችው ማንነት ላይ ተቁሞ … እንዲያም ሲል ይህንን ማንነት የኩራት ምንጭ እያደረጉ (እንግዳ ተቀባይ ፤ ሀገሩን ወዳድ ፤ ባህል ወጉን ጠባቂ ፤ …ወ.ዘ.ተ ተብሎ እንዲጠሩ እየፈለጉ) … የዚህን ማንነት ምንጭ ቆርጦ ለመጣል/እውቅና ለመንፈግ የሚደረግ ሩጫ ግን ፍጹም ሌላ ነገር ነው … ዋጋውም እንዲህ በቀላሉ የሚተመን አይሆንም። (በቅርቡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ተቋማትን ለመመዝገብ ረቂቅ መመሪያ ማውጣቱን ልብ ይሏል)



Nevertheless, the disorganized, demoralized and factionalized Orthodox believers also learned to bear the new ideology and, though it is now more blatant to their awareness, they chose not to wake up from the dream (of the once glorious and, more importantly, Christian Ethiopia), not only because it is a beautiful dream, but also the reality awaiting them was dreadful.

Now, however, when issues like the Waldiba Affair, (several other scenarios/incidents jeopardizing the church’s integrity and the current controversy over Muslims demanding to build Mosque in Axum, the spiritual capital of the Ethiopian Orthodox Church), come to the fore, the otherwise dreaming/drowsy Christian is inevitably confronted to the inescapable reality of the death of Christian Ethiopia.

በግልፅ እንደሚስተዋለው … አብዝሃው የክርስቲያን ማኅበረሰብ … አንገብጋቢ በሆኑ ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ … ተናጠላዊም ይሁን ቡድናዊ አቋም (ውሳኔ) ለመያዝ/ለመውሰድ … ግልፅ የሆነ ቁርጠኝት/ጥብዓት ይጎድለዋል። … ይህንንም ሩቅ መጓዝ ሳያስፈልግ … በጅማና ነገሌ በደረሱ የክርስቲያን ወገኖቹ እልቂት … በአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት መነሳት … እንዲሁም የቅዱሳን በዓት በሆነው የዋልድባ ገዳም መደፈር … ላይ ያሳየውን … ዘላቂነት የሌለው … ወቅታዊ መረበሽ/ድንጋጤ ወለድ ምላሹን ፤ በጊዜ ሂደትም ለጉዳዮቹ የማያዳግም መፍትሄ ሳያስቀምጥ/ሳይሰጥ ወደ ቀደመ ማንቀላፋቱ መመለሱን በማንሳት ማረጋገጥ ይቻላል። … አሁን አሁን ግን ይህንን የማንቀላፋት ዘመን ማብቃት ግድ የሚሉ አስገዳጅ ሁነቶች በፊታችን እየተጋረጡ ይገኛሉ … ከ40 እና 50 ዓመታት በፊት ልንመልሰው ይገባን የነበረው ጥያቄ … ክብደቱን ጨምሮ ጊዜ አይሰጤ ሆኖ ቀርቧል … እኛ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችም በመንታ መንገድ ላይ ቆመናል … ሁለቱ መንታ መንገዶች ጠቅለል ባለ መልኩ ሲቀመጡ የሚከተለውን ይመስላሉ፦

a.       To pursue the ‘never say die’ attitude over the claim that ‘the Christian Ethiopian Empire is long gone’ and with the zeal typical of our forefathers strive through all available means to reawaken/revitalize the Christian Ethiopian Spirit. (እየኖርንባት ያለችውን ኢትዮጵያ … ልባችን ውስጥ ባለችው ኢትዮጵያ የመተካት የሕይወት ምርጫ … የ40 እና 50 ዓመቱን ስህተት የማስተካከል ግብግብ … መሰረቷን ኦርቶዶክሳዊ ማንነት ላይ ያደረገችው ኢትዮጵያ ፤ ሌላ ባዕድና እምነት የለሽ ማንነትን ገንዘብ እንዳታደርግ የመታደግ ፈተና … የምናስባትን ክርስቲያናዊት ኢትዮጵያ ክርስቲያናዊ መሠረቶች የማጠባበቅ ምርጫ …)
b.      To embrace the separation of church and state with all its implicit consequences; the subsequent death of  Ethiopia as a Christian state and accordingly, learn to live under the new circumstances inevitably leading to the way of life the catacomb Christians used to lead. (ነፍሳቸውን በገነት ያኑረውና ፤ ግብጻዊው መንፈሳዊ መሪ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ‘ግብፅ ያለችው በልባችን ነው ፤ በልባችን ያለችውን ግብፅ ግን በዓይናችን የምናያት ለማድረግ ሁኔታዎች አይፈቅዱም’ ይሉ እንደነበረው … እዚህና እዚያ በሚከሰቱ (ልባችን ውስጥ ካለችው ክርስቲያናዊት ኢትዮጵያ ጋራ በማይጣጣሙ) ክስተቶች ፤ አሁንም አሁንም መደነቁን ፤ ‘ምን ሲደረግ? … እንዴት ተደርጎ?’ እያሉ መደንፋትና ማቅራራቱን ትተን … ነባራዊዋን ኢትዮጵያ ተቀብሎ … በአባቶቻችን ደምና አጥንት የቆየውን ክርስቲያናዊ ውርስ/ርስት/ዕሴት አንገት ደፍቶ በማስረከብ ከመሬት በታች መኖር …

A significant number of Christians go by the former alternative, i.e. are still reluctant, to say the least, to part ways with the former Christian Ethiopia. When not even the generation that had lived believing and dying for such religious ideals has not yet passed away, it is indeed difficult for them to accept this new brand of Ethiopia, although it has been a long time since the ink on the constitution has dried. One still sees prayers and mottos such as እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አስራት ሀገርሽን - ኢትዮጵያን ጠብቂያት’ posted on taxies and busses which reflects their inherent feelings about the Ethiopia that is in their hearts.

በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት ክብረ በዓል ወቅት ፤ አንድ ጌታ ፤ አንድ ሃይማኖት ፤ አንድ ጥምቀትኤፌ 4፦5 የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በልብሶቻቸው ላይ ጽፈው አደባባይ የወጡ ወጣቶችን አስመልክቶ … የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን ያላግባብ የ ‘መሰል ጽንፈኝነቶች ጠንሳሽ’ አድርገው በአደባባይ ሲከሱትና … በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው … ግልጽ በሆነ አማርኛ … ‘ክርስቲያናዊት ኢትዮጵያ የምትባል ነገር የለችም’ …  ሲሉን እንኳ … ሊሰማ በሚችልና ትርጉም ባለው መልኩ የቀረበ የመቃወምም ይሁን … በልባችን ከምናምነው እምነት ጋራ ፈጽሞ የማይስማማውን የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ሀሳብ በይፋ የመቀበል ተነሳሽነት አላሳየንም።


Writers like Mesfin Negash, on the other hand, seem to have accepted the latter perspective. They seem to have made their peace with the Athiest (and to some extent hostile to the traditional Ethiopian Christian mindset) Ethiopia which refuses to give any credit to any kind of god, let alone to bow down to previous church privileges. They thus seem to have no problem for the church to have to let go of her long cherished strong holds and religious holy sites simply because the times have changed and consequently, she has to readjust with the changing circumstances. Surely they must realize how the holy fathers of the previous era would have reacted if they had heard that a mosque was going to be built on Axum. But, we suppose people falling into this category feel that these are the things the church must endure in order to maintain her status under the new circumstances. But if they are ok with the Muslims striving to achieve their constitutional rights to the fullest, then they should be reminded that when the church to which they belong to is stripped of her rights, it is their duty to stand up on her behalf and see to it that her rights are, in turn, fulfilled to the fullest.

Unfortunately prominent and influential Christians, who do not hesitate to associate themselves with the new image of Ethiopia are doing nothing about the injustice their church is enduring and yet we observe them nodding in approval when other bodies are striving to get their rights achieved at the cost of the orthodox church.

The uncertainty over which road to take is exhibited by the recent ‘grip of indecision’ shown by the Christian faithful in general and Mahibere Kidusan (who embodies the spirit of both reform and adherence to tradition of the holy fathers) in particular. While the Christian faithful looked in vain for guidance and support, to pursue their quest for justice on the Waldiba affair, the society, unfortunately, poured cold water over the efforts Christians were trying to make. (look at -Waldiba’s Crisis & a glimpse at MK’s Report)

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን … ሁለተኛውን አማራጭ በመመርጥ ለመጓዝ የምትፈቅድ ከሆነ … ከሁሉ በፊት ከመንግስት ጋራ የተሳሰረችበትን ማንኛውንም ማሰሪያ በጣጥሳ ልትጥል ይገባታል። … በመቀጠልም በምርጫዋ ምክንያት የሚሆነውን … በሀገሪቱ ከነበራት ታሪካዊ ፤ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች የተነሳ ፤ አግኝታቸው የነበሩትንና የእርሷና የእርሷ ብቻ የሆኑ ጥቅማ ጥቅሞችን ከማጣት እና እርሷው ባቀናችው ምድር ላይ እንደ ባዕድ በተፅዕኖ ውስጥ ከመኖር ጀምሮ … - ከንጉስ ቆስጦንጢኖስ ዘመን አስቀድሞ ክርስቲያኖች ይኖሩት እንደነበሩት ያለ … በብዙ ግፍና ጭቆና መሃል የመኖር ግዴታ ውስጥ እስከመግባት ልትደርስ የመቻሏን ሀቅ በጸጋ ልትቀበለው ያስፈልጋታል። This choice might actually not be a bad thing, for, to guarantee the perceived overt benefits we Christians have been privileged to enjoy, i.e. public celebration of holydays, magnificent cathedrals, no persecution, Christian cultural heritage protected by the secular arm, we have unfortunately been forced to close our eyes when the government meddles with both hands in church affairs appointing whoever they want to and deposing and imposing suffering to those who do not wish to go with the flow. Thus altogether abandoning previously cherished benefits might actually liberate the church from the unseen hands pressuring and interfering in her internal affairs which are threatening the church’s spiritual credibility.

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ደግሞ … ታሪካዊና ባህላዊ ሁነቶች ያቀዳጇትን ልዕልናዋን አስጠብቃ ፤ ከመንግስት ጋራ ያላትን ትስስር አሜን ብላ (አሁን በአንጻራዊ መልኩ እንደሚስተዋለው) የምትቀበል ቢሆን … ቤተክርስቲያኗ እንደ ተቋም … ማኅበረ ቅዱሳንና መሰል ተቆርቋሪ አካላት … የቤተክርስቲያኒቱን ህልውና ለማስጠበቅ ማንኛውንም ህጋዊና ሰላማዊ ርምጃ ለመውሰድ የሚያስፈራቸውና የሚያሸማቅቃቸው አንዳችም ጉዳይ ሊኖር በፍጹም አይገባም … ባጭሩ … they have to take measures to ensure that sagas like Waldiba will never happen again.

በመጨረሻ … በመንፈሳዊ አስተውሎታችን ጎዶሎነት የሚታይብን … የመንጋው ታናናሾች የሆንን … እኛ ክርስቲያን ወገኖቻችሁ … በዚህ ውጥረት በነገሰበት ዘመን … በመንታ መንገዶች ፊት ቆመናልና … የምንመርጠውንም እንመርጥበት ዘንድ የምንደገፍበትን ግልፅና አዋጭ አመክንዮ ለማስቀመጥ ባለመቻል … በጨለማ ውስጥ እንገኛለንና … እናንት … በመንፈስ የጎለመሳችሁ … እውቀት ስጋዊ ከእውቀት መንፈሳዊ የተሰጣችሁ … አባቶቻችን ካህናት … ሊቃውንት መምህራን … ወንድሞቻችን ሆይ … ጨለማችንን የምታርቀውን … ዋጋዋ እጅግ ውድ የሆነ … መንፈሳዊ ምክራችሁን አሁን እንሻታለን … እንዲህ ባለው አስጨናቂ ጊዜ የትኛውን መንገድ እንከተል ዘንድ ትመክራላችሁ? … ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለምትገኝበት ነባራዊ ሁነት ምላሻችን ምን ይምሰል ትላላችሁ? … አባቶቻችንና ወንድሞቻችን ሆይ ዝምታችሁ ይብቃ … አሁን ድምጻችሁን አሰምታችሁ ተናገሩን … አሁን!!


‘ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ ወይስ ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን?
ለኦርቶዶክሳዊው ሰው በኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ላይ ያልተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት ሊኖረው ይችላልን/ይገባዋልንስ!’ … እግዚአብሔር ፈቃዱ ቢሆን በቀጣይነት በዝርዝር የምንመለስበት ጉዳይ ይሆናል።


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።



ማስታወሻ፦ ይህ ጽሑፍ ሲዘጋጅ … ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ህልውናዋ እንዲጠበቅ ፤ ብሎም ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የቆመችበትን መሰረት/አእማድ በማቆምና ማንነቷን በመቅረፅ ረገድ ፤ የነበራትና ያላት ጉልህ አስተዋጽኦ ፤ እውቅና ሳይነፈገውና ሳይዘነጋ ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገር  በመቅናት … እንዲሁም … ወቅታዊ በሆኑ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ፤ ምዕመኖቿ  የሚሰጡት ምላሽ ምን ላይ ሊመረኮዝ እንደሚገባው የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ካለ ፍላጎት በመነጨ እንጅ ፤ በሌሎች የእምነት ተቋማት ላይ ግፍንና ጭቆናን ስለመፈጸም አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል። … ክርስትና እንዲህ ያለውን ድርጊት አያስተምርምና።  

Friday, July 12, 2013

‘ጎረቤትህ ሲታማ … ለኔ ብለህ ስማ’

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

‘ጎረቤትህ ሲታማ … ለኔ ብለህ ስማ’


ባለፉት ሃያ አመታት ከተመዘገቡ ለውጦች መካከል በጣም አስገራሚውና አወዛጋቢው … በሮማ ቤተክርስቲያን ላይ … ከቤተ ክህነት አወቃቀም ሆነ ከአስተምህሮ ወጥነት አንጻር የደረሰው ፍጹምና ድንገተኛ ዝቅጠት ነው የለውጡ ዱብ እዳ መሆንም የደረሰውን ዝቅጠት ከፍተኛና የከፋ ያደርገዋል። … ዝቅጠቱ … በቀጣዮቹ የቅርብ ዓመታት የቴሌቪዥን ተመልካቾች በሳሎኖቻቸው ተቀምጠው … ፋይዳ ያለው ነገር ለማድረግ ባለመቻል ስሜት ውስጥ ሆነው … የፓፓውን ባደባባይ መገደል እንዲመለከቱ … ግዙፉ የቅዱስ ጴጥሮስ ካቴድራል አለም አቀፍ የፈንጂ ኤክስፐርቶች በተጠመዱ ፈንጂዎች ፈራርሶ እንደሚወድም እንዲያሰላስሉ ግድ የሚል … ብሎም እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ወደሆነ ቀውስ ሊያድግ የሚችል ዝቅጠት ነው

ነገሮች አሁን ባሉበት ሁኔታ ይህ እየተስተዋለ ያለው ዝቅጠት ይገታ ይሆናል ብሎ ተስፋ የሚያስደርግ አንዳች አመክንዮ ያለ አይመስልም የዚህች ለአደጋ የተጋለጠች ተክርስቲያ አስተዳደራዊ መዋቅር ባለበት ሁኔታ ተጠብቆ ክፍለ ዘመኑን ይሻገራል ብሎ ለመጠበቅም የሚያስችል ምንም ተጨባጭ ምክንያት የለም የሮማ ካቶሊክ ተክርስቲያ ሃይማኖታዊ መንፈሷና እምነቷ አይከስሙም የቅዱስ ጴጥሮስ ዙፋን ተተኪም አይጠፋም ከሚለው እምነቷ አንጻር ወደፊት ምን አይነት ገጽታ ሊኖራት ይችላል የሚለው እንቆቅልሽ በራሱእኛ ዘመናውያኑ በህይወት ዘመናችን ተፈትተው ከማናያቸው እንቆቅልሾች መሃል አንዱ ነው

ተጨባጭ የሆኑ አሀዛዊ ሆኑ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች ወግ አጥባቂው’ ሮማ ካቶሊክ አእምሮ ለማመን የሚከብዱ ናቸው። የቀሳውስት ፣ የወንድና ሴት መነኮሳት፣ የይማኖት ወንድማማቾች የመካከለኛና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የግል ኮሌጅ ተማሪዎችአዳዲስ ጥምቀቶችን (የአዳዲስ አማኞችን) ፤ በካቶሊኮች መካከል የተከናወኑ ጋብቻዎች፤ የቆራቢዎች ፤ የንስሐ ገቢዎች፤ እምነታቸውን ያጸኑ/ያረጋገጡ አማንያንን ፤ …  ቁጥር … የሚያሳዩ መረጃዎች ፤ ከ1965 እስከ 1980 ያሉትን አመታት ሚያካልል ግራፍ ላይ ቢቀመጡ  ፤  ግራፉ የሚያመለክተው ፤ ቁልቁል ያለማቋረጥ የሚምዘገዘግ ዝቅጠትን ነው። ነዚህ ወሳኝ መረጃዎች/ጉዳዮች በተጨማሪ ስለ ፍቺ ፣ ወሊድ መቆጣጠሪያ ፣ ጽንስ ማስወረድ ፣ ግብረ ሰዶማዊነት ፣ እና ኮሚኒዝም የሮማ ቤተክርስቲያ አስተምህሮ ሙሉ በሙሉ የማይቀበሉ ካቶሊክ እምነት ተከታዮች መኖራቸውን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል

ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች ‘ስውር’ ነገር ግን ተጨባጭ ተጽእኖ የሚያስከትሉ ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በተገቢው ሁኔታ ክህነት የተቀበሉ ምን ያህል ቀሳውስት እንዳሉ ማወቅ ፍጹም አዳጋች ነው። ለቅስና የቀረቡ እጩዎችን ክህነት ከሚሰጡት ጳጳሳት በርካታዎቹ ምስጢራትን ለመፈጸም ስልጣት ያላቸው ፤ ቀድሰው የሚያቆርቡና ተነሳሕያንን ከጢአት እስራት የሚፈቱ ቀሳውስትን የመፍጠር እቅድ የሌላቸው ናቸው። ይህ ስልጣን ከሌለ ደግሞ ቅስና የለም ፤ ቅዳሴም ሆነ በንስሐ ስርየት ማግኘትም አይኖርም። የክህነት ተግባር የመፈጸም አቅም ያላቸው አለመሆናቸው ከቤተክርስቲያኒቱ ውጪ ባሉ አካላት እስከዚህም ግምት የሚሰጠው ጉዳይ ባይሆንም የካቶሊክ እምነት ተከታይ በሆነው ምዕመን ዘንድ ግን ይህ ጉዳይ የቤተክርስቲያኒቱን በመንፈስ መሞት የሚያመላክት እውነት ነው።

የቀረቡት መረጃዎች እጅጉን አስደንጋ ቢሆኑም የግዙፉን የሮማ ካቶሊክ አካል ሁለንተናዊ መፈረካከስ በተገቢው ሁኔታ ማሳየት የቻሉ ጠቋሚዎች ግን አይደሉም። … በመላው አለም የሚገኘውና ወደ 740 ሚሊዮን (*) የሚጠጋው የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይ … ከፍተኛ ቁጥር ያለው ፣ እጅግ የተማረ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል አዳዊ ይማኖታዊ ተቋምን ይወክላ… ይህንን አሃዳዊ ሃይማኖታዊ ተቋም ፤ የሚያስተዳድረው አካልም ረጅ እድሜ ያስቆጠረና ትልቅ ዝና ካላቸው መናብርት መካከል አንዱ ነው - ቫቲካን። ነገር ግን በጦርነትና በሰላም፣ በረብና በብርካቴ፣ በዝቅጠትና በእድገት ፤ …  ይህን በመሳሰሉ ጉዳዮች ይህ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ተቋም (የካቶሊክ ምእመን) ይህ ነው የሚባል ትርጉም ያለውና የቤተክርስቲያኒቱን እምነት ታሳቢ ያደረገ … ፅዕ የሚያሳድር አልሆነም። እንዲያውም ይህ የካቶሊክ ማሕበረሰብ በኮሚኒስትና ካፒታሊስት ርእዮተ አለሞች ከሁለት ጎራ የተከፈለ ነው። ይህ ደግሞ በፍጥነት ከተስተዋለው የአምልኮትና የውስጣዊ ታማኝነት መዳከም ይልቅ ይበልጥ አስገራሚ ጉዳይ ነው ምክንያቱም ከጥቂት ጊዜያት በፊት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያበአለም አቀፍ ፖለቲካና ርእዮተ አለም መስክ ከፍተኛ ተፅዕኖ ታሳድር የነበረች ሀያል ተቋም ነበረችና።

ይህ የታየው መዳከም … ምንም እንኳ ባለፉት ሀያ አመታት ውስጥ ይበልጥ በጉልህ እየተስተዋለ ቢመጣም… የረጅም ዘመናት ለውጥ ውጤት ነው። ዛሬ ላይ ሆነን መለስ ብለን ስንመለከተው ከ400 አመታት ቀደም ብሎ ውጤቱ ሊተነበይ ይችል እንደነበር መገመት አያዳግትም ፤ … ምክንያቱም የሮማ ካቶሊክ አደረጃጀት ያከናወነው 1000 ዘመን እድሜ ያስቆጠረው ሙከራ የከሸፈው በዚያ ዘመን (ከ400 አመታት በፊት) ግድም ነበር ይኸው የካቶሊክ አስተዳደር የሰው ልጅን የፖለቲካ ማሕበራዊ እና የስነ-ባል መስኮች ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ሞክሮ የነበረ ሲሆን ፤ … በሂደቱም የቤተክርስቲያኒቱን ፤ በአጠቃላይ የክርስትና መርሆዎች እርግፍ አድርጎ አስከመተው ደርሶና ፍጹም አለማዊ ፈርጆችን ይዞ ነበር።

በ1979 መጨረሻ የተፈጠረ እምብዛም ትኩረት ያልሳበ አነስተኛ ክስተት የዚህን ሮማዊ አደረጃጀት ውድቀት ያሰመረ ነበር። ህዳር በባተ በ3ው ቀን 63 የአሜሪካ ዜጎች ቴሂራን በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በአያቶላህ ኮሚኒ አብዮታዊ ካድሬዎች ታገቱ ፤ ይህን ተከትሎም ዳግማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ የቴሂራን ተወካያቸው የሆኑትን አርችቢሾፕ አናቤል ቡግኒኒን በሳቸው ስም ጣልቃ በመግባት ከአያቶላህ (ኮሚኒ) ጋር ታጋቾቹ በሚፈቱበት ሁኔታ እንዲወያዩ ያዟቸዋል። ነገር ግን መፍትሔ ሊገኝ ልቻለም።

“ታላቁ ፓፓ አሁን ገና … ታጋቾች ሲፈቱ ማየት በመውደዳቸው ተገርሜያለ” አያቶላህ ቡግኒኒን ገሰጽዋቸው “ሻሀሁ (የኢራን መሪ) ህዝባችንን በጨቆነ ጊዜ ታላቁ ፓፓ ጣልቃ አልገቡልንም እናንተ ክርስቲያኖች ጠባያችሁ እንደክርስቶስ አይደለም… ኢየሱስ ያደርገው የነበረውን ታደርጋላችሁ ብለን ጠብቀን ነበር … ምክንያቱም እርሱ አለጥርጥር ሻሃሁ ያደርሰው የነበረውን ጭቆና መቃወሙ አይቀርም ነበር … ታላቁ ፓፓና የየሆኑት ክርስቲያኖች እንዲህ የሆኑት ለምንድነው…? የአያቶላህ ጥያቄ ነበር …

ኮሚኒ ቫቲካን ስልጣኗን አለአግባብ ተጠቅማለች ብሎ ጣቱን ቢቀስርም መሰረታዊና አንገብጋቢ ለሆነ አንድ ጥያቄ ግን መልስ አልሰጠም ነበር - የትኛውም ይማኖታዊ ተቋም … ሮማ ካቶሊክ ይሁን እስልምና … አለማዊውን ስልጣን ርካብ መጨበጥ/መቆናጠጥ ይገባዋልን? አያቶላህ ይህን ጥያቄ ያነሳ ዘንድ ፈጽሞ አይደፍርም … ምክንያቱም ለሱ ምድራዊውና መንፈሳዊው ስልጣን ፍጹም አንድ የሆኑ … የአላህ መለያየት የሌለበት አንድ  ስልጣን ሁለት መገለጫዎች ናቸው። ነገር ግን በጥንታዊትዋ የክርስቶስ ተክርስቲያን ዘንድ ይህ እሳቤ ፈጽሞ አልነበረም።

በቤተክርስቲያኒቱ የመጀመሪያዎቹ 250 ዓመታት እድሜ የቤተክርስቲያን አባቶች … አያቶላህ ለጠየቀው ጥያቄ ስለሚሰጡት መልስ አንዳች ማቅማማት/ወላወል አልነበረባቸውም። የቤተክርስቲያኒቱ ስልጣን መንፈሳዊና መንፈሳዊ  ብቻ ስለመሆኑ እርግጠኞች ነበሩ። … ክርስቶስ በስጋዌው ዘመን ሳለ ስለአዲሲቱ መንግስት በአንደበቱ የተናገራቸውን ንግግሮች በሚገባ ያስታውሳሉ - ‘የእግዚአብሔር መንግስት’፤ ‘መንግስተ ሰማያት’ የሚሉትን። እዚህ ላይ ታዲያ ፤ እነዚያ አባቶች ፤ ኢየሱስ ‘የእግዚአብሔር መንግስት’፤ ‘መንግስተ ሰማያት’ ሲል ምን ማለት እንደፈለገ ለመረዳት ይሞት ዘንድ አሳልፎ ከሰጠው ከሮማዊው አስተዳዳሪ ፤ ከጴንጤናዊው ጲላጦስ ጋር አድርጎት የነበረው ቃለ ምልልስ ላይ ይመረኮዛሉ

ጲላጦስ ‘ታዲያ አንተ ንጉስ ነህን?’ በማለት በጠየቀው ጊዜ
“አዎን ነኝ ፤ ነገር ግን መንግስቴ ከዚህች አለም አይደለችም እንደሌሎች መንግስታት ከዚህ አለም ብትሆን ኖሮ አገልጋዮቼ ነጻ ያወጡኝ ዘንድ በወደዱ ነበር …” የክርስቶስ ምላሽ ነበር።

በ67 ዓ.ም በሆነው የሐዋርያው ስምኦን ጴጥሮስ ሞትና በ312 ዓ.ም መካከል ሰላ አንድ ፓፓዎች የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪዎች በመሆን የሮማ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተሹመዋል። ከመጀመሪያዎቹ አስራ ስምንት ፓፓዎች መካከል አንዳቸውም ተፈጥሯዊ ሞትን አልሞቱም ሁሉም ያለፉት በጭካኔ በግፍ ተገድለው እንጅሰላሳ አንዱም የሮማ ፓፓዎች እያንዳንዳቸው በሕይወት ሳሉ የሰማያዊውን መንግስት ስልጣን ገንዘብ ያደረጉ የነበረ ሲሆን … ሁሉም ቀድመዋቸው የነበሩ አባቶችን አስተምህሮ ሳይበርዙ ሳይከልሱ አስተምረዋል - ይኸውም በእግዚአብሔር መንፈስ መመራትን ፤ በመንግስቱ ስርዓትም መገደብን ዚህ ሚታየው አለም ፍጻሜ በኋላ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ድል አድራጊነት ፤ የኢየሱስን ዳግም ምጽት መጠበቅን ነበር

በ312 ዓ.ም የሮማው ንጉሰ ነገስት ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን ተቀበለ ፤ ከአስር አመት በዋላም ክርስናን የሮማ ግዛት ይፋዊ ይማኖት እንዲሆን አደረገለቀጣዮቹ 1650 አመታት ክርስትና በአውሮፓ ፖሊቲካዊና ማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የፈጠረ ክስተት ለመሆን በቃ። ነዚህም አመታት የሮማ ፓፓዎች በአውሮፓና በምእራቡ አለም እጅግ በጣም ወሳኙን ሚና ከሚጫወቱት ግለሰቦች መካከል ዋነኞቹ ሆነው ነበር።

የሕዳሴ/ሬነሳንስ ዘመን ተብሎ በሚታወቀው የመካከለኛው ዘመን የመጀመሪያዎቹ አመታት ኢየሱስ የመሰረታት ቤተክርስቲያን ፤ እጅግ በተዋቀረ አደረጃጀት ፤ … የስልጣን ተዋረድ የጠበቀች ፣ ማእከላዊ አስተዳደር ያላት በስልጣኗ ፍጹም የሆነች ፤ ስለየበላይነቷ ቀናኢ የሆነች ፣ በአብዛኛው በሹመት ጥቂት ደግሞ በምርጫ የሚሾሙባቸው የአስተዳደር ቦታዎች ያሏት ፣ የዘውዳዊ አገዛዝ ስርአት መገለጫዎችን ሁሉ ያሟላች ፤ … ተክርስቲያን ሆና ብቅ አለች… ኤሪክ ኤም. ደ ሳቬንተም (የተባለ ምሁር) ዘውዳዊ ስርአትን በቅርቡ የተረጎመው “መሰረቱን አስቀድመው በታቀዱ እሳቤዎችና ርእዮተ አለሞች ያደረገ ፣ ተዋረዱን በጠበቀ የአስተዳደር መዋቅር ልውናውን ያስጠበቀ ፣ የማሕበርና ሌሎች የቡድን ጥቅሞች በተራቀቀ ጽንሰ ሐሳብ የተገለጹበት ፣ ተፈጥሮአዊ እድገት የሚያሳይ ፣ መገለጫዎቹን ለማግነንና ለመጠበቅ ትውፊት ላይ የሙጥኝ ያለ ፣ በሕልውናው ላይ ከውጪ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመመከት በጽኑ የሚፋለም/የሚከላከል ፣  ውስጣዊ ሰላሙን በሳብም ሆነ በቁሳዊ መንገዶች ለማስጠበቅ የሚተጋ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስርአት” በማለት ነበር … እንግዲህ በሮማ የምትገኘው የክርስቶስ ቤተክርስቲያንም ፤ ይህን ወደ መሰለ የአገዛዝ ስርአት ነበር አዝጋሚ በሆነ ሁኔታ የገባችው/የተለወጠችው።

ነገር ግን ፓፓዎቹ ወደ ምድራዊ አስተዳደር እጃቸውን ማስገባት ከጀመሩበት ቅፅበት አንስቶ … ጎን ለጎን … የሃይማኖታዊ ተቋማቸውን መንፈሳዊ ልዕልና ለማስጠበቅና ፤ ምዕመኑንም በመንፈሳዊ ስርዓት ለመምራት እንዳይችሉ … ከባድና ቋሚ በሆነ … በማይወልቅ እግረ ሙቅ እግር ተወርች እየታሰሩ ነበር። … ከተለያዩ (ከማይመስሏቸው) ጎራዎች ጋራ ወዳጅነትን ለመፍጠርና ፤ በእነዚህም ጎራዎች ላይ ተፅዕኖ የማሳደር ፍላጎታቸውን ለማርካት … ይማኖታዊ ተልዕኳቸውን/ስልጣናቸውን ወደ ጎን ባሉት መጠንም … እግረ ሙቁ እየጸናና … ከእግራቸው አልፎ ወደ አንገታቸው በመድረስ እያነቃቸው ይሄድ ጀመር። ጭራሽ በጊዜ ሂደት ፓፓዎቹ ራሳቸው … አሉ ተባሉ የፖለቲካ አቋማሪዎች መካከል የሚጠቀሱ ለመሆን በቁ … እስካለንበት ዘመን ድረስም ይህንን ሚና ጨርሰው ትተውት አያውቁም እንዲያውም ከዚያ በተቃራኒው ድርጊታቸው በጊዜ ሂደት ቅቡል እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳበማሕበራዊ ጉዳዮች የሚታየው የፓፓዎች ጣልቃ ገብነት ይማኖታዊ መርሆ ተደርጎ ሊቆጠር ምንም አልቀረውም ‘ግሊ አፋሪ ፓብሊሲ’ … የተሰኘ ኢጣልያዊ መሰረት ያለው የቤተክርስቲያኒቱ ብሂል እንደሚያሰምርበት የእለት ተእለት የፓፓዎቹ ትኩረት ማሕበራዊ ጉዳዮች እንደሆኑ የታመነበት ጉዳይ ነበር። መሰረታዊ የክርስትና እሴቶች ለአደጋ በተጋለጡባቸው ወቅቶች እንኳ ፓፓዎቹ አቋም ከመያዛቸው አስቀድሞ ዲፕሎማሲያዊ አሰላለፎችን ፣ አጋር ወገኖች የጣሉባቸውን ድርሻ /ክለብ ኦብሊጌሽንስ/ ፣ ፖለቲካዊ ስምምነቶችን ፣ ባሕላዊ ተዛምዶዎችን ፣ የድምበር ይገባኛል ጥያቄዎችን ፣ ኢኮኖሚያዊ ጥቅማ ጥቅሞችን ፣ የግል ምኞታቸውን ፣ የቤተሰቦቻቸውን እቅድ፣ የግዛት ማስፋፋት ሳቦቻቸውን ግምት ውስጥ ማስገባታቸው አይቀሬ ነበር

ሃይማኖታዊው አስተዳደር ከምድራዊው ጋር በመጋባቱ ምክንያት የተከተለው በእግረ ሙቅ የመቀፍደድ አጋጣሚ ፤ ታላቁን የፍቅር ግና ከፍተኛ የስነ ምግባር አስተምህሮዎች ይሰብኩ በነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶች ላይ ምን ያህል ሊከብና ሊያጎብቸው እንደሚች ያለፉ ፓፓዎች ሕይወት በገሀድ የሚገልጸው እውነት ነው። በታሪክ ድርሳናት በርካታ ምእራፎች እንደሚስተዋለው ፓፓዎቹ ምድራዊ ስልጣንና ብትን ከቤተክርስቲያኒቱ ጫንቃ ላይ አውርዶ ለመጣል … ከሰው ልጅ ድጋፍና ስጋዊ ከለላ ተላቃ መንፈሳዊ ልዕልናዋን ጠብቃ በራሷ እንድትቆም … ጸንታ እንደምትኖር ኢየሱስ ለቤተክርስቲያኑ ገባው ቃል ኪዳን ላይ ብቻ እንድትኖር ፤ እና የፈቀደላትን የመንፈስ ቅዱስ ስልጣን ብቻ እንድትጠቀም …  በርካታ አጋጣሚዎች ተፈጥረውላቸው ነበር ፤ … አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ እነዚህ መልካም አጋጣሚዎች የተፈጠሩት ፓፓዎ ምድራዊ ገዢዎች እንደሚያደርጉት በፖለቲካ ስልጣን ውስጥ ገብተው ሲያቋምሩ ፤ ቁማራቸው ከሸፎ/ባርቆ አስከፊ መዘዝ ባስከተለባቸው ጊዜያት ነበር። የሮማ መሪዎች ግን ባንጻሩ … በአጋጣሚዎቹ ላይ ፊታቸውን ሲያዞሩና ፤ ጭራሽ ያጡትን ማንኛውንም ምድራዊ ስልጣንና ተቀባይነት መልሰው ለማግኘት ሲፋለሙ ፤ ይኸውም በአመዛኙ ሲሳካላቸው እንመለከታለን። … የተሻሉ የሚባሉትም /መልካሞቹ?/ እንኳን  … ፓየስ 9ኛ እና ፓየስ 12ኛ ለምሳሌ … ምድራዊ ስልጣን መጠቀምን ሙሉ ለሙሉ  እርግፍ አድርገው ሊተዉ አልወደዱም።  ባጠቃላይ ክፍለ ዘመናቱ የነበሩት ፓፓዎች መርሆዋቸው የነበረው ያጡትን ማንኛውንም ስልጣን መልሰው ለማግኘት የተቻላቸውን ያክል መጣር ነበር

እንዲህም ሆኖ … በአመዛኙ የተዳፈነ ቢሆንም እንኳ ሁሌም የቤተክርስቲያኒቱ ሃይማኖታዊ (መንፈሳዊ) ግዳጅ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰውን … ይህን የሃይማኖታዊ አስተዳደርና ምድራዊ ስልጣን ቁርኝት የመስበር ፍላጎት ይስተዋል ነበር። ታላቁ የፍሎረንስ /ጥልያን/ ተወላጅ ባለቅኔ ዳንቴ አሊግዬሪ ‘ዘ ኢንፈርኖ’ በተሰኘው ድርሰቱ ይህንን ጉዳይ … ‘የመጀመሪያው ባለጸጋ የቤተክርስቲያን አባት’ በሚላቸው እና ከንጉሰ ነገስት ቆስጠንጢኖስ ጋር ባደረጉት ስምምነት… ቤተክርስቲያንን ከነበረችበት የምድራዊ አስተዳደር ታዳኝነት በቅጽበት … ያድናት የነበረው አካል ባልንጀራና ፤ የዚሁ አካል የመንፈሳዊና ግብረገብ አስተምህሮ መሰረት ወደመሆን እንድትለወጥ … ባደረጓት ፓ ሲልቨስተር 1ኛ ላይ ትኩረት ባደረጉ ጥቂት ስንኞች ጉዳዩን እንደሚከተለው ይገልጸዋል
Ahi! Costatin! Di quanto mal fu matre
Non la tua conversion, ma quella dote
Che da te presse il primo rico patre!

ወዮ! ቆስጠንጢኖስ! ወደዚች ዓለም ምን አይነት ክፋት አመጣህ!
(ክርስትናን) በመቀበልህ/በጥምቀትህ/ አይደለም ፤ በዚያ ጥሎሽ ነው እንጂ፤
የመጀመሪያው ባለጸጋ አባት ካንተ በተቀበለው!’

ልክ እንደ ዳንቴ ሁሉ … ባለፉት ክፍለ ዘመናት በነበሩ በርካታ ካናትና ምእመናንም እምነት … በጎች እንደ አንበሳ ለመሆን በጣሩ ጊዜ ሁሉ እንደአህያ የመሆን ውርደት መጎናጸፋቸው አይቀሬ ነው።

ማስታወሻ፦ በ(*) ምልክት የተቀመጠውና 760 ሚሊዮን የሚለው አሃዛዊ መረጃ የመጽሐፉ አዘጋጅ መጽሐፉን ባዘጋጀበት ዓመት ግድም ፤ ይኸውም ከ33 ዓመታት በፊት የተወሰደ አሃዛዊ መረጃ ነው።

The Decline and Fall of The Roman Church
By: Malachi Martin, 1981
(The Breakdown - የመጽሐፉ መግቢያ)

መግለጫ፦

የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ሆይ … የመጽሐፉ አዘጋጅ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ በግልጥ ካስቀመጠውና ፤ ሃይማኖታዊው አስተዳደር ከምድራዊው ስልጣን ጋራ በመቆራኘቱ … ተቀባይነትንም ከምድራውያን ለማግኘት በመታተሩ ምክንያት ፤ በተከሰተው የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ልዕልና ማጣት እና የሃይማኖታዊ እሴቶች መበላሸት (መጥፋት) መነሻነት፦ (ከብዙ በጥቂቱ)

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን …
1.      በወግ አጥባቂዎች …
2.     በአዲሱ ቅዳሴ አማኞች (ኖቨስ ኦርዶ)/በፓፓው ታማኞች
3.     በሴዴቫካንቲስቶች (ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በኋላ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ባዶ ነው ብለው በሚያምኑ)
4.     በፓዬስ 9ኛ ማኅበርተኞች … ለ4 ስትከፋፈል
የራሽያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ደግሞ …
1.      በጆሴፋይቶች (የካታኮምብ ክርስቲያኖች)
2.     በሞስኮ ፓትሪያሪኬት ታማኞች
3.     በዲያስፖራ የራሺያ ኦርቶዶክሶች … ለ3 ተከፋፍላለች።
የግሪክ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም እንዲሁ …
1.      ኦልድ ካላንደሪስቶችና
2.     ኒው ካላንደሪስቶች ተብለው ለሁለት ተከፍለዋል።
የእኛስ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምን ዓይነት ጎዳና ላይ እየተጓዘች ነው? … ለመሆኑስ የሮማ ፤ የራሽያና ፤ የግሪክ ቤተክርስቲያናት ከተጓዙበትና ለውድቀት ከዳረጋቸው መንገድ የተለየ መንገድን መርጣለችን? …  በቤተክርስቲያኗ የውስጥ ጉዳዮች ላይ (የፓትሪያሪክ የምርጫ ሂደትን ጨምሮ) የመንግስት ጣልቃ ገብነት/ተፅዕኖ በግልፅ አይስተዋልምን? … ቁልፍ የሆኑ የአስተዳደር ቦታዎቿስ በመንግስት ጉዳይ አስፈጻሚዎች አልተያዙምን? መንፈሳዊ ግዳጇንስ ፤ ከመንግስት አጀንዳዎች ጋራ የማይጋጩ/የማይጣረሱ እስካልሆኑ ድረስ ብቻ የምትፈፅም አልሆነችምን? … መጭውስ ጊዜ ለቤተክርስቲያናችን ምን መልክ የሚኖረው ይመስላችኋል? …. ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ …

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።