በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ያልተመለሰው ጥያቄ፡ የጃዋር መሃመድ ‘በአክሱም መስጊድ ይሰራ’ ጥያቄ በኦርቶዶክሱ
ማኅበረሰብ ላይ ያልተመለሰውን ጥያቄ ሲጎትት
A new reality has dawned upon us Christians. The French
revolution has introduced a new type of government previously unheard of during
the middle ages. During the medieval world, monarchy and Christianity were
inseparable part of the same whole. Monarchs were considered divinely
instituted with the blessing of the church. The post-French revolution world,
however, taking as a prototype the atheistic and secular revolution of France,
waged war on religion and sought, if
possible, to eradicate if not sideline it to an impotent status.
Consequently, the church and state as distinctly separate entities came to the
fore.
ይህ … የቤተክርስቲያንና የመንግስት ፍጹም የመለያየት ሀሳብ(እውነት) … በክርስቲያኑ ማኅበረሰብ ዘንድ … በተለያየ
አተያይ የታየ የነበረ ሲሆን ፤ የምዕራቡ አለም ክርስቲያኖች … ሀገራቶቻቸው የተገነቡባቸውን ክርስቲያናዊ መሠረቶች የሚያፈልስ
… ሃይማኖታዊ እሴቶችን የሚያጠፋና ፤ መንፈሳዊ ልዕልናቸውን የማያስጠብቅ አፍራሽ ክስተት አድርገው ሲመለከቱት … ለብዙ ምዕተ ዓመታት
… በሙስሊም መንግስታት አገዛዝ ስር የነበሩት የምስራቁ ዓለም መሰሎቻቸው ባንጻሩ ግን … በሃይማኖታቸው ምክንያት … በገዥዎቻቸው
ይደርስባቸው ከነበረ ጭቆና ፤ ይጣልባቸው ከነበረ ከፍተኛ ግብር ፤ … ፤ እንዲሁም ይህን ከመሰል የግፍ አገዛዝ ሁሉ የተነሳ …
ክስተቱን (የመንግስትንና የቤተክርስቲያንን ፍጹም መለያየት) ፤ … አንዳች እኩልነትንና የሃይማኖት ነጻነትን ይዞላቸው እንደሚመጣ
… ጥሩ አጋጣሚ/ተስፋ … እጃቸውን ዘርግተው ነበር የተቀበሉት። It is with this hope in mind
that Coptic Christians welcomed Napoleonic conquest of Egypt and British
colonial rule; and Turkish Christians for the secularization of the Turkish
government following the fall of the Ottoman Empire.
In Ethiopia, however, the situation has been very similar to
the Holy (Christian) Roman Empire. Both
civil and religious affairs were heavily intertwined and up until recently
(& for those who still choose to shroud themselves with the dream of the
Mighty Ethiopia), for the average Christian, the word ‘Ethiopia’ is synonymous
with the term ‘Christian’. The monarchs themselves, although they frequently
quarreled with the church, have often received strong education in clerical and
theological training, many of those who put on the crown having been priests
themselves. ለዚህም ሀቅ እንደ ማስረጃ … ኢትዮጵያዊው ንጉስ … ንጉስ
አጼ ካሌብ ፤ የየመን ክርስቲያኖች ጭቆናና እንግልት ግድ ብሎት ወደ የመን መዝመቱን ፤ ንጉስ ገላውዲዎስ ከኢየሱሳውያኑ ጋራ በተደረጉ
ሃይማኖታዊ ክርክሮች/ጉባኤዎች ፤ ዋና ተከራካሪ ሆኖ መሳተፉን ፤ ንጉስ አጼ ሚኒሊክ ሀገራዊ ወራሪ ፤ ሀገር በተወረረ ጊዜ የእግዚአብሔርን
ታቦት ከፊት አስቀድመው ጦርነት መዝመታቸውን ፤ … ወ.ዘ.ተ. ማንሳት ይቻላል። (The Jesuits,
who were learned men, were betrayed into long theological disputes. The abuna
and the native clergy could not stand up against them, but the king (ንጉስ ገላውዲዎስ), as
they freely admit in their own dispatches, often drove Oviedo into a corner.) –
A.H.M. Jones, E. Monroe, (1935). The History
of Abyssinia. The Clarendon Press, New York.
The
seeds of the divorce between church and state were first sown in 1974 when
the Derg regime came to power, where the state became officially atheistic and
the church was frowned upon even to the point of castigation (Death of Abuna
Teklahaimanot; closing of the Trinity Church; burning and closing of several
churches; appointing of pro-government patriarch). However, the church
community as a whole and the individual Christian, more or less, were able to
tolerate the ‘new reality’ because of the hostile attitude of the Derg towards
‘alien’ religions and because compared to other religious organizations, the
church was relatively favored (for being ‘አገር በቀል’). Moreover, the church was
content with the pan-nationalistic agenda (as contrasted to the ethnic-based
reorganization of the EPRDF era) of the Derg believing deep down that as long
as the pro-Ethiopian agenda is carried forward, she (the church) would have a
stake to claim (for Ethiopian
nationalism is ultimately founded on the church).
ኢህአዴግ በበኩሉ … ይህንን … የመንግስትና የቤተክርስቲያን ፍቺ/መለያየት … አንድ እርምጃ ወደፊት አራመደው። … አዲሱ
መንግስት … የመለያየቱን ጽንሰ ሃሳብ … የህገ መንግስቱ መሰረታዊ ይዘት ከማድረግ ባለፈ … ሁሉም ሃይማኖቶች በህግ ፊት እኩል
መሆናቸውን የሚያረጋግጡ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን/እርምጃዎችን መውሰድ ጀመረ። … አብያተ ክርስቲያናትን መዝጋት ፤ የቤተክርስቲያን
አባቶችን ማንገላታት/ማሰቃየት ፤ እምነት የለሽነትን ማወጅ ፤ እነዚህና መሰል ጥቃቶች ማድረስ አንድ ነገር ነው … (እጅጉን የሚያም
ፈተና ቢሆንም … የቅድስት ቤተክርስቲያንና የልጆቿ ጫንቃ ሊሸከመው የማይችለው ተግዳሮት ግን አይደለም … ለአሁኗ ኢትዮጵያ የዋለችውን
ውለታ የሚዘነጋ … ለሀገሪቱ የታሪክና የማንነት መሰረት መሆኗን አጥፍቶ ያልነበረ አዲስ ታሪክ የሚጽፍ አይደለምና) … ነገር ግን
… በሺህ በሚቆጠሩ ዓመታት ውስጥ አምጣ በወለደችው ማንነት ላይ ተቁሞ … እንዲያም ሲል ይህንን ማንነት የኩራት ምንጭ እያደረጉ
(እንግዳ ተቀባይ ፤ ሀገሩን ወዳድ ፤ ባህል ወጉን ጠባቂ ፤ …ወ.ዘ.ተ ተብሎ እንዲጠሩ እየፈለጉ) … የዚህን ማንነት ምንጭ ቆርጦ
ለመጣል/እውቅና ለመንፈግ የሚደረግ ሩጫ ግን ፍጹም ሌላ ነገር ነው … ዋጋውም እንዲህ በቀላሉ የሚተመን አይሆንም። (በቅርቡ የፌዴራል
ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ተቋማትን ለመመዝገብ ረቂቅ መመሪያ ማውጣቱን ልብ ይሏል)
Nevertheless, the disorganized, demoralized and
factionalized Orthodox believers also learned to bear the new ideology and,
though it is now more blatant to their awareness, they chose not to wake up from the dream (of the once glorious and,
more importantly, Christian Ethiopia), not only because it is a beautiful
dream, but also the reality awaiting them was dreadful.
Now, however, when issues like the Waldiba Affair, (several
other scenarios/incidents jeopardizing the church’s integrity and the current
controversy over Muslims demanding to build Mosque in Axum, the spiritual
capital of the Ethiopian Orthodox Church), come to the fore, the otherwise
dreaming/drowsy Christian is inevitably confronted to the inescapable reality of the death of Christian Ethiopia.
በግልፅ እንደሚስተዋለው … አብዝሃው የክርስቲያን ማኅበረሰብ … አንገብጋቢ በሆኑ ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ
… ተናጠላዊም ይሁን ቡድናዊ አቋም (ውሳኔ) ለመያዝ/ለመውሰድ … ግልፅ የሆነ ቁርጠኝት/ጥብዓት ይጎድለዋል። … ይህንንም ሩቅ መጓዝ
ሳያስፈልግ … በጅማና ነገሌ በደረሱ የክርስቲያን ወገኖቹ እልቂት … በአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት መነሳት … እንዲሁም የቅዱሳን በዓት
በሆነው የዋልድባ ገዳም መደፈር … ላይ ያሳየውን … ዘላቂነት የሌለው … ወቅታዊ መረበሽ/ድንጋጤ ወለድ ምላሹን ፤ በጊዜ ሂደትም
ለጉዳዮቹ የማያዳግም መፍትሄ ሳያስቀምጥ/ሳይሰጥ ወደ ቀደመ ማንቀላፋቱ መመለሱን በማንሳት ማረጋገጥ ይቻላል። … አሁን አሁን ግን
ይህንን የማንቀላፋት ዘመን ማብቃት ግድ የሚሉ አስገዳጅ ሁነቶች በፊታችን እየተጋረጡ ይገኛሉ … ከ40 እና 50 ዓመታት በፊት ልንመልሰው
ይገባን የነበረው ጥያቄ … ክብደቱን ጨምሮ ጊዜ አይሰጤ ሆኖ ቀርቧል … እኛ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችም በመንታ መንገድ ላይ ቆመናል
… ሁለቱ መንታ መንገዶች ጠቅለል ባለ መልኩ ሲቀመጡ የሚከተለውን ይመስላሉ፦
a.
To pursue the ‘never say die’ attitude over the claim that ‘the Christian
Ethiopian Empire is long gone’ and with the zeal typical of our forefathers
strive through all available means to reawaken/revitalize
the Christian Ethiopian Spirit. (እየኖርንባት ያለችውን ኢትዮጵያ … ልባችን ውስጥ ባለችው ኢትዮጵያ የመተካት
የሕይወት ምርጫ … የ40 እና 50 ዓመቱን ስህተት የማስተካከል ግብግብ … መሰረቷን ኦርቶዶክሳዊ ማንነት ላይ ያደረገችው ኢትዮጵያ
፤ ሌላ ባዕድና እምነት የለሽ ማንነትን ገንዘብ እንዳታደርግ የመታደግ ፈተና … የምናስባትን ክርስቲያናዊት ኢትዮጵያ ክርስቲያናዊ
መሠረቶች የማጠባበቅ ምርጫ …)
b.
To embrace
the separation of church and state with all its implicit consequences; the
subsequent death of Ethiopia as a
Christian state and accordingly, learn to live under the new circumstances inevitably
leading to the way of life the catacomb Christians used to lead. (ነፍሳቸውን በገነት ያኑረውና ፤
ግብጻዊው መንፈሳዊ መሪ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ‘ግብፅ ያለችው በልባችን ነው ፤ በልባችን ያለችውን ግብፅ ግን በዓይናችን የምናያት
ለማድረግ ሁኔታዎች አይፈቅዱም’ ይሉ እንደነበረው … እዚህና እዚያ በሚከሰቱ (ልባችን ውስጥ ካለችው ክርስቲያናዊት ኢትዮጵያ ጋራ
በማይጣጣሙ) ክስተቶች ፤ አሁንም አሁንም መደነቁን ፤ ‘ምን ሲደረግ? … እንዴት ተደርጎ?’ እያሉ መደንፋትና ማቅራራቱን ትተን
… ነባራዊዋን ኢትዮጵያ ተቀብሎ … በአባቶቻችን ደምና አጥንት የቆየውን ክርስቲያናዊ ውርስ/ርስት/ዕሴት አንገት ደፍቶ በማስረከብ
ከመሬት በታች መኖር …
A significant number of Christians go by the former
alternative, i.e. are still reluctant, to say the least, to part ways with the
former Christian Ethiopia. When not even the generation that had lived
believing and dying for such religious ideals has not yet passed away, it is
indeed difficult for them to accept this new brand of Ethiopia, although it has
been a long time since the ink on the constitution has dried. One still sees
prayers and mottos such as ‘እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አስራት ሀገርሽን - ኢትዮጵያን ጠብቂያት’ posted
on taxies and busses which reflects their inherent feelings about the Ethiopia
that is in their hearts.
በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት ክብረ በዓል ወቅት ፤ ‘አንድ ጌታ
፤ አንድ ሃይማኖት ፤ አንድ ጥምቀት’ ኤፌ 4፦5 የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በልብሶቻቸው ላይ ጽፈው አደባባይ
የወጡ ወጣቶችን አስመልክቶ … የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን ያላግባብ የ ‘መሰል ጽንፈኝነቶች ጠንሳሽ’ አድርገው
በአደባባይ ሲከሱትና … በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው … ግልጽ በሆነ አማርኛ … ‘ክርስቲያናዊት ኢትዮጵያ የምትባል ነገር የለችም’ …
ሲሉን እንኳ … ሊሰማ በሚችልና ትርጉም ባለው መልኩ የቀረበ የመቃወምም ይሁን … በልባችን ከምናምነው እምነት ጋራ ፈጽሞ
የማይስማማውን የጠቅላይ ሚኒስቴሩን ሀሳብ በይፋ የመቀበል ተነሳሽነት አላሳየንም።
Writers like Mesfin Negash, on the other hand, seem to have
accepted the latter perspective. They seem to have made their peace with the
Athiest (and to some extent hostile to the traditional Ethiopian Christian
mindset) Ethiopia which refuses to give any credit to any kind of god, let
alone to bow down to previous church privileges. They thus seem to have no
problem for the church to have to let go of her long cherished strong holds and
religious holy sites simply because the times have changed and consequently,
she has to readjust with the changing circumstances. Surely they must realize how the holy fathers of the previous era would
have reacted if they had heard that a mosque was going to be built on Axum.
But, we suppose people falling into this category feel that these are the
things the church must endure in order to maintain her status under the new
circumstances. But if they are ok with
the Muslims striving to achieve their constitutional rights to the fullest,
then they should be reminded that when the church to which they belong to is
stripped of her rights, it is their duty
to stand up on her behalf and see to it that her rights are, in turn, fulfilled
to the fullest.
Unfortunately prominent and influential Christians, who do
not hesitate to associate themselves with the new image of Ethiopia are doing
nothing about the injustice their church is enduring and yet we observe them
nodding in approval when other bodies are striving to get their rights achieved
at the cost of the orthodox church.
The uncertainty over which road to take is exhibited by the
recent ‘grip of indecision’ shown by the Christian faithful in general and
Mahibere Kidusan (who embodies the spirit of both reform and adherence to
tradition of the holy fathers) in particular. While the Christian faithful
looked in vain for guidance and support, to pursue their quest for justice on
the Waldiba affair, the society, unfortunately, poured cold water over the efforts
Christians were trying to make. (look at -Waldiba’s Crisis & a glimpse at MK’s Report)
ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን … ሁለተኛውን አማራጭ በመመርጥ ለመጓዝ የምትፈቅድ ከሆነ … ከሁሉ በፊት ከመንግስት
ጋራ የተሳሰረችበትን ማንኛውንም ማሰሪያ በጣጥሳ ልትጥል ይገባታል። … በመቀጠልም በምርጫዋ ምክንያት የሚሆነውን … በሀገሪቱ ከነበራት
ታሪካዊ ፤ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖዎች የተነሳ ፤ አግኝታቸው የነበሩትንና የእርሷና የእርሷ ብቻ የሆኑ ጥቅማ ጥቅሞችን ከማጣት
እና እርሷው ባቀናችው ምድር ላይ እንደ ባዕድ በተፅዕኖ ውስጥ ከመኖር ጀምሮ … - ከንጉስ ቆስጦንጢኖስ ዘመን አስቀድሞ ክርስቲያኖች
ይኖሩት እንደነበሩት ያለ … በብዙ ግፍና ጭቆና መሃል የመኖር ግዴታ ውስጥ እስከመግባት ልትደርስ የመቻሏን ሀቅ በጸጋ ልትቀበለው
ያስፈልጋታል። This choice might actually not be a bad thing, for,
to guarantee the perceived overt benefits we Christians have been privileged to
enjoy, i.e. public celebration of holydays, magnificent cathedrals, no
persecution, Christian cultural heritage protected by the secular arm, we have
unfortunately been forced to close our eyes when the government meddles with
both hands in church affairs appointing whoever they want to and deposing and
imposing suffering to those who do not wish to go with the flow. Thus
altogether abandoning previously cherished benefits might actually liberate the
church from the unseen hands pressuring and interfering in her internal affairs
which are threatening the church’s spiritual credibility.
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ደግሞ … ታሪካዊና ባህላዊ ሁነቶች ያቀዳጇትን ልዕልናዋን አስጠብቃ ፤ ከመንግስት ጋራ ያላትን ትስስር
አሜን ብላ (አሁን በአንጻራዊ መልኩ እንደሚስተዋለው) የምትቀበል ቢሆን … ቤተክርስቲያኗ እንደ ተቋም … ማኅበረ ቅዱሳንና መሰል
ተቆርቋሪ አካላት … የቤተክርስቲያኒቱን ህልውና ለማስጠበቅ ማንኛውንም ህጋዊና ሰላማዊ ርምጃ ለመውሰድ የሚያስፈራቸውና የሚያሸማቅቃቸው
አንዳችም ጉዳይ ሊኖር በፍጹም አይገባም … ባጭሩ … they have to take measures
to ensure that sagas like Waldiba will never happen again.
በመጨረሻ … በመንፈሳዊ አስተውሎታችን ጎዶሎነት የሚታይብን … የመንጋው ታናናሾች የሆንን … እኛ ክርስቲያን ወገኖቻችሁ
… በዚህ ውጥረት በነገሰበት ዘመን … በመንታ መንገዶች ፊት ቆመናልና … የምንመርጠውንም እንመርጥበት ዘንድ የምንደገፍበትን ግልፅና
አዋጭ አመክንዮ ለማስቀመጥ ባለመቻል … በጨለማ ውስጥ እንገኛለንና … እናንት … በመንፈስ የጎለመሳችሁ … እውቀት ስጋዊ ከእውቀት
መንፈሳዊ የተሰጣችሁ … አባቶቻችን ካህናት … ሊቃውንት መምህራን … ወንድሞቻችን ሆይ … ጨለማችንን የምታርቀውን … ዋጋዋ እጅግ
ውድ የሆነ … መንፈሳዊ ምክራችሁን አሁን እንሻታለን … እንዲህ ባለው አስጨናቂ ጊዜ የትኛውን መንገድ እንከተል ዘንድ ትመክራላችሁ?
… ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ለምትገኝበት ነባራዊ ሁነት ምላሻችን ምን ይምሰል ትላላችሁ? … አባቶቻችንና ወንድሞቻችን ሆይ ዝምታችሁ
ይብቃ … አሁን ድምጻችሁን አሰምታችሁ ተናገሩን … አሁን!!
‘ክርስቲያን ኢትዮጵያዊ
ወይስ ኢትዮጵያዊ ክርስቲያን?
ለኦርቶዶክሳዊው ሰው
በኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ላይ ያልተመሰረተ ኢትዮጵያዊነት ሊኖረው ይችላልን/ይገባዋልንስ!’ … እግዚአብሔር ፈቃዱ ቢሆን በቀጣይነት
በዝርዝር የምንመለስበት ጉዳይ ይሆናል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።
ማስታወሻ፦ ይህ ጽሑፍ ሲዘጋጅ … ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ህልውናዋ እንዲጠበቅ ፤ ብሎም ሀገራችን ኢትዮጵያ
እንደ ሀገር የቆመችበትን መሰረት/አእማድ በማቆምና ማንነቷን በመቅረፅ ረገድ ፤ የነበራትና ያላት ጉልህ አስተዋጽኦ ፤ እውቅና ሳይነፈገውና
ሳይዘነጋ ከትውልድ ትውልድ እንዲሸጋገር በመቅናት … እንዲሁም …
ወቅታዊ በሆኑ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ፤ ምዕመኖቿ የሚሰጡት
ምላሽ ምን ላይ ሊመረኮዝ እንደሚገባው የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ካለ ፍላጎት በመነጨ እንጅ ፤ በሌሎች የእምነት ተቋማት ላይ ግፍንና
ጭቆናን ስለመፈጸም አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል። … ክርስትና እንዲህ ያለውን ድርጊት አያስተምርምና።
I have to admit that I found this blog very impressive than the main stream EOTC blogs. I found non preaching style of teaching Christianity and I am also wondering how the issues you raise are very critical for someone who sink in Internet and west metality like me. keep the good job
ReplyDelete