Pages

Friday, July 12, 2013

‘ጎረቤትህ ሲታማ … ለኔ ብለህ ስማ’

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

‘ጎረቤትህ ሲታማ … ለኔ ብለህ ስማ’


ባለፉት ሃያ አመታት ከተመዘገቡ ለውጦች መካከል በጣም አስገራሚውና አወዛጋቢው … በሮማ ቤተክርስቲያን ላይ … ከቤተ ክህነት አወቃቀም ሆነ ከአስተምህሮ ወጥነት አንጻር የደረሰው ፍጹምና ድንገተኛ ዝቅጠት ነው የለውጡ ዱብ እዳ መሆንም የደረሰውን ዝቅጠት ከፍተኛና የከፋ ያደርገዋል። … ዝቅጠቱ … በቀጣዮቹ የቅርብ ዓመታት የቴሌቪዥን ተመልካቾች በሳሎኖቻቸው ተቀምጠው … ፋይዳ ያለው ነገር ለማድረግ ባለመቻል ስሜት ውስጥ ሆነው … የፓፓውን ባደባባይ መገደል እንዲመለከቱ … ግዙፉ የቅዱስ ጴጥሮስ ካቴድራል አለም አቀፍ የፈንጂ ኤክስፐርቶች በተጠመዱ ፈንጂዎች ፈራርሶ እንደሚወድም እንዲያሰላስሉ ግድ የሚል … ብሎም እጅግ ተስፋ አስቆራጭ ወደሆነ ቀውስ ሊያድግ የሚችል ዝቅጠት ነው

ነገሮች አሁን ባሉበት ሁኔታ ይህ እየተስተዋለ ያለው ዝቅጠት ይገታ ይሆናል ብሎ ተስፋ የሚያስደርግ አንዳች አመክንዮ ያለ አይመስልም የዚህች ለአደጋ የተጋለጠች ተክርስቲያ አስተዳደራዊ መዋቅር ባለበት ሁኔታ ተጠብቆ ክፍለ ዘመኑን ይሻገራል ብሎ ለመጠበቅም የሚያስችል ምንም ተጨባጭ ምክንያት የለም የሮማ ካቶሊክ ተክርስቲያ ሃይማኖታዊ መንፈሷና እምነቷ አይከስሙም የቅዱስ ጴጥሮስ ዙፋን ተተኪም አይጠፋም ከሚለው እምነቷ አንጻር ወደፊት ምን አይነት ገጽታ ሊኖራት ይችላል የሚለው እንቆቅልሽ በራሱእኛ ዘመናውያኑ በህይወት ዘመናችን ተፈትተው ከማናያቸው እንቆቅልሾች መሃል አንዱ ነው

ተጨባጭ የሆኑ አሀዛዊ ሆኑ ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች ወግ አጥባቂው’ ሮማ ካቶሊክ አእምሮ ለማመን የሚከብዱ ናቸው። የቀሳውስት ፣ የወንድና ሴት መነኮሳት፣ የይማኖት ወንድማማቾች የመካከለኛና ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የግል ኮሌጅ ተማሪዎችአዳዲስ ጥምቀቶችን (የአዳዲስ አማኞችን) ፤ በካቶሊኮች መካከል የተከናወኑ ጋብቻዎች፤ የቆራቢዎች ፤ የንስሐ ገቢዎች፤ እምነታቸውን ያጸኑ/ያረጋገጡ አማንያንን ፤ …  ቁጥር … የሚያሳዩ መረጃዎች ፤ ከ1965 እስከ 1980 ያሉትን አመታት ሚያካልል ግራፍ ላይ ቢቀመጡ  ፤  ግራፉ የሚያመለክተው ፤ ቁልቁል ያለማቋረጥ የሚምዘገዘግ ዝቅጠትን ነው። ነዚህ ወሳኝ መረጃዎች/ጉዳዮች በተጨማሪ ስለ ፍቺ ፣ ወሊድ መቆጣጠሪያ ፣ ጽንስ ማስወረድ ፣ ግብረ ሰዶማዊነት ፣ እና ኮሚኒዝም የሮማ ቤተክርስቲያ አስተምህሮ ሙሉ በሙሉ የማይቀበሉ ካቶሊክ እምነት ተከታዮች መኖራቸውን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል

ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች ‘ስውር’ ነገር ግን ተጨባጭ ተጽእኖ የሚያስከትሉ ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ በአሁኑ ወቅት በተገቢው ሁኔታ ክህነት የተቀበሉ ምን ያህል ቀሳውስት እንዳሉ ማወቅ ፍጹም አዳጋች ነው። ለቅስና የቀረቡ እጩዎችን ክህነት ከሚሰጡት ጳጳሳት በርካታዎቹ ምስጢራትን ለመፈጸም ስልጣት ያላቸው ፤ ቀድሰው የሚያቆርቡና ተነሳሕያንን ከጢአት እስራት የሚፈቱ ቀሳውስትን የመፍጠር እቅድ የሌላቸው ናቸው። ይህ ስልጣን ከሌለ ደግሞ ቅስና የለም ፤ ቅዳሴም ሆነ በንስሐ ስርየት ማግኘትም አይኖርም። የክህነት ተግባር የመፈጸም አቅም ያላቸው አለመሆናቸው ከቤተክርስቲያኒቱ ውጪ ባሉ አካላት እስከዚህም ግምት የሚሰጠው ጉዳይ ባይሆንም የካቶሊክ እምነት ተከታይ በሆነው ምዕመን ዘንድ ግን ይህ ጉዳይ የቤተክርስቲያኒቱን በመንፈስ መሞት የሚያመላክት እውነት ነው።

የቀረቡት መረጃዎች እጅጉን አስደንጋ ቢሆኑም የግዙፉን የሮማ ካቶሊክ አካል ሁለንተናዊ መፈረካከስ በተገቢው ሁኔታ ማሳየት የቻሉ ጠቋሚዎች ግን አይደሉም። … በመላው አለም የሚገኘውና ወደ 740 ሚሊዮን (*) የሚጠጋው የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይ … ከፍተኛ ቁጥር ያለው ፣ እጅግ የተማረ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር የሚችል አዳዊ ይማኖታዊ ተቋምን ይወክላ… ይህንን አሃዳዊ ሃይማኖታዊ ተቋም ፤ የሚያስተዳድረው አካልም ረጅ እድሜ ያስቆጠረና ትልቅ ዝና ካላቸው መናብርት መካከል አንዱ ነው - ቫቲካን። ነገር ግን በጦርነትና በሰላም፣ በረብና በብርካቴ፣ በዝቅጠትና በእድገት ፤ …  ይህን በመሳሰሉ ጉዳዮች ይህ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ ተቋም (የካቶሊክ ምእመን) ይህ ነው የሚባል ትርጉም ያለውና የቤተክርስቲያኒቱን እምነት ታሳቢ ያደረገ … ፅዕ የሚያሳድር አልሆነም። እንዲያውም ይህ የካቶሊክ ማሕበረሰብ በኮሚኒስትና ካፒታሊስት ርእዮተ አለሞች ከሁለት ጎራ የተከፈለ ነው። ይህ ደግሞ በፍጥነት ከተስተዋለው የአምልኮትና የውስጣዊ ታማኝነት መዳከም ይልቅ ይበልጥ አስገራሚ ጉዳይ ነው ምክንያቱም ከጥቂት ጊዜያት በፊት የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያበአለም አቀፍ ፖለቲካና ርእዮተ አለም መስክ ከፍተኛ ተፅዕኖ ታሳድር የነበረች ሀያል ተቋም ነበረችና።

ይህ የታየው መዳከም … ምንም እንኳ ባለፉት ሀያ አመታት ውስጥ ይበልጥ በጉልህ እየተስተዋለ ቢመጣም… የረጅም ዘመናት ለውጥ ውጤት ነው። ዛሬ ላይ ሆነን መለስ ብለን ስንመለከተው ከ400 አመታት ቀደም ብሎ ውጤቱ ሊተነበይ ይችል እንደነበር መገመት አያዳግትም ፤ … ምክንያቱም የሮማ ካቶሊክ አደረጃጀት ያከናወነው 1000 ዘመን እድሜ ያስቆጠረው ሙከራ የከሸፈው በዚያ ዘመን (ከ400 አመታት በፊት) ግድም ነበር ይኸው የካቶሊክ አስተዳደር የሰው ልጅን የፖለቲካ ማሕበራዊ እና የስነ-ባል መስኮች ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር ሞክሮ የነበረ ሲሆን ፤ … በሂደቱም የቤተክርስቲያኒቱን ፤ በአጠቃላይ የክርስትና መርሆዎች እርግፍ አድርጎ አስከመተው ደርሶና ፍጹም አለማዊ ፈርጆችን ይዞ ነበር።

በ1979 መጨረሻ የተፈጠረ እምብዛም ትኩረት ያልሳበ አነስተኛ ክስተት የዚህን ሮማዊ አደረጃጀት ውድቀት ያሰመረ ነበር። ህዳር በባተ በ3ው ቀን 63 የአሜሪካ ዜጎች ቴሂራን በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በአያቶላህ ኮሚኒ አብዮታዊ ካድሬዎች ታገቱ ፤ ይህን ተከትሎም ዳግማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ የቴሂራን ተወካያቸው የሆኑትን አርችቢሾፕ አናቤል ቡግኒኒን በሳቸው ስም ጣልቃ በመግባት ከአያቶላህ (ኮሚኒ) ጋር ታጋቾቹ በሚፈቱበት ሁኔታ እንዲወያዩ ያዟቸዋል። ነገር ግን መፍትሔ ሊገኝ ልቻለም።

“ታላቁ ፓፓ አሁን ገና … ታጋቾች ሲፈቱ ማየት በመውደዳቸው ተገርሜያለ” አያቶላህ ቡግኒኒን ገሰጽዋቸው “ሻሀሁ (የኢራን መሪ) ህዝባችንን በጨቆነ ጊዜ ታላቁ ፓፓ ጣልቃ አልገቡልንም እናንተ ክርስቲያኖች ጠባያችሁ እንደክርስቶስ አይደለም… ኢየሱስ ያደርገው የነበረውን ታደርጋላችሁ ብለን ጠብቀን ነበር … ምክንያቱም እርሱ አለጥርጥር ሻሃሁ ያደርሰው የነበረውን ጭቆና መቃወሙ አይቀርም ነበር … ታላቁ ፓፓና የየሆኑት ክርስቲያኖች እንዲህ የሆኑት ለምንድነው…? የአያቶላህ ጥያቄ ነበር …

ኮሚኒ ቫቲካን ስልጣኗን አለአግባብ ተጠቅማለች ብሎ ጣቱን ቢቀስርም መሰረታዊና አንገብጋቢ ለሆነ አንድ ጥያቄ ግን መልስ አልሰጠም ነበር - የትኛውም ይማኖታዊ ተቋም … ሮማ ካቶሊክ ይሁን እስልምና … አለማዊውን ስልጣን ርካብ መጨበጥ/መቆናጠጥ ይገባዋልን? አያቶላህ ይህን ጥያቄ ያነሳ ዘንድ ፈጽሞ አይደፍርም … ምክንያቱም ለሱ ምድራዊውና መንፈሳዊው ስልጣን ፍጹም አንድ የሆኑ … የአላህ መለያየት የሌለበት አንድ  ስልጣን ሁለት መገለጫዎች ናቸው። ነገር ግን በጥንታዊትዋ የክርስቶስ ተክርስቲያን ዘንድ ይህ እሳቤ ፈጽሞ አልነበረም።

በቤተክርስቲያኒቱ የመጀመሪያዎቹ 250 ዓመታት እድሜ የቤተክርስቲያን አባቶች … አያቶላህ ለጠየቀው ጥያቄ ስለሚሰጡት መልስ አንዳች ማቅማማት/ወላወል አልነበረባቸውም። የቤተክርስቲያኒቱ ስልጣን መንፈሳዊና መንፈሳዊ  ብቻ ስለመሆኑ እርግጠኞች ነበሩ። … ክርስቶስ በስጋዌው ዘመን ሳለ ስለአዲሲቱ መንግስት በአንደበቱ የተናገራቸውን ንግግሮች በሚገባ ያስታውሳሉ - ‘የእግዚአብሔር መንግስት’፤ ‘መንግስተ ሰማያት’ የሚሉትን። እዚህ ላይ ታዲያ ፤ እነዚያ አባቶች ፤ ኢየሱስ ‘የእግዚአብሔር መንግስት’፤ ‘መንግስተ ሰማያት’ ሲል ምን ማለት እንደፈለገ ለመረዳት ይሞት ዘንድ አሳልፎ ከሰጠው ከሮማዊው አስተዳዳሪ ፤ ከጴንጤናዊው ጲላጦስ ጋር አድርጎት የነበረው ቃለ ምልልስ ላይ ይመረኮዛሉ

ጲላጦስ ‘ታዲያ አንተ ንጉስ ነህን?’ በማለት በጠየቀው ጊዜ
“አዎን ነኝ ፤ ነገር ግን መንግስቴ ከዚህች አለም አይደለችም እንደሌሎች መንግስታት ከዚህ አለም ብትሆን ኖሮ አገልጋዮቼ ነጻ ያወጡኝ ዘንድ በወደዱ ነበር …” የክርስቶስ ምላሽ ነበር።

በ67 ዓ.ም በሆነው የሐዋርያው ስምኦን ጴጥሮስ ሞትና በ312 ዓ.ም መካከል ሰላ አንድ ፓፓዎች የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪዎች በመሆን የሮማ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ተሹመዋል። ከመጀመሪያዎቹ አስራ ስምንት ፓፓዎች መካከል አንዳቸውም ተፈጥሯዊ ሞትን አልሞቱም ሁሉም ያለፉት በጭካኔ በግፍ ተገድለው እንጅሰላሳ አንዱም የሮማ ፓፓዎች እያንዳንዳቸው በሕይወት ሳሉ የሰማያዊውን መንግስት ስልጣን ገንዘብ ያደረጉ የነበረ ሲሆን … ሁሉም ቀድመዋቸው የነበሩ አባቶችን አስተምህሮ ሳይበርዙ ሳይከልሱ አስተምረዋል - ይኸውም በእግዚአብሔር መንፈስ መመራትን ፤ በመንግስቱ ስርዓትም መገደብን ዚህ ሚታየው አለም ፍጻሜ በኋላ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ድል አድራጊነት ፤ የኢየሱስን ዳግም ምጽት መጠበቅን ነበር

በ312 ዓ.ም የሮማው ንጉሰ ነገስት ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን ተቀበለ ፤ ከአስር አመት በዋላም ክርስናን የሮማ ግዛት ይፋዊ ይማኖት እንዲሆን አደረገለቀጣዮቹ 1650 አመታት ክርስትና በአውሮፓ ፖሊቲካዊና ማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የፈጠረ ክስተት ለመሆን በቃ። ነዚህም አመታት የሮማ ፓፓዎች በአውሮፓና በምእራቡ አለም እጅግ በጣም ወሳኙን ሚና ከሚጫወቱት ግለሰቦች መካከል ዋነኞቹ ሆነው ነበር።

የሕዳሴ/ሬነሳንስ ዘመን ተብሎ በሚታወቀው የመካከለኛው ዘመን የመጀመሪያዎቹ አመታት ኢየሱስ የመሰረታት ቤተክርስቲያን ፤ እጅግ በተዋቀረ አደረጃጀት ፤ … የስልጣን ተዋረድ የጠበቀች ፣ ማእከላዊ አስተዳደር ያላት በስልጣኗ ፍጹም የሆነች ፤ ስለየበላይነቷ ቀናኢ የሆነች ፣ በአብዛኛው በሹመት ጥቂት ደግሞ በምርጫ የሚሾሙባቸው የአስተዳደር ቦታዎች ያሏት ፣ የዘውዳዊ አገዛዝ ስርአት መገለጫዎችን ሁሉ ያሟላች ፤ … ተክርስቲያን ሆና ብቅ አለች… ኤሪክ ኤም. ደ ሳቬንተም (የተባለ ምሁር) ዘውዳዊ ስርአትን በቅርቡ የተረጎመው “መሰረቱን አስቀድመው በታቀዱ እሳቤዎችና ርእዮተ አለሞች ያደረገ ፣ ተዋረዱን በጠበቀ የአስተዳደር መዋቅር ልውናውን ያስጠበቀ ፣ የማሕበርና ሌሎች የቡድን ጥቅሞች በተራቀቀ ጽንሰ ሐሳብ የተገለጹበት ፣ ተፈጥሮአዊ እድገት የሚያሳይ ፣ መገለጫዎቹን ለማግነንና ለመጠበቅ ትውፊት ላይ የሙጥኝ ያለ ፣ በሕልውናው ላይ ከውጪ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመመከት በጽኑ የሚፋለም/የሚከላከል ፣  ውስጣዊ ሰላሙን በሳብም ሆነ በቁሳዊ መንገዶች ለማስጠበቅ የሚተጋ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስርአት” በማለት ነበር … እንግዲህ በሮማ የምትገኘው የክርስቶስ ቤተክርስቲያንም ፤ ይህን ወደ መሰለ የአገዛዝ ስርአት ነበር አዝጋሚ በሆነ ሁኔታ የገባችው/የተለወጠችው።

ነገር ግን ፓፓዎቹ ወደ ምድራዊ አስተዳደር እጃቸውን ማስገባት ከጀመሩበት ቅፅበት አንስቶ … ጎን ለጎን … የሃይማኖታዊ ተቋማቸውን መንፈሳዊ ልዕልና ለማስጠበቅና ፤ ምዕመኑንም በመንፈሳዊ ስርዓት ለመምራት እንዳይችሉ … ከባድና ቋሚ በሆነ … በማይወልቅ እግረ ሙቅ እግር ተወርች እየታሰሩ ነበር። … ከተለያዩ (ከማይመስሏቸው) ጎራዎች ጋራ ወዳጅነትን ለመፍጠርና ፤ በእነዚህም ጎራዎች ላይ ተፅዕኖ የማሳደር ፍላጎታቸውን ለማርካት … ይማኖታዊ ተልዕኳቸውን/ስልጣናቸውን ወደ ጎን ባሉት መጠንም … እግረ ሙቁ እየጸናና … ከእግራቸው አልፎ ወደ አንገታቸው በመድረስ እያነቃቸው ይሄድ ጀመር። ጭራሽ በጊዜ ሂደት ፓፓዎቹ ራሳቸው … አሉ ተባሉ የፖለቲካ አቋማሪዎች መካከል የሚጠቀሱ ለመሆን በቁ … እስካለንበት ዘመን ድረስም ይህንን ሚና ጨርሰው ትተውት አያውቁም እንዲያውም ከዚያ በተቃራኒው ድርጊታቸው በጊዜ ሂደት ቅቡል እየሆነ ከመምጣቱ የተነሳበማሕበራዊ ጉዳዮች የሚታየው የፓፓዎች ጣልቃ ገብነት ይማኖታዊ መርሆ ተደርጎ ሊቆጠር ምንም አልቀረውም ‘ግሊ አፋሪ ፓብሊሲ’ … የተሰኘ ኢጣልያዊ መሰረት ያለው የቤተክርስቲያኒቱ ብሂል እንደሚያሰምርበት የእለት ተእለት የፓፓዎቹ ትኩረት ማሕበራዊ ጉዳዮች እንደሆኑ የታመነበት ጉዳይ ነበር። መሰረታዊ የክርስትና እሴቶች ለአደጋ በተጋለጡባቸው ወቅቶች እንኳ ፓፓዎቹ አቋም ከመያዛቸው አስቀድሞ ዲፕሎማሲያዊ አሰላለፎችን ፣ አጋር ወገኖች የጣሉባቸውን ድርሻ /ክለብ ኦብሊጌሽንስ/ ፣ ፖለቲካዊ ስምምነቶችን ፣ ባሕላዊ ተዛምዶዎችን ፣ የድምበር ይገባኛል ጥያቄዎችን ፣ ኢኮኖሚያዊ ጥቅማ ጥቅሞችን ፣ የግል ምኞታቸውን ፣ የቤተሰቦቻቸውን እቅድ፣ የግዛት ማስፋፋት ሳቦቻቸውን ግምት ውስጥ ማስገባታቸው አይቀሬ ነበር

ሃይማኖታዊው አስተዳደር ከምድራዊው ጋር በመጋባቱ ምክንያት የተከተለው በእግረ ሙቅ የመቀፍደድ አጋጣሚ ፤ ታላቁን የፍቅር ግና ከፍተኛ የስነ ምግባር አስተምህሮዎች ይሰብኩ በነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶች ላይ ምን ያህል ሊከብና ሊያጎብቸው እንደሚች ያለፉ ፓፓዎች ሕይወት በገሀድ የሚገልጸው እውነት ነው። በታሪክ ድርሳናት በርካታ ምእራፎች እንደሚስተዋለው ፓፓዎቹ ምድራዊ ስልጣንና ብትን ከቤተክርስቲያኒቱ ጫንቃ ላይ አውርዶ ለመጣል … ከሰው ልጅ ድጋፍና ስጋዊ ከለላ ተላቃ መንፈሳዊ ልዕልናዋን ጠብቃ በራሷ እንድትቆም … ጸንታ እንደምትኖር ኢየሱስ ለቤተክርስቲያኑ ገባው ቃል ኪዳን ላይ ብቻ እንድትኖር ፤ እና የፈቀደላትን የመንፈስ ቅዱስ ስልጣን ብቻ እንድትጠቀም …  በርካታ አጋጣሚዎች ተፈጥረውላቸው ነበር ፤ … አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ እነዚህ መልካም አጋጣሚዎች የተፈጠሩት ፓፓዎ ምድራዊ ገዢዎች እንደሚያደርጉት በፖለቲካ ስልጣን ውስጥ ገብተው ሲያቋምሩ ፤ ቁማራቸው ከሸፎ/ባርቆ አስከፊ መዘዝ ባስከተለባቸው ጊዜያት ነበር። የሮማ መሪዎች ግን ባንጻሩ … በአጋጣሚዎቹ ላይ ፊታቸውን ሲያዞሩና ፤ ጭራሽ ያጡትን ማንኛውንም ምድራዊ ስልጣንና ተቀባይነት መልሰው ለማግኘት ሲፋለሙ ፤ ይኸውም በአመዛኙ ሲሳካላቸው እንመለከታለን። … የተሻሉ የሚባሉትም /መልካሞቹ?/ እንኳን  … ፓየስ 9ኛ እና ፓየስ 12ኛ ለምሳሌ … ምድራዊ ስልጣን መጠቀምን ሙሉ ለሙሉ  እርግፍ አድርገው ሊተዉ አልወደዱም።  ባጠቃላይ ክፍለ ዘመናቱ የነበሩት ፓፓዎች መርሆዋቸው የነበረው ያጡትን ማንኛውንም ስልጣን መልሰው ለማግኘት የተቻላቸውን ያክል መጣር ነበር

እንዲህም ሆኖ … በአመዛኙ የተዳፈነ ቢሆንም እንኳ ሁሌም የቤተክርስቲያኒቱ ሃይማኖታዊ (መንፈሳዊ) ግዳጅ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰውን … ይህን የሃይማኖታዊ አስተዳደርና ምድራዊ ስልጣን ቁርኝት የመስበር ፍላጎት ይስተዋል ነበር። ታላቁ የፍሎረንስ /ጥልያን/ ተወላጅ ባለቅኔ ዳንቴ አሊግዬሪ ‘ዘ ኢንፈርኖ’ በተሰኘው ድርሰቱ ይህንን ጉዳይ … ‘የመጀመሪያው ባለጸጋ የቤተክርስቲያን አባት’ በሚላቸው እና ከንጉሰ ነገስት ቆስጠንጢኖስ ጋር ባደረጉት ስምምነት… ቤተክርስቲያንን ከነበረችበት የምድራዊ አስተዳደር ታዳኝነት በቅጽበት … ያድናት የነበረው አካል ባልንጀራና ፤ የዚሁ አካል የመንፈሳዊና ግብረገብ አስተምህሮ መሰረት ወደመሆን እንድትለወጥ … ባደረጓት ፓ ሲልቨስተር 1ኛ ላይ ትኩረት ባደረጉ ጥቂት ስንኞች ጉዳዩን እንደሚከተለው ይገልጸዋል
Ahi! Costatin! Di quanto mal fu matre
Non la tua conversion, ma quella dote
Che da te presse il primo rico patre!

ወዮ! ቆስጠንጢኖስ! ወደዚች ዓለም ምን አይነት ክፋት አመጣህ!
(ክርስትናን) በመቀበልህ/በጥምቀትህ/ አይደለም ፤ በዚያ ጥሎሽ ነው እንጂ፤
የመጀመሪያው ባለጸጋ አባት ካንተ በተቀበለው!’

ልክ እንደ ዳንቴ ሁሉ … ባለፉት ክፍለ ዘመናት በነበሩ በርካታ ካናትና ምእመናንም እምነት … በጎች እንደ አንበሳ ለመሆን በጣሩ ጊዜ ሁሉ እንደአህያ የመሆን ውርደት መጎናጸፋቸው አይቀሬ ነው።

ማስታወሻ፦ በ(*) ምልክት የተቀመጠውና 760 ሚሊዮን የሚለው አሃዛዊ መረጃ የመጽሐፉ አዘጋጅ መጽሐፉን ባዘጋጀበት ዓመት ግድም ፤ ይኸውም ከ33 ዓመታት በፊት የተወሰደ አሃዛዊ መረጃ ነው።

The Decline and Fall of The Roman Church
By: Malachi Martin, 1981
(The Breakdown - የመጽሐፉ መግቢያ)

መግለጫ፦

የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ሆይ … የመጽሐፉ አዘጋጅ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ በግልጥ ካስቀመጠውና ፤ ሃይማኖታዊው አስተዳደር ከምድራዊው ስልጣን ጋራ በመቆራኘቱ … ተቀባይነትንም ከምድራውያን ለማግኘት በመታተሩ ምክንያት ፤ በተከሰተው የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ልዕልና ማጣት እና የሃይማኖታዊ እሴቶች መበላሸት (መጥፋት) መነሻነት፦ (ከብዙ በጥቂቱ)

የካቶሊክ ቤተክርስቲያን …
1.      በወግ አጥባቂዎች …
2.     በአዲሱ ቅዳሴ አማኞች (ኖቨስ ኦርዶ)/በፓፓው ታማኞች
3.     በሴዴቫካንቲስቶች (ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በኋላ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ባዶ ነው ብለው በሚያምኑ)
4.     በፓዬስ 9ኛ ማኅበርተኞች … ለ4 ስትከፋፈል
የራሽያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ደግሞ …
1.      በጆሴፋይቶች (የካታኮምብ ክርስቲያኖች)
2.     በሞስኮ ፓትሪያሪኬት ታማኞች
3.     በዲያስፖራ የራሺያ ኦርቶዶክሶች … ለ3 ተከፋፍላለች።
የግሪክ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም እንዲሁ …
1.      ኦልድ ካላንደሪስቶችና
2.     ኒው ካላንደሪስቶች ተብለው ለሁለት ተከፍለዋል።
የእኛስ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምን ዓይነት ጎዳና ላይ እየተጓዘች ነው? … ለመሆኑስ የሮማ ፤ የራሽያና ፤ የግሪክ ቤተክርስቲያናት ከተጓዙበትና ለውድቀት ከዳረጋቸው መንገድ የተለየ መንገድን መርጣለችን? …  በቤተክርስቲያኗ የውስጥ ጉዳዮች ላይ (የፓትሪያሪክ የምርጫ ሂደትን ጨምሮ) የመንግስት ጣልቃ ገብነት/ተፅዕኖ በግልፅ አይስተዋልምን? … ቁልፍ የሆኑ የአስተዳደር ቦታዎቿስ በመንግስት ጉዳይ አስፈጻሚዎች አልተያዙምን? መንፈሳዊ ግዳጇንስ ፤ ከመንግስት አጀንዳዎች ጋራ የማይጋጩ/የማይጣረሱ እስካልሆኑ ድረስ ብቻ የምትፈፅም አልሆነችምን? … መጭውስ ጊዜ ለቤተክርስቲያናችን ምን መልክ የሚኖረው ይመስላችኋል? …. ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ …

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።


No comments:

Post a Comment