Pages

Friday, March 7, 2014

ቴክኖሎጂ ያዘመነው የእኛ ትውልድና ፤ ሚዲያ መራሹ ማሕበራዊ ምስቅልቅል Part 3

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡


“ወበከመ ኢሐለይዎ ለእግዚአብሔር በልቦሙ ከማሁ እግዚአብሔርኒ ወወሀቦሙ ልበ እበድ ፤ … እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሰሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው”
ሮሜ 1፡-28-29


" … I may not get there with you. But some day we shall enter the promise land where men and women will not be judged by their sexual desires but by the content of their character.... (ያችን ቀን )… በሕይወት ኖሬ … አብሬያችሁ ላላያት እችላለሁ ፤ ነገር ግን … አንድ ቀን … ወንዶችና ሴቶች … ባላቸው ጾታዊ ፍላጎት ሳይሆን … በስብናቸው ጥንካሬ ወደሚመዘኑባት የቃል ኪዳን ምድር እንገባለን" ... ይህ የንግግር ክፍል … ከዛሬ ሃያ አመት በፊት … ሌሪ ክሬመር  የተባለ … የግብረ ሰዶማውያን መብት ተሟጋች … ዋሽንግተን ዲ.ሲ. በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ተገኝቶ … ካሰማው ንግግር ላይ የተወሰደ ነው። … በወቅቱ … ይህ የ/ር ክሬመር ንግግር … ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ንግግር በቀጥታ የተቀዳ … የተውሶ ንግግር እንደነበረ … ከበርካ ታዳሚዎቹ የተሸሸገ አልነበረም። …  ያም ሆኖ … ሌሪ የዶ/ር ማርቲንን ንግግር ሆን ብሎ በማዛባት " የቆዳ ቀለም" በሚለው ፋንታ "ጾታዊ ፍላጎት" ሚለው ቃል መተካቱን ግን ያስተዋሉ ጥቂቶች ነበሩ:: … እንግዲህ በዚህ እሳቤ ነበር  (እ.ኤ.አ) በ1993 ዓ.ም  የተካሄደው ‘ማርች ኦን ዋሺንግተን’ የተሰኘው ታላቁ የግብረ ሰዶማውያን ሰላማዊ ሰልፍ … ዓላማውን … የወንድና ሴት ግብረሰዶማውያንን ፤ ፆታቸውን በህክምና ያስቀየሩ ግለሰቦችንና ፤ የባይሴክሺዋሎችን መብት ማስከበር ላይ አድርጎ … ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው::


‘ማርች ኦን ዋሽንግተን’ የተሰኘው … ይህ የግብረ ሰዶማውያን ሰላማዊ ሰልፍ ከመካሄዱ ከ30 ዓመታት በፊት … ጥቁር አሜሪካውያን … በታዋቂው የጥቁሮች መብት ተሟጋች … ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እየተመሩ … ባካሄዱት ከፍተኛ የትግል እንቅስቃሴ … የዘር መድልዎን ለማስቀረት በእጅጉ አስፈላጊ የነበረው … ‘የማሕበራዊ መብት ረቂቅ’ (Civil Rights Act) … (እ.ኤ.አ) በ1964/65 እንዲተላለፍ ማድረግ ችለው ነበር ፤ … በተመሳሳይ መልኩ … የግብረ ሰዶማውያኑና የሌሎች ጾታዊ ጠባይ ግድፈት ያለባቸው ግለሰቦች ጥምረት … የዶ/ር ማርቲንን ንግግር ከመኮረጃቸውና ፤ ከሌሎች መሰል ጥረቶቻቸው እንደተስተዋለው … ዋና ፍላጎታቸው … የ1964ቱን የጥቁር አሜሪካውያን የሰብአዊ መብት የትግል ፈለግ በመከተል … ጥቁሮች ያሳኩትን ግብ … ይኸውም … በአናሳ ማሕበረሰብነት የሕግ እውቅና የማግኘት ድል … መቀዳጀት ነበር:: … እዚህ ላይ ታዲያ ልብ ሊባል የሚገባው ነጥብ … ጥቁር አሜሪካውያኑ … በአናሳ ማሕበረሰብነት የመታወቅ ሕገ መንግስታዊ መብት ለማግኘት የቻሉት … በቀድሞ ታሪካቸው ከደረሰባቸው የዘር መድልዎና ጭቆና የተነሳ መሆኑ ነው፡፡


ንጻሩ … የግብረ ሰዶማውያንና የሌሎች ጾታዊ ጠባይ ግድፈት ያለባቸው ግለሰቦች መብት ተሟጋቾች … በአናሳ ማሕበረሰብነት ለመታወቅ ሽተው አደባባይ የወጡት ግን … እንደ ጥቁር አሜሪካውያኑ የእኩልነት መብት ማስከበር አልነበረም … ምክንያቱስ … ሀገሪቱ ሕግ በ1ኛ እና 14ኛ የሕግ ማሻሻያዎች (ammendments)እንዲሁም በእያንዳንዱ የአሜሪካ ክፍለ ግዛት ሕገ መንግስት ላይ ይህ የእኩልነት መብት ከተረጋገጠላቸው ቆይቶ ነበርና ነው:: … እውነተኛውና እኩዩ ዓላማቸው ግን …  የተለየ እውቅና መብትና የሕግ ከለላን በማግኘት በአብዝሃው ሕብረተሰብ ዘንድ እንደጋጠወጥነት የሚታየውን የአኗኗር ዘቸውን አለአንዳች እንቅፋት እንደልባቸው ማስፋፋት ነበር::

ለመሆኑስ … ይህን አናሳ ማሕበረሰብነት የመታወቅ ልዩ ቸሮታ ሊያገኙ በእርግጥ ይገባቸው ነበርን? … እውንስ … በነቂስ ወደ ዋሽንግተን የሕግ መወሰኛ ም/ቤት ያወጣቸው ጉዳይ … ጥቁሮች እንደደረሰባቸው አይነት ያለ ግፍና መድልዎ ደርሶባቸው ነበርን? … ጥቁር አሜሪካውያ ለዘመናት ሸከመውት የኖሩትስ … ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ጭቆና ቀንበር .. በግብረ ሰዶማውያኑ ጫንቃ ላይ በርግጥ አርፎ ነበርን? … እንዲያውም!! …  በአሜሪካ ይህን ዘመቻ ያካሄዱ … የእነዚህን ግብረ ሰዶማውያን እውነተኛ የኑሮ ገጽታ ንመለከት … ‘ተጨቁነናል’ የሚለው እሮሯቸው ግልፅ የወጣ ውሸትና ተራ ጩኸቴን ቀሙኝ እንደሆነ እንረዳለን። … ይህም … እነዚህ ወገኖች በእኛም ገር … ጆሮ የሚሰጣቸው ቢያገኙና የፖለቲካ መዘውሩን ቢቆጣጠሩ … ምን ሊከሰት እንደሚችል የሚጠቁም ጥሩ ማሳያ ነው:: … ለአብነት በዎል ስትሪት ጆርናል ላይ የተዘገበንና ፤ በግብረ ሰዶማውያንና አፍሪካ አሜሪካውያን (ጥቁሮች) መካከል የተደረገን … የንፅፅር ዳሰሳ ጥናት ውጤት እንመልከት፦

ቁጥር
ጠቋሚዎች
ግብረ ሰዶማውያን
አፍሪካ አሜሪካውያን/ጥቁሮች/
1
አማካይ የነፍሰ ወከፍ ገቢ
$ 55,430
$12166
2
የኮሌጅ ተመቂዎች /በፐርሰንት/
60%
5%
3
በሹመት/በእልቅና መደብ ላይ/ ያሉ በፐርሰንት/
49%
1%
4
ለመዝናናት ባሕር ማዶ ወዳሉ አገሮች የተጓዙ
66%
1%
5
የመምረጥ መብት ተነፍጓቸው ነበርን?
አልተከለከሉም
አዎ
6
ማሕበራዊ ሽንት ቤቶችን እንዳይጠቀሙ ታግደው ነበር?
አልተከለከሉም
አዎ
7
ንግድ ቤቶችና ምግብ ቤቶች እንዳይገለገሉ ተከልክለው ነበር?
አልተከለከሉም
አዎ

ከጥናቱ ውጤት በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ወንዶችም ይሁኑ ሴ ግብረሰዶማውያን እንደጥቁሮቹ መኖርያ ያጡ ስርቻው መጠለያ ድንኳን ቀልሰው የሚኖሩ … አልያም እርጥባን ፍለጋ በየእርዳታ ድርጅቶች በራፍ ላይ … ረጃጅም ሰልፍ ሰርተው የምናገኛቸው አይደሉም:: ነዚህ ሰዎች ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ፣ ከፍተኛ የትምህርት እድል ተጠቃሚ የሆኑና ፤ ሀብትና ስልጣ የሚያስገኘውን የቅምጥል ኑሮ የሚኖሩ ናቸው… ብቸኛ አላማቸውም ከተሉት ተፈጥሯዊ ያልሆነ የአኗኗር ሁኔታና ጾታዊ ተራክቦ በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ላይ ማስረጽ ተቀባይነት እንዲኖረው ማስቻል  ነበር … በሌላ አነጋገር … የባሕልና የአመለካከት የበላይነት መቀዳጀት ነበር።

ግብረ ሰዶማውያኑና ሌሎች የተዛባ ጾታዊ ግንኙነት ፈጻሚዎቹ … ይህን ተፈጥሯዊ ያልሆነ ባህልና አመለካከታቸውን በአብዘሃው ላይ ለማስረጽ ካደረጓቸው የዘመቻ እንቅስቃሴዎች አንዱ በሆነውና ‘ማርች ኦን ዋሽንግተን’ በተሰኘው የ1993ቱ ሰልፍ ላይ … ቁጥራቸው 300,000 የሚደርሱ ሰዎች የተካፈሉ ሲሆን ፤ … በወቅቱ … የሰልፉ አዘጋጆች የተሳታፊውን ቁጥር ለማብዛት  በግብረ ሰዶማውያ የሕትመት ውጤቶች ላይ ሙሉ ገጽ ማስታወቂያዎችን መስራታቸው የሚታወስ ነው:: … ማስታወቂያዎቹን ተከትሎም …  በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ግብረሰዶማውያን እና ሌሎች የተዛባ ጾታዊ ግንኙነት ፈጻሚዎች በዋና ከተማዋ ተገኝተው ነበር ሲሆን ፤ … አብዘሃኛዎቹም ከሰልፉ ጋር ተያይዞ የሚኖረውን ልቅ የግብረ ስጋ ግንኙነት ተስፋ በማድረግ የመጡ ነበሩ:: … ሰልፉ … ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት በአለ ሲመት አዘጋጅ ኮሚቴ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከፊል ወጪው የተሸፈነለት ሲሆን … ዋነኛ አላማው የነበረውም … ሕግ አርቃቂ ተቋም ላይ ጫና በማሳደር ለጆሮ የሚከብዱ የግብረ ሰዶማውያኑ ጥያቄዎ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ ነበር::

የሰልፉ አዘጋጆች በስራቸው 55 ንዑሳን ጥያቄዎችን ያካተቱ 7 ዓበይት የግብረ ሰዶማውያንና ሌሎች መሰል የተዛባ ጾታዊ ጠባያት ያሏቸው ጎራዎችን ፍላጎት የሚያስተጋቡ ጥያቄዎች ይዘው የቀረቡ ሲሆን ፤ … ያቀረቧቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ነበሩ፦

1.     ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያግዱ ማናቸውም አይነት ሕግጋት እንዲሻሩና ሁሉም አይነት ጾታዊ ተራክቦዎች በሕግ የተፈቀ እንዲሆኑ (በዚህ ጥያቄ ስር ይስተካከሉ ያሏቸው በርካታ ጉዳዮች ካተቱ ሲሆን ነዚህም መካከል)
1.1.  ጾታዊ ግንኙነት የሚፈቀድበት የእድሜ ገደብ እንዲቀየር፤
1.2. የአለባበስ ስርአትን የሚገድበው ሕግ ተሸሮ ማንኛውም አይነት ልብስ የመልበስ ነጻነት እንዲኖር፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል። … ይኸውም … እርቃን መሄድና ከሕጻናት ጋር ዝሙት መፈጸምን (pedophilia) የመሰሉ እኩይ ፍላጎቶቻቸው እንዲፈቀዱላቸው በማሰብ የጠየቁት ለመሆኑ አይጠረጠርም።
2.    ግብር ተሰብስቦ ከተገኘው ገቢ ላይ ፤ ለኤድስ ታማሚዎች የሕክምና ወጪ ለመሸፈን የሚውል በጀት እንዲያዝ(በዚህ ከላይ ሲታይ ሰብአዊና አግባብ የሆነ በሚመስለው ጥያቄያቸው ስር ሌሎች አጸያፊ ጉዳዮችን ያካተቱ ሲሆን … ለአብነትም)
2.1. ከግብ ሚገኘው ገቢ ጾታቸውን የሚቀይሩ ግለሰቦች ሚያካሂዷቸው ቀዶ ጥገናዎች ወጪ  ፈሰስ እንዲደረግ
2.2.ከግብ ሚገኘው ገቢ እጽ ተጠቃሚዎች ለሚያስፈልጋቸው መርፌ መግዣ እንዲውል፤ የሚሉት ይገኙበታል።
3.    ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ግለሰቦች መካከል የሚከናወን ጋብቻ በሕግ ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው፤ ልጆችን በማደጎነት የማሳደግ መብት እንዲኖር፤
4.    ግብረሰዶማውያንና ማንኛውም አይነት ጾታዊ ተራክቦ የሚፈጽሙ ግለሰቦች በት/ት ቤቶች፣ በሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከላት እና በት/ቤት የምክር አገልግሎት ፕሮግራሞች ውስጥ አለገደብ እንዲሰማሩ እንዲፈቀድ
5.    በማንኛውም የእድሜ ደረጃ ያሉ ሴቶች የወሊድ መቆጣጠሪያ አቅርቦቶች ና ልቅ የውርጃ አገልግሎቶች እንዲያገኙ
6.    መንግስት ከግብር ከሚያገኘው ገቢ ፤ … የሴት ግብረ ሰዶማውያን ሰው ሰራሽ የጽንስ የማሳደር ዘዴ (artificial insemination) ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ የሕክምና ወጪያቸው እንዲሸን፤ በተጨማሪም ይማኖታዊ መርሆዎችን መሰረት ያደረጉ በግብረ ሰዶማውያን ላይ የሚሰነዘሩ ተቃውሞዎች በሕግ እንዲታገዱ
ሁሉም ድርጅቶች (የግልም ይሁኑ የመንግስት) ግብረ ሰዶማውያን ሰራተኞችን የመቅጠር ግዴታ እንዲኖርባቸው


የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን … ይህ … ከመነሻው ጀምሮ ተገቢነት የጎደለውና ቅጥ ያጡ ጥያቄዎች የቀረቡበት … ‘ማርች ኦን ዋሽንግተን’ የተሰኘ ዘመቻ … የተካሄደው ከ20 አመታት በፊት እ.ኤ.አ. 1993 ዓ.ም መሆኑን ተከትሎ … በአንድ ወቅት እንደተከሰተ ቅጥያ አልባ ግንጥል ታሪካዊ ስህተት አድርገን ልንወስደው እንችል ይሆናል ፤ … እውነታው ግን … ከዚያም በኋላ ቢሆን እነዚህ እኩይ አጀንዳ ያነገቡ ግብረ ሰዶማውያን እጃቸውን አጣጥፈው አለመቀመጣቸው ነው ፤ … በ2000 ዓ.ም በአሜሪካ ብቻ የ1993ቱን የመሰ ግዙፍ ሰላማዊ ሰልፍን ያደረጉ ሲሆን ፤ … በዚህ ሳይወሰኑም … በገንዘብ በመደለል ፤ የተለያዩ የፕሮፓጋንዳ መጻሕፍትና የሕትመት ውጤቶችን በማሰራጨት ፤ እንዲሁም ከፍተኛ መዋእለ ንዋይ በማፍሰስ የመገናኛ ብዙንን መቆጣጠር ፤ … በተቀረው አለም ጭምር … በተለይም በምዕራቡ አለም ማህበረሰብ ዘንድ … የግብረ ሰዶማውያን አኗኗር … አስነዋሪነቱ ተዘንግቶ አወንታዊ ፋይዳ እንዳለው ድርጊት … ቅቡል እንዲሆን ከማድረግ አንጻር ብዙ ርቀት ተጉዘዋል:: … እንዲያውም ይህ እንቅስቃሴያቸው … ስም በማጥፋት ፤ በማዋከብና ፤ የአንደበትና የጉልበት ዛቻዎችን በመሰንዘር የታጀበ ለመሆኑ እማኝ አያሻውም ፤ … ይህን ተከትሎም በውጤቱ … በበርካታ ሀገራት ግብረ ሰዶም መፈጸም ሕጋዊ የተደረገ ሲሆን ፤ … በግብረ ሰዶማውያን መካከል የሚደረግን ጋብቻ የፈቀዱ ፤ ተቃውሞ የሚያቀርቡ አካላትንም ለመቅጣት ሕግ ያወጡ ሀገራት ቁጥር ትንሽ አይደለም።

እስኪ አሁን ደግሞ … ግብረ ሰዶማውያ እያደረሷቸው ካሉ ፈርጀ ብዙ አሉታዊ ተጽኖዎች መካከል … ለአብነት ያህል የተወሰኑትን አንጻራዊ በሆነ ጥልቀት ለመመልከት እንሞክር፤

የመገናኛ ብዙንን በመጠቀም እደረሱት ያለ የባሕል ወረራ

የውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚጠቁሙት … የአለምን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስርአት በመቀመር ፤ ቅኝቱን በማስተካከልና ፤ ሚዛኑን በመጠበቅ ረገድ … ወሳኝ ሚና ከሚጫወቱ ልሂቃን መካከል በርካታዎቹ … ግብረ ሰዶማውያን ናቸው:: … እነዚህ ሃያላን ታዲያ … የግብረ ሰዶማውያን አጀንዳ … በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲስፋፋ … የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም ፤ … በመዳፋቸው ያለውን ሀብትና ሥልጣን እንኳን ለመጠቀም … ማቅማማት አይታይባቸውም። … ይህንኑ አላማቸውን ከግብ ለማድረስ ታዲያ … በርካታ መዋእለ ንዋይ ካፈሰሱባቸው መስኮች … ዋነኛውና ተቀዳሚው … የመዝናኛ ኢንዱስትሪው ነው:: … በዚህ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ መስክ … ማንኛውንም ዓይነት የምስል ወድምጽ ውጤት … ክፉና ደጉን ለማይለዩ ሕጻናት ከሚዘጋጁ የካርቶንና አኒሜሽን ፊልሞች አንስቶ … የአፍላ ወጣቶችንና ጎልማሶችን ቀልብ እስከሚገዙት … ፊልሞች … ሙዚቃዎች … የሙዚቃ ቪዲዮዎች … ቃለ መጠይቆችና … የማሕበራዊ ቶክ ሾው ዝግጅቶች ድረስ ብትመለከቱ … ግብረ ገባዊ ፣ ባህላዊና ፤ ሃይማኖታዊ እሴቶችንና ትምህርቶችን በሚንዱ … ባጠቃላይ … የግብረ ሰዶማውያን አኗኗር ተቀባይነት እንዲያገኝ ብቻ ሳይሆን … ተመራጭ የሕይወት መንገድ እን ሚሰብኩ … ፕሮፖጋንዳዎች የተሞሉ እንደሆኑ … በቀላሉ መረዳት ትችላላችሁግብረ ሰዶማዊቷ መምህርት /ር ቨርጂኒያ ዩሪብ “This is war… As far as I am concerned, there’s no room for conscientious objectors. We’ve got to be involved in this war. … ያለነው ጦርነት ውስጥ ነው… እስከሚገባኝ ድረስበጦርነት ውስጥ ለሕሊና ቦታ የምንሰጥበት አንዳችም ምክንያት የለም ፤ ግብረ ሰዶማውያን ሁላችን … በዚህ ጦርነት ውስጥ ልንሳተፍ ይገባል::’ በማለት በማያወላዳ ሁኔታ እንዳስቀመጠችው ፤ … የግብረ ሰዶማውያኑ ጥምረት … በተቀረው ማሕበረሰብ ላይ ግልጽ የሆነ ጦርነት ያወጀበት ዘመን ላይ እንገኛለን ፤ … መገናኛ ብዙሃኑንም እንደ አንድ መሳሪያው እየተጠቀመበት ይገኛል። … ከዚህ በመቀጠል … በግብረ ሰዶማውያኑ እየተሰነዘ ያለው ጥቃት … ምን ያህል የከፋ እንደሆነ መረዳት ይቻል ዘንድ … የተወሰኑ የምስል ወድምፅ ውጤቶችን ለአብነት እናቀርባለን

[BERT & ERNIE]




ይህ … ‘ሲሰሚ ስትሪት’ (Sesame Street) የተሰኘ ካርቶን ፊልም … በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን … የልጆች ክፍለ ጊዜ … ለረጅም ጊዜ ይተላለፍ የነበረ … ተከታታይ ፕሮግራም ነው። … ታዲያ በዚህ የካርቶን ፊልም ላይ … ርኒ የተሰኘና የወንድ ጾታ የተላበሰ አሻንጉሊት በርት የተሰኘን የሌላ ወንድ አሻንጉሊት የሰውነት ክፍሎች በጨዋታ አመካኝቶ ሲዳስሰው በስተመጨረሻም ፍረቱን እንደዳሰሰው በአንደበቱ ሲገልጽ ይታያል ፤ … ይህ አድራጎት … መልካምና ክፉውን በማያመዛዝኑት ጨቅላ ሕጻናት አእምሮ አንዱ የሌላውን የአካል ክፍል መዳሰስ ይችላል የሚል መልእክት የሚያስተላልፍና … ፍጻሜውም በወንዶች መካከል ሊፈጠሩ ወደሚችሉ አሳፋሪ ግብራት የሚመራ የጭቃ እሾህ መሆኑን ለመገንዘብ አያዳግትም ::

 [OPRAH -  The Oprah Winfrey Show


በዚህ ዝነኛ ቶክ ሾው … አንድ … የግብረ ሰዶማዊነት ፍትወት በውስጡ የተጸነሰ … ነገር ግን በሕሊና ወቀሳ ምክንያት ለመወሰን ግራ የተጋባ ወጣትን አስመልክቶ … ሁለት የፕሮቴስታንት ፓስተሮች … ከዝነኛዋ ኦፕራ ዌንፍሬይ ጋር በሚያደርጉት ውይይት …. የግብረ ሰዶማዊነትን ኢ-ተፈጥሯዊነት በመካድ … እንሰብከዋለን በሚሉትም መጽሐፍ … በመጽሐፍ ቅዱስ … የተቀመጡትን ትእዛዛት ወደጎን በመተው አለአንዳች ፍረት ግብረሰዶማዊነት ከአምላክ የተሰጠ ልዩ ስጦታ እንደሆነ ሲናገሩ እናያቸዋለን። … ውድ አንባብያን ወገኖቻችን …. ይህን የተነወረ ጾታዊ ተራክቦ በተመለከተ … አላማቸው ግራ የሆነ ሰዎች … ብዥብዥታን ለመፍጠር የማይፈነቅሉት ድንጋይ … የማይምሱትም ጉድጓድ የለም … ለመሆኑ ቅዱሱ መጽሐፍ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የሚያስቀምጠው ነገር ሁለትና ሦስት ትርጉም የሚያስከትል … ያልተገለጠ የሚብራራ ነውን? … በጭራሽ!! … ለአብነት የተወሰኑትን ጥቅሶች እናስታውሳችሁ …

“ጽራሖሙ ለሰዶም ወለገሞራ በጽሐ ኀቤየ ወኀጢአቶሙኒ በዝኃት ጥቀ ፤ … የሰዶምና የገሞራ ጩት በእኔ ዘንድ በዛ ፤ ሐጢአታቸውም እጅግ ከበደች”
                        ዘፍ 18፡-20

“ወምስለ ተባዕት ኢትስክብ ከመ አንስት እስመ ርኩስ ውእቱ ፤ … ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ ፤ ጸያፍ ነገር ነውና።’’
ዘሌ 18፦22

“ወለእመቦ ዘሰከበ ምስለ ተባዕት ከመ አንስት ርኩሰ ገብሩ ሞተ ለይሙቱ ክሌኤሆሙ ጊጉያን እሙንቱ ፤ …. ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል ፤ ፈጽመው ይገደሉ በደለኞች ናቸውና” ዘሌ 20፡-13

 “ወከማሁ እደዊሆሙ ኀደጉ አንስቲያሆሙ ወነዱ በፍትወቶሙ ወገብኡ በበይናቲሆሙ ብእሲ ላዕለ ብእሲ ኀሣሮሙ ገብሩ ወባሕቱ ይረክቡ ፍዳሆሙ ወይገብእ ጌጋዮሙ ዲበ ርሶሙ ወበከመ ኢሐለይዎ ለእግዚአብሔር በልቦሙ ከማሁ እግዚአብሔርኒ ወወሀቦሙ ልበ እበድ ፤ … ስለዚህም እግዚአብሔር ክፉ መቅሰፍትን አመጣባቸው ፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባቸውን ትተው ለባሕርያቸው የማይገባውን ሰሩ … ወንዶች በወንዶች ላይ የሚያዋርዳቸውን ነውር ሰሩ ፤ ነገር ግን ፍዳቸውን ያገናሉ ፤ ፍዳቸውም በራሳቸው ይመለሳል ፤ እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱ መጠን እንዲሁ እግዚአብሔር ይህን የማይገባውን ይሰሩ ዘንድ ሰነፍ አእምሮን ሰጣቸው”
ሮሜ 1፡-26-29

[HOMIES OVER HOES] 



ሆሚስ ወቨር ሆ(ር)ስ በካርቶን ምስል የታጀበ የሙዚቃ ቪዲዮ ሲሆን … በውስጡም ዘፋኝ ራፐሮቹ … ሴቶችን ከክለባቸው እያወጡ ሲወረውሯቸውና … ከነሱ ጋር ከመሆን ይልቅ ከወንድ ጓደኞቻቸው ጋራ መጫወትን እንደሚመርጡ ሲያውጁ ያሳያል:: የዘፈኑ ርእስ የሙዚቃ ቪዲዮውን ዋና መልእክት ግልጽ አድርጎ እንደሚናገረው ሆሚስ ወቨር ሆ(ር)ስ ማለት … ከሴት አዳሪዎች ጋር ከሆን … ከሰፈር የወንድ ባልንጀሮቼ ጋር መሆን ይሻለኛል እንደማለት ሲሆን ፤ ቪዲዮው ላይ … ወንዶቹ እርስ በርሳቸው ደረት ለደረት ሲጋጩ የሚታዩበት ትዕይንት … የወጣቶቹ የእርስበርስ ግንኙነ ከተራ ወዳጅነት ዘለለ ጾታዊ ግንኙነት ሊባል የሚችል እንደሆነ የሚጠቁም … የእጅ አዙር መልዕክት ነው … ከዚህ በተጨማሪም …. አንዱ ወጣት … ዘሩን በሚያፈስ መልኩ የሻምፓኝ ጠርሙስ እየናጠ ፤ መክደኛውን ከፍቶ … ከጓደኞቹ ጋር በሻምፓኝ ሲራጭ ይታያል … እንዲህ ያለው … አስጸያፊና ባህሪያዊ ያልሆነ ግበረ ሰዶማዊ ርኩሰት … መልካም ቅብ ተቀብቶ … ለህጻናት ተመልካቾች እንኳ ሳይቀር መቅረቡን ሲመለከቱ … እየተሰነዘረ ያለው ጥቃት ምን ያህል የገዘፈ እንደሆነ ይረዳሉ። … ሌላው ቀርቶ … ህጻናት ይህን መሰል የሙዚቃ ቪዲዮ … ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመለከቱ … ግራ የመጋባት ስሜት እንደሚስተዋልባቸው … በጊዜ ሂደትም እንደሚቀበሉትና እንደሚዋሃዳቸው … ደስ ተሰኝተውበትም ከሙዚቃው ጋራ አብረው ወደመጨፈር እንደሚደርሱ … እስከማሳየት የሚደርስ ድፍረት የሚታይበት   የሙዚቃ ቪዲዮ ነው ፤ … ከዚህ በተረፈ  … ስለዚህ ቪዲዮ ምን መጨመር ያስፈልጋል ይሆን?

[HOLLYWOOD/MADONNA]



በዚህ የዘፈን ክሊፕ ደግሞ … ማዶና ፣ ክሪስቲና አጉሌራና ብሪትኒ ስፒርስ … በመላው አለም በተላለፈና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሳይቀር በታየ … የኤም ቲቪ አመታዊ የሙዚቃ የሽልማት ዝግጅት ላይ … አለአንዳች ሀፍረት እርስ በርስ ሲሳሳሙ ይታያሉ:: … እዚህ ላይ ታዲያ … እነዚህ …  ዝሙትንና ፤ በሴቶች መካከል የሚፈጸምን ባህሪያዊ ያልሆነ … ጾታዊ ግንኙነት … ሌዝቢያኒዝምን … የሚያሻሽጡ … ታዋቂ ሴት ዘፋኞች … በአብዛሃኞቹ የአገራችን የከተማ ታዳጊዎች ዘንድ … ከፍተኛ ተወዳጅነት እንዳላቸው ፤ ልብ ይበሉ:: … ታዳጊዎቻችን … እነዚህን የጥፋት ግብረ አበሮች … ከማድነቅና ከመውደድ አልፈው ... የዘፈን ግጥሞቻቸውን ለመሸምደድ ይደክማሉ ፤ በቃላቸውም የሚያንጎራጉሯቸው ዘፈኖች ቁጥር ጥቂት አይደለም … ይህን ተከትሎም … ዘፈኖቹ በውስጣቸው የቋጠሯቸው የርኩሰት አጀንዳዎች … ቀስ በቀስ በውስጣቸው መስረጹ … የማይቀርና የማይጠረጠር ነው:: … እንዲያውም … ከሚያደርሱት ተፅዕኖ አንጻር ሲታይ … ልጆቻችን … የእነዚህን ዘፋኞች … የአለባበስ … የጸጉር አሰራር ፤ የአነጋገር ፤ የአረማመድ ፤ ባጠቃላይ የአኗኗር ስርዓት የሚከተሉትን ያህል … የቅርብ ወላጆቻቸውና ዘመዶቻቸው የሚነግሯቸውን ግማሹን እንኳን አይከተሉም።

[I KISSED A GIRL/KATY PERRY]


ቀጥሎ የምንሰማውን ዘፈን የተጫወተችው … ካቲ ፔሪ ነች ፤ … በዘፈኗ አዝማች ላይ የሚከተለውን ትለናለች …

“I kissed a girl & I liked it                         አንዲት ኮረዳን ሳምኳት ይህንን መፈጸሜም ደስ አሰኘኝ፤
Hope my good friend don’ mind it          ወዳጄ ቅር እንደማይልህ ተስፋ አደርጋለሁ::

አዝማቹ በራሱ … ተጨማሪ ማብራሪያ በማያስፈልገው ሁኔታ … በሴቶች መካከል የሚፈጸምን ባህሪያዊ ያልሆነ … ጾታዊ ግንኙነት … የሚደግፍ … አልፎም ደስ የሚያሰኝ ድርጊት እንደሆነ የሚሰብክ ነው።





[SAVED BY THE BELL]



ሴቭድ ባይ ቤል’ … 10 ዓመት ግድም በፊት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንቲቪ አፍሪካ ከተሰኘ የደቡብ አፍሪካ የቲቪ ኔትወርክ ጋር በመተባበርበተከታታይ ያቀርበው ነበር … አስቂኝ የታዳጊዎች የሃይ ስኩል ፊልም ነው:: … በዚህ ለለጋ ታዳጊ ተመልካቾች ታቅዶ ዘጋጀ … ተከታታይ ፊልም ላይ … ሁለት ወጣት ወንዶች በትምህርት ቤታቸው ውስጥ ጀመሩት ገራገር ቀረቤታ ቀስ በቀስ አድጎ … አብረው አዘውትረው ከመታየት አንስቶ … በይፋ በጓደኞቻቸው ፊት በትምህርት ቤቱ ኮሪደሮች እስከመሳሳምና ፤ ግብረ ሰዶም እስከመፈጸም ሲደርሱ የምንመለከትበትን ትዕይንት እናገኛለን። አስገራሚ በሆነ ሁኔታ … የፊልሙ አዘጋጆች የወጣቶቹን ግንኙነት … ተቀባይነት ያለውና ፤ መሳጭ ቃና እንዲላበስ አድርገው ያቀረቡት ሲሆን ይህም … በቀላሉ በፊልም ፅዕ ለሚጠቁ ለጋ ተመልካቾች … ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ሳይታለም የተፈታ ነው::

በትምህርት ዘርፉ ላይ እያሳደሩት ያለ ተፅዕኖ


ግብረ ሰዶማውያ … የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም … መጠነ ሰፊ የሆነ የጥቃት ዘመቻ ውስጥ እንደመገኘታቸው ሁሉ … በትምህርቱ መስክም የተፅዕኗቸውን አሻራ ለማሳረፍ ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም:: የኤች አይ ቪ ኤድስ ግንዛቤ መፍጠሪያ ፣ የህብረ-ባሕል ማስተዋወቂያ … multi-culturalism ፤ የጉልበት ትንኮሳ መከላከያ ፤ ወ.ዘ.ተ … የሚሉ ክፍለ ጊዜያትንና መሰል ዝግጅቶችን እንደጭምብል በመጠቀም … በየትምህርት ቤቱ በትምህርት ገበታ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች … ለአጸደ ሕጻናት ጨቅላዎች ሳይቀር  ጸያፍ የሆነ ምግባራቶቻቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ:: … በአሜሪካ ብቻ እንኳን … የግብረ ሰዶማውያንን ኢ-ባህሪያዊ ጠባይ .. መልካምና ተቀባይነት ያለው አድርገው የሚያቀርቡት … ‘ሄተር ሐዝ ቱ ማሚስ’ እና ‘ዳዲስ ሩሜት’ … የተሰኙ መጻሕፍት .. በበርካታ የግልና የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ቤተ መጻሕፍት ውስጥ … ወላጆች ባላወቁበት ሁኔታ የትምህርት ማጣቀሻ መጻሕፍት በመሆን ግልጋሎት ላይ መዋል ከጀመሩ ዋል አደር ብሏል:: … በተጨማሪም … ‘ዘ ፕሌይ ቡክ ፎር ኪድስ አባውት ሴክስ’ የተሰኘና ፤ አላማውን ግብረ ስጋ ግንኙነትን ለሕጻናት ማስተዋወቅ ያደረገ መጽሐፍ … በ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ሕጻናትና ተዳጊዎች በተለያዩ መንገዶች እንዲያገኙት እየተደረገ ሲሆን … በውስጥ ገጾቹም … ዘርን የማፍሰሻ ዘዴዎች … ማስተርቤሽን ሜትድስ እና ሌሎች መሰል አስጸያፊ የዝሙት ግብራት የሚፈጸሙባቸውን መንገዶች  በዝርዝር የሚያስረዱ በርካታ ጽሑፎች ተካተውበታል::


‘we shall sodomize your sons, emblems of your feeble masculinity; we shall seduce them in your schools, in your dormitories, in your gymnasiums, in your locker rooms, in your sports arenas, in your seminaries, in your youth groups. …የደካማ ወንዳወንድነታችሁ መገለጫ የሆኑ ወንዶች ልጆቻችሁን በግብረ ሰዶም እናጠቃቸዋለን ፤ በትምህረት ቤቶቻችሁ ፣ በዶርሚተሪዎቻችሁ ፣ በጂምናዝየም አዳራሾቻችሁ ፣ በስፖርት ማሳያ ስፍራዎቻችሁ ፣ በካህናት ማሰልጠኛዎቻችሁና በወጣት ማኅበራቶቻችሁ ሳይቀር … ፍትወታችንን እንፈጽምባቸዋለን …’ Michael Swift, Gay Community News, Feburuary 15-21 1985

ከዚህ የማን አለብኝነት መገለጫ የሆነ ንግግር እንደምንረዳው … ከአጠቃላይ ማሕበረሰቡ አንጻር ፤ እዚህ ግባ የሚባል ቁጥር የሌላቸው … እነዚህ የጥፋት ሰራዊት አባላት … አብዝሃውን ወደ ተያያዙት የርኩሰት ጎዳና ለመክተት ምን ያሕል ርቀት እየተጓዙ እንደሆነ ነው::


ፕሮጀክት ቴን  … እ.ኤ.አ በ1984 ዓ.ም በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ የተቋቋመ የግብረ ሰዶማውያን ማስፋፊያ ማሕበር ነው:: … ማኅበሩ … ግብረ ሰዶማዊቷ የማኅበሩ መስራች …መምህርት ዶ/ር ቨርጂኒያ ዩሪብ በግልፅ እንዳስቀመጠችው … ‘ከአጸደ ሕጻናት አንስቶ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች የሚገኙ ተማሪዎች … የግብረ ሰዶማውያንን ጾታዊ ጠባይ ተፈጥሯዊ እና ተመራጭ እንደሆነ እንዲቀበሉ ግንዛቤ መፍጠር’ን ተቀዳሚ አላማው አድርጎ የሚንቀሳቀስ ማኅበር ነው:: … ዶ/ር ዩሪብ … አስገራሚ በሆነ ሁኔታ … ናሽናል ኢዱኬሽን አሶሴሽን ከተሰኘ ተቋም … ‘ለሰዎች መብት መጠበቅ ፤ በታየ አፍላቂ የአመራር ችሎታ’ ዘርፍ … ሽልማትን የወሰደች ሲሆን … በሽልማቱ ወቅት ያደረገችው ንግግር ፤ የወገኖቿን የወደፊት ዕቅድ ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነበር። … ዶር ዩሪብ እንዲህ ነበር ያለችው …

“the state courts must be used to force the school districts to disseminate accurate information about homosexuality. They need to hear this; kids need to hear the latest scientific information on the subject of homosexuality and that’s something that all kids need to hear, not just gay and lesbian kids. Starting from kindergarten, again and working its way all the way through high school. This idea of talking about it one time in high school… well we know that doesn’t work. We need to start tackling this at the very early ages. … የክልል ፍርድ ቤቶችን ተጠቅመን ፤ የወረዳ ትምህርት ተቋማት ስለ ግብረ ሰዶማውያን አኗኗር ወቅታዊ መረጃዎችን ለተማሪዎቻቸው እንዲያሰራጩ ልናስገድዳቸው ይገባል ፤ ሕጻናት ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ዘመኑ የደረሰበትን ወቅታዊና ሳይንሳዊ መረጃ ሊያውቁ ይገባል ፤ ይህ ደግሞ ግብረ ሰዶማውያን ሕጻናት ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች የዕድሜ እኩዮቻቸው ሁሉ ሊያውቁት የሚገባ መረጃ ነው ፤ ከአጸደ ሕጻናት አንስቶ በየደረጃው እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ እስኪደርሱ … አመለካከታቸው ላይ ተጠንክሮ ሊሰራባቸው ይገባል:: … ሁለተኛ ደረጃ ሲደርሱ አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሰሙት የማድረጉ አካሄድ … እንደማይሰራ ተገንዝበነዋል እጅግ ዝቅተኛ የእድሜ ደረጃ ሳሉ አንስተን ይህንን የተዛባ አመለካከተ ልንፋለመው ይገባል::’

እነዚህ ግብረ ሰዶማውያን … በትምህርቱ መስክ እያሳደሩ ያሉትን ፈርጀ ብዙ ተፅዕኖ በውል መረዳት ይቻለን ዘንድ … እግረ መንገድም በአሜሪካ የትምህርት ስርት ላይ ተፅዕኗቸው ምን ያህል ርቀት እንደተጓዘ ለመገንዘብ ይረዳን ዘንድ በሜይ 2009 ዓ.ም ሳን ፍራንሲስኮ ውስጥ በአላሜዳ ካውንቲ ወረዳ በሚገኝ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ሕጻናትን ከጉልበት ትንኮሳ ራሳቸውን እንዲከላከሉ ለማስተማር በሚል ሰበብ የግብረ ሰዶም አጀንዳ በስርተ ትምህርቱ ውስጥ እንዴት ካተት እንደበቃ … የፎክስ የዜና ማሰራጫ የዘገበውን ዘገባ ቀጥለን እንመልከት

[GAY AGENDA IN SCHOOLS] 




ዘገባው ላይ በግልጽ እንደምንመለከተው
·        የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ቦርድ የግብረ ሰዶማውያኑ ጀንዳ በስርተ ትምህርታቸው ውስጥ እንዲካተት ለማድረግ ምህርት ቤቱ በጀ ፈሰስ አድርለስብሰባ የሚያስፈልገውን ወጪ መሸፈን ጀምሮ … ወላጆችን ጠርቶ እስከ መሰብሰብና ፤ ድምጹን ሰጥቶ አጀንዳውን እስከ ማጽደቅ የደረሰ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
·        የግብረ ሰዶማውያኑ ጥምረት አጀንዳቸውን የሚደግፍ ትምህርት በስርተ ትምህርውስጥ እንዲካተት ለማድረግ ይቻሉ እንጅ ፤ በልጆቻችን ላይ እየደረሰ ነው የሚሉትን ትንኮሳና መገለል የሚደግፍ መስረጃ … በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረጉ ጥናቶች ላይ አልተገኘም።
·        በዚህ ውሳኔ መሰረት 2ኛ እና 3ኛ ክፍል ሕጻናት የግብረ ሰዶማውያንን አኗኗር ተመራጭ አድርገው የሚያቀርቡ መጻህፍትን … ለአብነትም ሁለት ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ፔንጊዩኖች ሕጻን ፔንጊዩን ሲያሳድጉ የሚተርከውን ‘ታንጎ ሜክስ ስሪ’ … የግብረ ሰዶማውያን ቤተሰብ ኑሮ መልካምና ተመራጭ አድርጎ የሚያሳየውን ‘ዛት ኢዝ ኤ ፋሚሊ’ የተሰኙ መጻሕፍት … በንባብ ክፍለ ጊዜያቸው እንዲያነቡ ይገደዳሉ።
·        ከዚህ ጋር በተያያዘ … በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ 11 ክፍላተ ሀገራት … የጸረ ትንኮሳ ትምህርትን በስርተ ትምህርታቸው ውስጥ እንዲተት ያደረጉ ሲሆን በዚህ ትምህርት ውስጥም ከ2ኛ ክፍል ጨቅላዎች አንስቶ እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ድረስ ስለጾታዊ የሩካቤ ፍላጎትና ስለ ተመሳሳይ ጾታ ሩካቤ ተፈጥሯዊነት እንዲማሩ ይደረጋ::
  
ግብረ ሰዶማውያን በኢትዮጵያ



ሀገራችን ኢትዮጵያ ስለሚገኙ ግብረ ሰዶማውያንና ሕቡዕ ስለሆነው እንቅስቃሴያቸው ጥናት ማድረግ ተጨባጭና የጠራ መረጃ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው:: ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ነባራዊው ለቀደሙ መልካም እሴቶች ቀናኢ የሆነው ይማኖታዊና ባላዊ ዳራ ፈፅሞ ባለመጥፋቱ … በግብረ ሰዶማውያኑ ፅዕኖ ስር ሙሉ በሙሉ ባለመውደቁ … እነዚህ የጥፋት ሀይሎች እኩይ የሆነ ግብራቸውን በይፋ ለመፈጸም ባለመድፈራቸው አመቺ ሁኔታዎች ተፈጥረው አንገታቸውን ካደቡበት ብቅ እስኪያደርጉ ድረስ ከሕብረተሰቡ አይን ተሸሽገው ምስጢራዊ በሆኑ የግለሰብ ቤቶችና እነሱው ብቻ በሚያውቋቸው የምሽት ክበቦችና መሸታ ቤቶች ለመፈጸም በመገደዳቸው ነው:: … ይህም ሆኖ ግን ድምጻቸውን አጥፍተው ውስጥ ለውስጥ ግብረ ሰዶማዊነትን በማስፋፋት የበላይነቱን ለመያዝ የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው የሚያመለክቱ መረጃዎች አልጠፉም:: በተለይ በከተሞች አካባቢ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግብረሰዶማውያን መገኘታቸውን ይፋዊ ያልሆኑ የዳሰሳ ጥናቶች ያመለክታሉ::

የኢንተርኔትና የዲሽ ተጠቃሚዎች በከተማዎች አካባቢ መበራከት የግብረ ሰዶማውያን የኑሮ ዘይቤ የነገሰባቸው የምራብ አለም ገራት የባል ተፅዕኖ በሕብረተሰቡ ዘንድ እንዲሰርጽ ከማድረግ አንጻር ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል:: በተጨማሪ ወላጅ አልባ ሕጻናትን በማሳደግና መሰል በሆኑ የግብረ ሰናይ ስራዎች ተሰማሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አካባቢ የሚፈጸሙ ሕጻናትን የመድፈር ተግባራት ግብረ ሰዶማዊነትን ለማስፋፋት የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል::


በከተሞቻችን አካባቢ እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግብረ ሰዶማውያን መገኘታቸውን ተከትሎ የግብረ ሰዶማውያን መብት አቀንቃኝ የሆኑ ማሕበራት የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ቀልብ ለመሳብና የመብትና የእኩልነት ጥያቄን ለማንሳት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ሲሆን ፤ አብነትም እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብረ ሰዶማውያን ፊርማ አሰባስበው የእኩልነት መብትን ለመጠየቅ የሞከሩበትን … በጊዜውም ማመልከቻው ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ሳይደርስ ሊጨናገፍ በቃበትን አጋጣሚ ማውሳት ይቻላል:: በዛ አመት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ይፋዊ ያልሆነ የግብረ ሰዶማውያን የጋብቻ ስነ ስርት በሸራተን አዲስ ሆቴል በሁለት ኢትዮጵያውያን ወንዶች መካከል መፈጸሙም የሚጠቀስ ነው:: ይህንና ይህን መሰሉ አወዛጋቢ የግብረ ሰዶማውያን ፋዊ ያልሆኑ ሕቡዕ እንቅስቃሴዎች ለመግታት ብሎም ለማስቆም በማሰብ በሕዳር 2008 ዓ.ም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፣ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንየፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናትን ጨምሮ የኢትዮጵያ ይማኖት ተቋማት መሪዎች ስብሰባ ተቀምጠው የነበረ ሲሆን ፤   የእኩይ ግብራት ሁሉ ቁንጮ በማለት የጠሩትን የግብረ ሰዶማውያኑን እንቅስቃሴ አስመልክቶ የአንድነት አቋምና የጋራ መግለጫ አውጥተዋል:: በዚህ የጋራ መግለጫቸው ላይ ፤ ይማኖት መሪዎቹ … ለሀገሪቱ ፓርላማ የሚከተሉትን አበይት ጥያቄዎች አቅርበዋል።

·  የተመሳሳይ ጾታ ተዋስቦ የትውልድን ቀጣይነት የሚጻረርና ሕገ መንግስቱ እውቅና የሚሰጣቸውን የቤተሰብ እሴቶች የሚንድ እኩይ ግብር በመሆኑ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያግድ ሕግ በሕገ መንግስቱ ውስጥ እንዲካት፤
· በግብረ ሰዶም ለተጠቁ ግለሰቦች የስነ ልቦና እርዳታና የምክር አገልግሎት የሚሰየማገገሚያ ማዕከላት እንዲቋቋሙ
· ግብረ ሰዶማዊነትንና ሌሎች አስነዋሪ ድርጊቶችን በማዛመት ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ የሚገኙት የኢንተርኔት ድረ ገጾች ሳንሱር እንዲደረጉ፤ (ማሞ፣ 2009፣ ገጽ 28)
የሚሉት ናቸው፡፡


ያም ሆኖ ይህ … የሃይማኖት መሪዎቹ መግለጫ ፤ … በታሳስ 2009 ዓ.ም ፤ … በከፊል ይፋዊ የሆነ … የመጀመሪያው የግብረ ሰዶማውያን ማበራዊ መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ … እንዳይዘጋጅ የሚከላከል ሳይሆን ቀርቷል።

ይፋዊ ያልሆኑ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአዲስ አበባ ብቻ ቢያንስ 50 000 የሚደርሱ ፤ ጎዳና ላይ ገላቸውን በመሸጥ የሚተዳደሩ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስይ 5000 የሚሆኑት ግብረ ሰዶማውያን ወንደኛ አዳሪዎች ናቸው ፤ ወንደኛ አዳሪዎቹ ቱሪስቶች በሚያዘወትሯቸው ኢንተርናሽናል ሆቴሎች ዙሪያ ባሉ ጎዳናዎች ፤ ታዋቂ ናይት ክለቦች ፤ የማሳዥና የቤተሰብ መታጠቢያ ማዕከላት አዘውትረው የሚታዩባቸውና ከደምበኞቻቸው ጋር የሚቃጠሩባቸው ስፍራዎች ናቸው፡፡

ግብረ ሰዶማዊነት … በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያደርገውን መስፋፋት ለመግታት ፤ የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ  ከሚያደርጉት ምክንያቶች ዋነኛው ፤ ለጉዳዩ የሚሰጠው ዝቅተኛ ግምት ነው። … የሃይማኖት መሪዎችና ሌሎች ተቆርቋሪ አካላት ፤ ችግሩን ሀገር በቀልና ፤ በአንዳንድ አእምሯቸውን ያጡ ፤ ቅንጡ ግለሰቦች የሚፈጸም ተራ ጋጠወጥነት አድርገው ስለሚመለከቱት መዘናጋት ይስተዋልባቸዋል ፤ እውነታው ግን  … ግብረ ሰዶማዊነት … ፈጣሪን ከማክበርና ከመፍራት ወጥተው ፤ ሊገዳደሩት በሚሞክሩ ምዕራባውያን  ፤ በተለይም አዋቂና ታዋቂ በሚባሉት ግለሰቦች የሚፈጸም ፤ በአለም አቀፍ ደረጃ ሕቡዕ የሆነ መረቡን ዘርግቶ ፤ በተደራጀ መልኩ መስፋፋትን የሚያደርግ ፤ ተፈጥሯዊ ያልሆነ አስነዋሪ ድርጊት መሆኑ ነው።

ባጠቃላይ ባለፉት አስርት አመታት የተካሄዱትን የጌይ ፕራይድ እንቅስቃሴዎችን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት ግብረ ሰዶማዊነትንና ሌሎች መሰል የተመሳሳይ ጾታ ተራክቦን መፍቀድ ከዴሞክራሲና ከመብት ጥያቄዎች ጋር በስፋት በመያያዝ ላይ ናቸው፡፡ አስቀድሞ በግብረ ሰዶማውያን ላይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ የሚታወቁ ሀገራት ሳይቀሩ የዜጎችን መብት ለማክበርና የሰብዓዊ መብትን ለማስጠበቅ በሚል አመክንዮ አቋማቸውን በመቀየር ላይ ናቸው፡፡

የተባበሩት መንግስታትን ፣ የአለም ባንክን ፣ የአለም ገንዘብ ድርጅትን ፣ የኒዎርኩ ዎልስትሪትን ፣ የአለም ጤና ድርጅትን ፣ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶን ፤ … በመሳሰሉ ፤ አለም አቀፍ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መድረኮች ውስጥ ፤ ቁልፍ የስልጣን መንበሮችን ከተቆናጠጡት ፤ ፅዕ ፈጣሪ ቃን መሃል ፤ … በርካቶቹ … ግብረ ሰዶማውያን መሆናቸውን ተከትሎም ፤ በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ ጽኑ እርምጃን በመውሰድ የሚታወቁ ሀገራት ፤ የሕግ ማሻሻያ እንዲያደርጉ ፤ አልፎ ተርፎም ለግብረ ሰዶማውያኑ እውቅናና የሕግ ከለላ እንዲሰጡ ፤ ተፅዕኖ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ (በቅርቡ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የግብረሰዶማውያንን መብት ለማያከብሩና ለማያስከብሩ የአፍሪካ ሀገራት የሚደረግን እርዳታ እንደሚያግድ ማስጠንቀቂያ ብጤ ማስተላለፉን ልብ ይሏል ፤ ሰሞኑንም የዩጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቨኒ የጸረ ግብረሰዶም ህግ መፈረማቸውን ተከትሎ የተከሰተው እንኪያስላንቲያ … የዚሁ ተጽዕኖ አንዱ ማሳያ ነው፡፡)




ልብ ያለው ልብ ይበል!!  ይቆየን...


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።

Tuesday, March 4, 2014

ቴክኖሎጂ ያዘመነው የእኛ ትውልድና ፤ ሚዲያ መራሹ ማሕበራዊ ምስቅልቅል Part 2

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡





Did you remember a film which encourages you not to have sex before marriage? click here.

ከላይ እንደተመለከትነው ወጣቶች እስከዛሬ ከተመለከቷቸው ፊልሞች መካከል ከትዳር በፊት ከሚደረግ ጾታዊ ተራክቦ እንዲታቀቡ የሚመክሩ ካሉ እንዲያስታውሱ ተጠይቀው ነበር፡፡ ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ወጣቶች ሁሉ አንድ እንኳ ፊልም መጥቀስ ተቸግረው ግራ ሲጋቡ መመልከት ስለሆሊውድ ፊልሞች መጠነኛ ግንዛቤ ላላቸው ሰዎች እምብዛም አስገራሚ አይሆንም፤ አንድም የለምና!

"… የሰራሁት ፊልም ሁሉን ይዟል ፤ ጭካኔ ጾታዊ ግንኙነት ፤ በጣም ጸያፍና ዘግናኝ ትዕይንቶች ፤ ቀልብ የሚገዙና ልብ የሚሰቅሉ ፍልሚያዎች … ሁሉን አካቷል ፤ በቃ ያልያዘው ነገር የለም ፤ ይህን ያደረኩት ታዲያ ሰዎች መጥተው እንዲያዩት ካለኝ ፍላጎት የተነሳ ነው…" ፍራንሲስ ፎርድ ኮፖላ ፤ የጎድ ፋዘር ፤ አሜሪካን ግራፊቲ ፤ ፍራንከንስታይን ፊልሞች ዳይሬክተር

"… ፊልም የመስራት ሞያ ፤ ተመልካቹ ሳያስተውል እንግዳ አስተሳሰቦችን የማስረግ ጥበብ ነው ፤ በዚህ መልኩ ስናየው ወጣ ያለ ፊልም የመስራት ሂደት ፤ ሆን ብሎ የተመልካችን አስተሳሰብ ከማዛባትና ከማዳከም ሴራ /ሰቨርዥን/ ጋር የተያያዘ ነው …" አለን ሩዶልፍ ፤ የሜድ ኢን ሄቨን ፤ ኢኩዊኖክስ ፤ ... ፊልሞች ዳይሬክተር

"… የፊልም ስክሪፕት በየአስራ አምስት ገጹ እርቃን የሚያሳይ ትእይንት መያዝ አለበት ፤ … በየአስራ አምስት ገጹ ፤ ልብ አድርግ … የተዋናይዋን እግሯን የሚያሳይ ሊሆን ይችላል ፤ ወይም ሙሉ እርቃኗን ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን በየአስራ አምስት ገጹ የእርቃን ትእይንቶችን በማካተት የተመልካችን ቀልብ ገዝተህ ልትጓዝ ይገባሃል …" ማርቲን ኮርሲስ የዘላስት ቴምፕቴሽን ኦፍ ክራይስት ፤ ጉድ ፌላስ ፤ ዘ ዲፓርትድ ፤ ... ፊልሞች ዳይሬክተር


ለመሆኑ የፊልም አዘጋጆችና ዳይሬክተሮች ሕሊናቸውን ሸጠው በነቂስ በሰፊዋ የጥፋት መንገድ ለመንጎድና በፊልም ውጤቶቻቸው ዘግናኝና አስጻያፊ የሆኑ ዝሙት ቀስቃሽ ትዕይንቶችን ለማካተት የፈቀዱበት ምክንያቱ ምን ይሆን? በርካታ ለዘርፉ ቅርበት ያላቸው ውስጥ አዋቂ አጥኚዎች ለዚህ መንስኤ የሚሆኑና በበቂ መረጃ የተደገፉ በርካታ አመክንዮዎችን የሚጠቅሱ ሲሆን የተቀሩትን በይደር ትተን ከእነዚህ መካከል አንዱን ማንሳት በቂ ይሆናል - ኢኮኖሚያዊ ትርፍን፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት የፊልም ኢንዱስትሪው ዋነኛ ሸማቾች ከሆኑት መካከል በግምባር ቀደምትነት የሚገኙት ከ12-18 የእድሜ ደረጃ ላይ የሚገኙ ታዳጊ ወጣቶች ናቸው፡፡ እኒህ በእድሜ ለጋ የሆኑ የፊልም ደምበኞች ፤ ስራ የመስራት ግዴታ የሌለባቸው ፤ ለዋዛ ፈዛዛ የሚሆን በቂ ጊዜ ያላቸውና ወላጆቻቸው ወዛቸውን አንጠፍጥፈው የሚያገኙትን ገቢ በግድ የለሽነት ለመበተን የማያቅማሙ እንደመሆናቸው መጠን በመዝናኛ ኢንዱስትሪው የወርቅ እንቁላል እንደምትጥል ዶሮ ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡

እንደእሳት መያዣ መጨበጫ በሌለው አስቸጋሪ እድሜ ላይ ላሉት እኒህ ታዳጊዎች ምን አይነት ይዘት ያላቸው የፊልምና የሕትመት ውጤቶች በቀላሉ በኪሳቸው የያዙትን ገንዘብ አሟጠው እንዲያራግፉ ይገፋፏቸው ይሆን? በቀላሉ ለመገመት እንደሚቻለው ዝሙት ቀስቃሽና የጭካኔ ድርጊቶች ያሉባቸው ፊልሞች ናቸው፡፡

… Do you want what kids want? … well, this may sound silly to you … but kids go completely aped if you do three things … 1. Defiey authority 2. Destroy property and 3. Take people clothe off. …

በሚዲያዎች በሚዘወተሩ ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች ላይ ያተኮሩ በርካታ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት እኒህ አጸያፊ ትእይንቶች በታዳጊዎችና በወጣቶች ብሎም በአጠቃላይ የዘመኑ ትውልድ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ በማስከተል ላይ ይገኛሉ፡፡ አስነዋሪ ትእይንቶች በትውልዱ ላይ እያስከተሉት ያለውን ተጽእኖ ካጋለጡ ጥናቶች መካከል የተወሰኑትን እንደማስረጃነት ለአብነት እንመልከት፡-

… የአየር ሰአቱን ከተቆጣጠሩት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ሁለት ሶስተኛ (64%) የሚሆኑት ለዘብ ያሉ ዝሙት ቀስቃሽ ትዕይንቶች፣ አንድ ሶስተኛ (32%) የሚሆኑት ልቅ የፍትወት ተግባራት፤ አንድ ሰባተኛ (14%) የሚሆኑት ደግሞ ግልጽ ጾታዊ ተራክቦ ሲፈጸም ይታይባቸዋል … ከይዘር ፋሚሊ ፋውንዴሽን

… ከአንድ ሰአት ላነሰ ጊዜ የኤም ቲ ቪ የሙዚቃ ፕሮግራሞችን እንዲመለከቱ የተደረጉ የ7ኛ እና 9ኛ ክፍል ታዳጊዎች ፤ ካልተመለከቱት ታዳጊዎች በተለየ ‹ከትዳር በፊት ጾታዊ ግንኙነት ማድረግ ምንም ችግር የለውም› የሚል አመለካከት ለማዳበር ይበቃሉ… ግሪንሰን እና ዊሊያምስ /1986

ካልፊን፣ ካሮልና ሽሚድት (1993) ባዘጋጁት ጥናታዊ ሪፖርት በተመሳሳይአንድ የሙዚቃ ቪዲዮ እንዲመለከቱ የተደረጉ የኮሌጅ ተማሪዎች ካልተመለከቱት በላቀ ሁኔታ ቅድመ-ትዳር ለሚደረግ ጾታዊ ግንኙነት በጎ አመለካከት አንጸባርቀዋል፡፡

ግሪንበርግ የተሰኘ ተመራማሪ እንዲሁ በሁሉም አይነት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ በአማካይ በሰአት ሶስት ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች እንደሚተላለፉ በመረጃ በተደገፈው ጥናቱ ጠቁሟል፡፡ በዚህም መሰረት ሰዎች በአዘቦት ቀናት በአማካይ በቀን አንድ ሰአት በእረፍት ቀናት ደግሞ በአማካይ ለሁለት ሰአታት ቴሌቪዥን ይመለከታሉ በሚል እሳቤ (ይህ ስሌት እንግዲህ በአመዛኙ ቴሌቪዥን የማየት ሱስ ለተጠናወተው የምዕራቡ አለም ተመልካች እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ልብ ይሏል) ያሰላው ግሪንበርግ አንድ ተመልካች በአማካይ በሳምንት 27 ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶችን በአመት ደግሞ 1400 ትእይንቶችን በትንሹ እንደሚመለከት ዘግቧል፡፡

ሃዋርድ በ 1985 ወደ 1000 በሚደርሱ ታዳጊዎች ላይ ባካሄደው ሌላ ጥናት ቴሌቪዥን ታዳጊዎች ጾታዊ ተራክቦ አለጊዜያቸው እንዲጀምሩ ከሚያደርጓቸው ተጽእኖዎች መካከል ዋነኛውና ከፍተኛው እንደሆነ ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

የታይም/ሲ. ኤን. ኤን የሕዝብ አስተያየት ውጤት ላይ ተመስርቶ ስትሮጅሂል    በ 1998 ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከአሜሪካውያን ታዳጊዎች መካከል 29 በመቶ የሚሆኑቱ ቴሌቪዥንን ስለጾታዊ ተራክቦ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ እንደሆነ ጠቅሰዋል፤ ይህም በ1986 11 በመቶ ብቻ እንደነበር ሲታሰብ በተለይ ታዳጊዎች ምን ያህል ከጊዜ ወደ ጊዜ በቴሌቪዥን ተጽእኖ ስር እየወደቁ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ወደ 45 በመቶ የሚሆኑት ታዳጊዎች ደግሞ ስለ ጾታዊ ተራክቦ አብዛኛውን መረጃ የሚያገኙት ከጓደኞቻቸው እንደሆነ ሲገልጹ ስለዚህ ጉዳይ የመረጃ ምንጮቻችን ወላጆቻችን ናቸው ያሉ ግን 7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው፡፡ እንግዲህ የወላጅ ምክር ተዘንግቶ በምትኩ የሚዲያዎች ተጽእኖ ምን ያህል የልጆቻችንን አኗኗር እየቀረጸ እንደሆነ ከዚህ በላይ መረጃ አያሻንም፡፡

ኢፍ ዩ ሲክ ኤሚ
የሆሊውድ ዘፈኖች ውስጥ የተመሰጉ የርኩሰት መልዕክቶች አንዱ ማሳያ

ሊዮኒ ባርሰንባች የተሰኘች በሲድኒ የምትኖር አንዲት የቤት እመቤት ዘፈን ውስጥ የተመሰጉ ዝሙት ቀስቃሽ ትእይንቶች ጓዳዋን እንዴት እንዳወኩት እንደሚከተለው ትገልጻለች፤ ‹የ5 እና የ7 አመት ልጆቼ በቤታችን እየተዘዋወሩ (ለጆሮ የሚቀፍ የዝሙት ቃል) እየጠሩ ሲዘፍኑ ስሰማ በጣም ነው የደነገጥኩት፤ ድርጊቱን ለማመን ከብዶኛል… ምን እያሉ እንደሆነ ስጠይቃቸው የብሪትኒ ስፒርስ (ዘፈን) እንደሆነ ነገሩኝ፡፡ በጣም ነው የዘገነነኝ… በጣም ክብር የሚነካ ነገር ነው፡፡ እንደተጭበረበርኩ ተሰምቶኛል፡፡›

ከላይ ከላይ ሲታይ  ‹ኢፍ ዩ ሲክ ኤሚ› የተሰኘው የብሪትኒ ዘፈን ኤሚ ስለተሰኘች አንዲት ምናባዊ ገጸ ባሕርይ የሚያጠነጥን ይመስላል፡፡ ይህ ግን የዘፈኑ ሰም ነው፡፡ የምስጢር መልእክቱ እጅግ አስነዋሪ ከመሆኑ የተነሳ ድርጊቱን ታዋቂነት ከመቀዳጀትአልያም የአልበም ሽያጭ ከማሳደግ አንጻር ብቻ ለመተነተን አዳጋች ይሆናል፡፡ ኢፍ ዩ ሲክ ኤሚ የተሰኘው የዘፈኑ አዝማች የመጀመሪያ ፊደላት ድምጸት ኤፍ ዩ ሲ ኬ ሚ (FUCK ME) የሚል አስነዋሪ የዝሙት ጥሪ ነው፡፡ እንግዲህ ይህን ለመድገም እንኳ የሚያጸይፍ መልእክት ትውልዱ በምን አይነት ርኩሰት እየተበከለ እንደሆነ የጉዳዩን አንገብጋቢነት ለማሳየት ስንል ጠቅሰነዋል፡፡

‹የወደድነውን መዝፈን መብታችን ነው፤ ልጆቻቸውን ማሳደግም ሆነ ምግባር ማስተማር የኛ ሓላፊነት ሳይሆን የወላጆች ነው› ትላለች ትውልድ አጥፊ የሆኑ መርዛማ አስተምህሮዎችን በዘፈኖቻቸው አማካኝነት ከሚነዙት ዘፋኞች መካከል የሆነችዋ ክሪስቲና አጉሌራ፡፡

በዚህ የማያባራና መቋጫ በሌለው እሰጥ አገባ መካከል ግን እምቦቃቅላዎች ሳይቀር በነዚህ ወደረኞች ዘፈን አዚም አእምሯቸው ናውዞ ግጥሞቻቸውን በደመነፍስ እያቀነቀኑ ወደአይቀሬው የጥፋት ጎዳና በመንጎድ ላይ ናቸው…

በአገራችንም በ60ዎቹ አነኤልቪስን በሚኮርጁ አቀንቃኞች መሪነት የተጀመረው የባሕል አብዮት በሕብረተሰቡ ስር ሰዶ ከፍተኛ የሆነ የአኗኗር ለውጥ አስከትሏል፡፡


ይህን ተከትሎም… በአንድ ወቅት እንደነውር ይታይ የነበረው ከጋብቻ ውጪ ጾታዊ ግንኙነት መፈጸም የተለመደ ከመሆን አልፎ ቀስ በቀስ በድንግልና ጸንተው በሚቆዩት ላይ ሽሙጥና ስላቅ መሰንዘር የተጀመረበት፤ … ቅጥ ያጣ ልቅ ዝሙት የሚያስከትለውን ያልተፈለገ እርግዝና ጉዳይ መፍትሔ ለመስጠት ምግባርን ከማስተማር ይልቅ ኮንዶም አጠቃቀምና የውርጃ መፈጸሚያ ማእከላትን አድራሻ ለሕጻናት ሳይቀር ማመላከት የተመረጠበት … ይህን ተከትሎም በአገራችን በአስር ሺዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናት ከማሕጸን ሳይወጡ የሚፈጁበት፤ … በጾታዊ ፍላጎት አለመጣጣምና ሌሎች መሰል ቁንጽል ምክንያቶች ትዳር በቀላሉ የሚፈርስበትና የትዳር ጓደኛን እንደልብስ መለዋወጥ የተዘወተረበት ፤ ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡








እንደ ዳቪንቺ ኮድ ያሉ ፍጥጥ ያሉ ጸረ ክርስቶሳዊ ፊልሞች የቦክስ ኦፊስ የደረጃ ሰንጠረዥን መቆጣጠር ሲጀምሩ ነበር አሸልበው የነበሩት ክርስቲያኖች ለመጀመሪያ ጊዜ ጠንከር ያሉ የተቃውሞ ድምጾችን  በሆሊውድ የፊልም ኢንዱስትሪና በሚዲያ ተቋማት ላይ ማሰማት የጀመሩት፡፡ ነገር ግን በዚህም ወቅት እንኳ ድርጊቱን አልፎ አልፎ የሚከሰትና በአንዳንድ ክርስትና ላይ ግላዊ ጥላቻን በሚያንጸባርቁ የፊልም ዳይሬክተሮች/ፕሮዲዩሰሮች ከስንቴ አንዴ በተናጠል ከሚፈጸም ተግባር የዘለለ አድርገው አልተመለከቱትም፡፡ እናም የኒህን የክርስትናን መሰረተ እምነት ጭቃ የሚቀቡ የፊልም ውጤቶች ተጽእኖ ለመቃወም ያደረጓቸው ጥረቶች አልፎ አልፎ ፊልሞቹን ከማሳገድ አልያም በሕዝብ የሲኒማ ቤቶች እንዳይታዩ ከማስወሰን… ከዚያም ወደሞቀ እንቅልፋቸው መመለስ… በቃ ጥረታቸው ከዚህ የዘለለ አልነበረም፡፡

እነዚህን አወዛጋቢ ፊልሞች የጥቂቶች ግላዊ ጥላቻ ውጤት አድርገው መመልከታቸው በራሱ ክርስቲያኖች ምን ያህል ስለችግሩ ጥልቀትና ስፋት ያላቸው አመለካከት የተገደበ እንደሆነ ነው የሚያሳየው፡፡ የችግሩን ሁለንተናዊ ገጽታ ማየት ስለተሳናቸው በማሕበረሰቡ ውስጥ የሰረጹ ክርስቲያናዊ እሴቶችና አስተምህሮዎች በሆሊዉድ የአመጻና የጽርፈት ላንቃ ጥላሸት እንዳይቀቡና ክብራቸው እንዳይነወር በቡድን ተደራጅተው ያካሄዷቸው ጥረቶች ግባቸውን ሊመቱ አልቻሉም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንደተለመደው ሆሊዉድ አዲስ ክርስትናን የሚያንቋሽሽ ፊልም ባስተዋወቀ ቁጥር የሚነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ ከጥቂት ሳምንታት… ቢበዛ ከወራት አያልፍም፤ ትንኮሳውም ሆነ ተቃውሞው አንዳች ትርጉም ያለው እልባት ሳይሰጠው ሌላ ተመሳሳይ አወዛጋቢ ፊልም አልያም መጽሐፍ እስኪወጣ ድረስ ከናካቴው ይረሳል፡፡

በሆሊውድና በአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን እልፎ አልፎ የሚሰራጩት በክርስትና ላይ ያነጣጠሩ ለጆሮ የከበዱ ስድቦችና ትችቶች የግለሰቦች አመለካከቶች እንጂ ተቋማቱን አይወክሉም የሚለው እሳቤ ከእውነት በእጅጉ የራቀ ነው፡፡ በተጨባጭ ያሉትን መረጃዎች ሊመረምር ለፈቀደ ሁሉ ፍንትው ብሎ የሚታየው አሳዛኝ እውነታ ሆሊውድና የምእራቡ አለም ሚዲያና የመዝናኛ ኢንዱስትሪ የከርስትና አስተምህሮዎችና በሕብረተሰቡ የሰረጹ የክርስትና መሰረት ያላቸው ያኗኗር እሴቶችን ለመሸርሸር ብሎም በባእድ አስተሳሰቦች ለመተካት የተቀናጀ እንቅስቃሴ ላለፉት 50 አመታት እያደረጉ መሆኑ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እኒህ ክርስትና ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች ይበልጥ እየፈጠጡ መምጣታቸው ነው የአሁኑን ሁኔታ ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው፡፡

ላለፉት 50 አመታት የተላለፉ የሚዲያ ውጤቶችን ዋቢ በማድረግ የተደረጉ ጥናቶች ከየትኛውም ሐይማኖት በተለየ የክርስትና መሰረተ እምነት ከምእራቡ አለም ሚዲያ የሚሰነዘሩ … ቅኔያዊ ይዘት ካላቸው ስውር ነቀፋዎች … ፍጥጥ እስካሉ ማንጓጠጦችና ጸያፍ ስድቦች ድረስ … የበርካታ ትችቶችና የማጥላላት ዘመቻዎች ሰለባ እንደነበረ ያመላክታሉ፡፡ 

የሆሊውድ ልሂቃን ክርስትና ላይ ያላቸው አሉታዊ አመለካከት በርካታ የፊልምና የሚዲያ ፈርጦቻቸው በሚሰጧቸው መግለጫዎች ወቅት በድፍረት በሚሰነዝሯቸው የመረረ ጥላቻን የጸነሱ ጽርፈትና ትችቶቻቸው በግልጽ ለመረዳት ይቻላል፡፡ ‹ኧ ፊው ጉድ ሜን› የተሰኘውን ታዋቂ ፊልም ጨምሮ በርካታ ሌሎች ፊልሞችን ዳይሬክት በማድረጉ የምናውቀው ሮብ ሬይነር አሌ ኤ ታይምስ ለተሰኘው መጽሔት በሰጠው ቃለ ምልልስ ክርስቲያኖችን እንዲህ በማለት ያንቋሽሻል፤

“This kind of sanctimonious [***]… these right wing, moral majority, these people are [***] destroying the country ... አጉል ቅዱስ እንሁን እያሉ የሚመጻደቁ (...) እኒህ የቀኝ ክንፍ ወግ አጥባቂ (ክርስቲያኖችን ማለት ነው)፤ እኒህ ሰዎች ናቸው (…) ይህችን አገር እያወደሟት/እያጠፏት ያሉት" ... Rob Reiner Director of A Few Good Men. LA Times 12/6/92


ተዋናይና ዳይሬክተር የሆነው ዝነኛው ስቴቨን ሴጋል ለክርስትና ያለውን ንቀት ከመርዝ ጋር በማነጻጸር ይገልጸዋል፤ በኦሪትና ክርስትና ትውፊት ላይ የተመሰረተውን ባሕልና አኗኗር… ስቴቨን ሴጋል … "(አለውዴታችን) ወደተወለድንበትና እየተመገብነው ባደግነው በዚህ መርዝ በሆነው የአይሁድና የክርስትና ባሕል… … poisons that we as human beings are born with and are indoctrinated into through our Judeo-Christian culture." በማለት አንቋሾታል፡፡ 

እኒህ ማስረጃዎች ላላሳመኗቸውና አሁንም የሆሊውድ አቋም ግልጽ ላልሆነላቸው ተመልካቾች… ዋን ፈሊው ኦቨር ዘ ኩኩስ ኔስት የተሰኘውና… ጃክ ኒክልሰን መሪ ተዋናይ የሆነበትን ፊልም ዳይሬክት ያደረገው  የኬን ኪዚ ቀጣይ ንግግር የማያወላዳ ምላሽ ይሰጣል፡፡ የአርቲስቱ ዋነኛ ተግባር ይላል ኬን ኪዚ…

“The job of the artist is to say [***] you God. [***] you and the old Testament you rode in on! ... የአርቲስቱ ዋነኛ ተግባር አምላክን (መስደብና)  የተገለጥክበትን ብሉይ (እና አዲስ) ኪዳን (መርገም) ነው" ... Ken Keasey, the creator of Jack Neckelson’s ‘One flew over the Kuku’s Nest

የቀድሞ የሲ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ባለቤትና አስተዳዳሪ የነበረው ቴድ ተርነር ክርስትናን የውዳቂዎች ሐይማኖት በማለት አብጠልጥሎታል፡፡ ከዚህ አልፎም የሚከተለውን ስላቅና ስድብ የተሞላውን ንግግር በይፋ አድርጓል፤

"… እምነቴ መሠርሠር ጀመረ … አዎ አሁን አማኝ አይደለሁም … እውነቱን ንገረን ካላችሁ … ይበልጥ እየካድኩ በሄድኩ ቁጥር ይበልጥ ጥሩ ስሜት ይሰማኝ ዠመር .. (ኢየሱስ) ወደዚህ ወደታች ወርዶ ለኛ ሲል በመስቀል ላይ መከራ ሊቀበልና ሊሞት በቃ! … ለማመን ይከብደኛል! …" Ted Turner

ታይም ማሺን፣ ዋር ኦፍ ዘ ወርልድስ፣ እና ዘ ኢንቪዚብል ማን የተሰኙ ፊልሞችን በመድረሱ በፊልም አፍቃርያን ዘንድ ታዋቂነትን ያተረፈው ኤች ጂ ዌልስ የአምላክን ሕላዌ የሚገልጹ አስተምህሮዎችን ከምድረ ገጽ ማጥፋት የሕይወት ዘመኑ ዋነኛ አላማ አድርጎ ይንቀሳቀስ እንደነበረ ገልጾ ጽፏል፤ እንዲህ ይላል ኤች ጂ ዌልስ፤

“Never had I hated God so intensely… I have a sort of love for most living things, but cannot recall any time in my life when I had the faintest shadow of an intimation or love for any one of the persons of the Holy Trinity… But God, you are not much of a man. Leave me alone at any rate. Else I will canvass against you. I will make your position unbearable. I will jeer and make a mock of you. ... ለፈጣሪ ያለኝ ጥላቻ ገደብ የለውም… ለአብዛኛዎቹ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ከሞላ ጎደል ፍቅርና አዘኔታ እንዳለኝ አምናለሁ፤ ነገር ግን ከሶስቱ ስላሴ ለአንዳቸውም አንዳችም አይነት ፍቅር በሕይወት ዘመኔ የነበረበት አጋጣሚ ፈጽሞ አልነበረም… ፈጣሪ ሆይ… ወደ አጠገቤ እንዳትደርስ፤ አለበለዚያ በአንተ ላይ አመጻን አሴርብሐለሁ፤ … እሳለቅብሐለሁ" ... H. G. Wells creator of Time Machine, War of the Worlds & The Invisible Man. Desperately Mortal, 1980, p. 216



በአብዛኛው የማሕበረሰብ ክፍል ስለክርስትና መልካም ገጽታ እንደሚሰብኩ ተደርገው የሚቆጠሩ በርካታ ፊልሞች እንኳ ሳይቀር በውስጣቸው ቅኔያዊ ስድቦችና ስላቆችን የተሞሉ ናቸው፡፡




ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተቀበለውን መከራ የሚያሳየው ፓሽን ኦፍ ዘ ክራይስት በአገራችን ሳይቀር በበርካታ ሰንበት ት/ቤቶች ለመታየት የበቃ ሲሆን የፊልም ኢንዱስትሪው ለክርስቲያኖች ያበረከተው መልካም ስጦታ ተደርጎ በብዙዎች ይታያል፡፡ ነገር ግን የእርቃንና የግልጽ ዝሙት ላይ የሚተውኑ እንደሞኒካ ቤሉቺ (በፊልሙ ላይ ማርያም መቅደላዊትን ሆና የተወነችው ማለት ነው ፤ የጲላጦስን ሚስት ሆና እንደተወነችው ክላውዲያ ጌሪኒ ፤ እንዲሁም ዲያቢሎስን ሆና እንደተወነችው ሮሳሊንዳ ሴሌንታኖ) ያሉ በርካታ የፖርን ፊልም ተዋንያን በዚህ ስለቅድስና፣ ስለንጽሕናና ራስን ስለመካድ በሚሰብከው የክርስቶስ የመስቀል ላይ መከራን የሚያሳይ ፊልም ላይ እንዴት ሊተውኑ በቁ? በፊልሙ ላይ ክርስቶስ ለመግለጽ የሚከብድ ድብደባና ውርደት ሲቀበል የሚያሳየው ይሄ ፊልም ትንሳኤውንና መክበሩንስ ለምን ሳያሳይ ቀረ? የሚሉት ጥያቄዎች የሆሊዉድ የፕሮፖጋንዳ ኢንዱስትሪ ሕቡእ አላማ ምን እንደሆነ ያሳብቃሉ፡፡



የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅና የፊልም ሐያሲ የሆነው ማይክል ሜድቬድ ከሙያው ጋር በተያያዘ ብዙዎቻችን የማየት እድሉ የማያጋጥመንን የሆሊውድ ኢንዱስትሪ ከመድረክ በስተጀርባ ያለውን እውነተኛ ገጽታ ለማየት የበቃ ውስጥ አዋቂ ነው፡፡ ማይክል ሜድቬድ ታዲያ በበርካታ አጋጣሚዎች ከፊልም ኢንዱስትሪው ዝነኛ ተዋንያንና ዳይሬክተሮች ጋር ባደረጋቸው ግንኙነቶች ወቅት በአብዛኞቹ የኢንዱስትሪው ልሂቃን ላይ የሚስተዋለውን ለክርስትና ያላቸውን ገደብ የለሽ ጥላቻ ለመታዘብ በቅቷል፡፡

"በሆሊውድ ልሒቃን ዘንድ የሚስተዋለው በአማኞች ላይ ያነጣጠረ የፈጠጠና ዘግናኝ ጥላቻ ያስገርማል ፤ ሁሌም በሆሊውድ ፊልሞች ላይ ባሁኑ ዘመን ያሉ ሃይማኖተኞችን እንዲወክሉ የሚደረጉት ገጸ ባህሪያት ወይ እብዶች ፤ አልያም ሞኛሞኞች ፤ ጥቅም አሳዳጅ ሌቦች ፤ አንዳች ግድፈት ያለባቸውና ወራዶች ተደርገው ይቀረጻሉ…" Micheal Medved

ሚስተር ሜድቬድ አያይዞም በአብዛኞቹ የሆሊውድ ፊልሞች ላይ ክርስቲያን እምነት ያላቸው ገጸ ባሕርያትን ሁሌም ወይ እብዶች፣ አልያም ሞኛ ሞኞች፣ ወይም ጥቅም ፈላጊ (ሌቦች) ወይም አንዳች ግድፈት ያለባቸውና ወራዶች አድርገው ማቅረባቸውን ከዚህ ከጸነሱት ጥልቅ ጥላቻ ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ያሰምርበታል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የሚዲያ ተቋማት እንደቀድሞው ተመልካቾች ተመራምረው የሚደርሱባቸውን ስውርና ቅኔያዊ የሆኑ ጸረ ክርስትና ፕሮፓጋንዳዎችን በማሰራጨት ብቻ አልተወሰኑም፡፡ ሕብረተሰቡ ያለው ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ንቃቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወረደ ፣ የሚዲያ ውጤቶች ይዘት ምን ይሁን ምን ይበልጡን ግድ የለሽ እየሆነ በመሄዱ በሚዲያ ውጤቶች ላይ የሚስተዋሉት ርኩሰቶችና ስድቦች ይበልጥ እየጎሉና እየፈጠጡ ሄደዋል፡፡




የክርስቲያኖችን አስተምህሮና የአምልኮት መገለጫዎችን ለማንቋሸሽ ፣ ጭቃ ለመቀባትና ለማስነወር የመዝናኛ ኢንዱስትሪው ለሕጻናት የሚዘጋጁ ፊልሞችን እንኳ ከመጠቀም ወደኋላ አላሉም፡፡




የገና በአል አከባበርን የሚያሳየው (ከላይ የተመለከትነው) የሕጻናት ፊልም የጌታችን በበረት መወለድ የሚተርከው የታሪክ ክፍሉ ላይ አሳፋሪ በሆነ መልኩ በተወከሉት ገጸ ባሕርያት አማካኝነት ሲሳለቁ ይታያል፤ ሕጻኑ ክርስቶስን ለማምለክ ከመጡት ሶስቱ የጥበብ ሰዎች መካከል አንዱ ስራውን ረስቶ በእጣን ፋንታ ኩኪዝ ይዞ ሲቀርብ፣ እጣን ማምጣት እንደሚገባው ሲነገረው ኩኪሱን ሲበላው፣ በመሀል ሕጻኑ ክርስቶስ ከተኛበት ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ፣ ሲያጡት ፕሮግራሙ እንዳይቋረጥ ሌላ ሕጻን በምትኩ ተክተው ሲቀጥሉ፣ በሆነው ባልሆነው ፕሮግራሙ ሲበላሽና ሁሉም የሚጠበቅበትን  ዘንግቶ ሲደናበር ይታያል፡፡

የክርስትና አስተምህሮዎችን፣ ቀኖናዎችን፣ ባህላዊና ትውፊታዊ እሴቶችን እንዲሁም ግብረገባዊ መርሆዎችን የሚተቹና የሚያንቋሽሹ ሌሎች ተጨማሪ የሚዲያ ውጤቶችን እስኪ ለአፍታ እንመልከት፤



ክርስቲያኖችን ደም የጠማቸውና ስለስልጣኔ አንዳችም ግንዛቤ የሌላቸው ቡትቶ ለባሽ ደንቆሮዎች አድረጎ የሚስለው አጎራ የክርስቲያን ምእመናን እንደወሮበሎች ቤተ መጻሕፍትን ሲያፈርሱ፣ መጻሕፍትን ሲያቃጥሉ፣ ፈላስፎችና ተመራማሪዎችን በሐይማኖት ስም ሲጨፈጭፉ ያሳያል፡፡ ክርስቲያኖቹ አይሁዳውያኑን ሲጨፈጭፉ የሚያሳየው የፊልሙ ትእይንት ሆን ተብሎ በአውሽዊትዝ የአይሁድ እስረኞች ጣብያ (Aushwitz) ላይ የጀርመን ናዚዎች የፈጸሙትን ጭፍጨፋ ከሚያሳዩ ፊልሞች ጋር እንዲመሳሰል ተደርጎ መሰራቱ ሕብረተሰቡ ናዚዎችን በሚያይበት አተያይ ክርስቲያኖችን እንዲያይ የታቀደ ስነልቦናዊ ታክቲክ መሆኑን አንዳንድ ምሁራን ጠቁመዋል፡፡




ዘ ዳቪንቺ ኮድ (The Davinci Code): - ብዙዎቻችሁ ተመልክታችሁት ይሆናል … ያም ሆኖ ጥቂት ማብራሪያ የሚያስፈልገው ነው … የፊልሙ ዋና ሀሳብ … ክርስቶስ በመስቀል ላይ አልሞተም … ከመግደላዊቷ ማርያምም ጋር ጋብቻ መስርቶ ወደ ፈረንሳይ ሄዶ ይኖር ነበር … ልጆችም ነበሩት … የዘር ሀረጉም እስካሁን በዚያ ይገኛል … የሚል በሬ ወለደ አይነት ነጭ ውሸት ነው … (ክርስቲያኖች ሆይ … እንዲህ አምላክ ሲሰደብና የአምላክ ስም ጭቃ ሲቀባ ከማየት የሚበልጥ ምን በሀዘን የሚያደማ ነገር ይኖር ይሆን?)


ጁዳስ የተሰኘው የሌዲ ጋጋ የዘፈን ቪዲዮ:- በዚህ የሙዚቃ ቪዲዮ ላይ ክርስቶስና ደቀ መዛሙርቱ ሐዋርያት ሞተር ሳይክል እንደሚነዱ ጋንግስታሮች ተደርገው ቀርበዋል … ሌዲ ጋጋም ሴተኛ አዳሪ ሊያስመስላት በሚችል መልኩ ተቀርጻ ክርስቶስን እንዲወክል ካስቀመጡት ወሮበላ ጀርባ ተቀምጣ ትታያለች … (ይህም ሆሊውድ እያቀነቀነው የሚገኘው … ክርስቶስና ማርያም መግደላዊት ጾታዊ ግንኙነት ነበራቸው የሚለው ስድብ አካል ነው) … በክርስቶስ ላይ ማሾፍና መሳደባቸውን ሲቀጥሉም … ሌዲ ጋጋ ክርስቶስን ወክሎ የቀረበውን የእሾህ አክሊል መሰል ጉንጉን አናቱ ላይ ያስቀመጠ ተዋናይ ትታ ከሀዲውን የአስቆሮቱ ይሁዳ ወደ ወከለው ጋንግ/ተዋናይ ስትሄድና ለርሱም ውዳሴን ስታቀርብ ያሳያሉ … የሙዚቃ ቪዲዮው ርዕስም ‘Judas’ የመሆኑ ምክንያት ይኼው ነው::

ጁዳስ - ትሬይተር ኦር ፍሬንድ ፡- ይሁዳ ከሃዲ ወይስ የልብ ወዳጅ በሚል ርእስ የቀረበው የሂስትሪ ቻነል ታሪካዊ ዶክመንተሪ ይሁዳ የክርስቶስ የልብ ወዳጅ እንጂ ከሀዲ እንዳልሆነ፣ ከሀዋርያት ሁሉ በተለየ የክርስቶስ አስተምህሮ እሱ ብቻ እንደገባውና፣ ጌታውን አሳልፎ የሰጠው የክርስቶስን ፈቃድ ለመፈጸም እንደሆነ፣ እናም ሊሞገስ እንጂ ሊወነጀልና ሊረገም እንደማይገባው… የሚገልጹና ይህን የመሰሉ እጅግ አስጸያፊ መከራከሪያዎችን በማቅረብ ተመልካችን ለማሳምን ይጥራል - ጥናታዊ ዘገባው፡፡

ዘ ኢንቬንሽን ኦፍ ላዪንግ፣ ብሩስ ኦልማይቲ፣ ኢቫን ኦልማይቲ፣ ኤጅ ዋን፣ ጁዳስ፣ ኪንግደም ኦፍ ሄቨን፣ ሊጅን የክርስትናን አስተምህሮ ከሚያንቋሽሹ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችና በቅዱሳን አባቶች ላይ ከሚያላግጡ ፊልሞችና የሙዚቃ ቪዲዮዎች መካከል እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ 


ለመሆኑ መቼ ይሆን ዘወትር የሚያደነቁሩን ፊልሞችና ዘፈኖች ክርስትና ላይ የተነጣጠሩ ጽርፈቶችና ማንቋሸሾች እንደሆኑ ተረድተን የክህደቱ ተባባሪ ከመሆን ራሳችንንና ወገናችንን የምንጠብቀው?

ይቆየን






ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።

Saturday, March 1, 2014

ቴክኖሎጂ ያዘመነው የእኛ ትውልድና ፤ ሚዲያ መራሹ ማሕበራዊ ምስቅልቅል Part 1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡


ቴክኖሎጂ ያዘመነው የእኛ ትውልድና ፤ ሚዲያ መራሹ ማሕበራዊ ምስቅልቅል



Nowadays it is considered a self-evident and undoubted fact that we are living at a unique time in history where mankind is enjoying supreme technological progress and man-made heaven on earth is soon to be within our reach.

But many people deviate from this popular perception. They claim that we are in the middle of social and cultural turmoil which will inevitably bring civilization into utter destruction and total collapse.
These informed critics point towards:

F Increasing display of nerve wrecking violence and despicable sexual imagery on medias and its subsequent impact in producing a generation preoccupied with sexual lust and rebelliousness;
F The rejection of traditional religious and moral values and the increasing acceptance of abominable vices such as homosexuality, pedophilia, trans-sexuality, and sado-masochism;
F The spread of Satanism, witchcraft and an obsession with what is evil and unrighteous; and
F The subsequent growth of audio-visual products that blaspheme God and make a mockery of Christianity thereby making obscenity and blasphemy a cultural and behavioral norm…

as evidence that illuminates the severity of the problem.
The social and historical critics go further and claim that the current chaos and social upheaval is not spontaneous but the result of meticulous planning and malicious conspiracy.

Could secret societies behind the scenes have possibly orchestrated the most outrageous deception that fooled most of us into becoming willing participants of our own destruction?

Stay with us as we examine in detail
F all the available information,
F explore the evidence,
F analyze official documents
F and inspect credible sources.
 You be the judge as we ask you to maintain an unbiased attitude until you have all the available evidence.



ከ20ኛው መ.ክ.ዘ መገባደጃ አንስቶ ባሉት ጥቂት አስርት አመታት የአለምን ምስል ፈጽመው የለወጡ ሁለት አስደናቂና ቅጽበታዊ የሆኑ ለውጦች በተመሳሳይ ጊዜ ተከስተዋል ፤ አንደኛው ለውጥ ለማመን በሚያዳግት ሁኔታ የሰው ልጅ ያስመዘገበው የቴክኖሎጂ ምጥቀት ሲሆን ፤ ሌላኛው ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ በስነ ምግባር፣ በሃይማኖትና በሰብአዊ እሴቶች ዙሪያ እየተስተዋለ የመጣው ሁለንተናዊ ዝቅጠት ነው፡፡ እነዚህ ሁለት እርስበርስ ተመጋጋቢ ነገር ግን ፍጹም ተጻራሪ የሆኑ ክስተቶች ያለንበት ትውልድ መገለጫዎች ለመሆን በቅተዋልም ማለት ይቻላል፡፡

ተንጠልጣይ ድልድዮች፣ ከድምጽ የፈጠኑ አውሮፕላኖች፣ ተንሳፋፊና ሰማይ ጠቀስ ሕንጻዎች፣ የጠፈር መንኮራኩሮች፣ የሕዋ ሳታላይቶች፣ ሰው አልባና ከራዳር እይታ የተሰወሩ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ እጅግ የረቀቁ የሕክምና የቴክኖሎጂ ውጤቶች … በርግጥም ከአእምሮ በላይ የሆኑ አስደማሚ ግኝቶች ናቸው፡፡

የሰው ልጅ ለደረሰበት የጥበብ ከፍታ ቋሚ ምስክሮች የሆኑት እነዚህ የቴክኖሎጅ መራቀቆች ታዲያ በርካቶችን በሰው ልጅ ጥበብ ወደ መመካት ሲያደርሷቸው ፤ አንዳንዶችንም ጥልቅ ወደ ሆነ የአግራሞትና የመደመም ስሜት ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም የሰው ልጅ  ቁሳዊ ፍላጎቶቹን እንዳያሟላ ለዘመናት የተፈጥሯዊ ተግዳሮቶች ምርኮኛ ሆኖ መኖሩን በማስታወስ ባለንበት ክፍለ ዘመን አእምሮውን ተጠቅሞ ባስገኛቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመታገዝ ከእነዚህ ማነቆዎች ራሱን ነጻ አውጥቶ የምቾት ኑሮ ለማጣጣም መብቃቱን የሚያወሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ እንደነዚህ ወገኖች እምነት የሰው ልጅ በትክክለኛው የእድገትና የብልጽግና ጎዳና ላይ ለመገኘቱ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ አያስፈልግም፡፡ ይህንን በነሱ አተያይ የማያሻማ፣ አገር ያወቀውና ፀሐይ የሞቀው የፈጠጠ ሐቅ ተአማኒነት መጠርጠርም ከጤናማና ከተማረ ሰው እንደማይጠበቅ በልበ ሙሉነት ያሰምሩበታል፡፡

ያም ሆኖ ከእነዚህ ወገኖች አመለካከት በተቃራኒ የቆሙና ቁሳዊ ፍላጎቶችን ከማሳካት አንጻር ‹ዘመናዊው› አለም በቴክኖሎጂ በኩል ያስመዘገባቸው ስኬቶች ተደርሶበታል ለሚባለው ከፍተኛ ስልጣኔና ብልጽግና መገለጫ ነው ብለው ለመቀበል የሚያንገራግሩ አካላት ቁጥርም ጥቂት የሚባል አይደለም፡፡ እኒህ ወገኖች ትውልዱ ቁሳዊ ፍላጎቶቹን ከማሟላት አንጻር እጅግ ርቆ መጓዙን ባይክዱም ቁሳዊ መሻሻል የእድገትና የስልጣኔ መስፈርት ነው የሚለው አስተሳሰብ ግን አይዋጥላቸውም፡፡

ይህ ከተለመደው ወጣ ያለ እይታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋና እየዳበረ የሌሎች መስኮችንም በር በማንኳኳት ላይ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ያህል አፍሮ ሴንትሪክ ቲዮሪ በመባል የሚታወቀውን ፍልስፍና የሚያራምዱ ምሁራን የስነ ሕንጻ ጥበብን የሚመሰክሩ የአርኪዮሎጂ ግኝቶች በአመዛኙ የሌሏት አህጉራችን አፍሪካን በስልጣኔ ኋላ ቀር አድርጎ የሚፈርጃትን ቁሳዊ ብልጽግና ላይ ብቻ ያነጣጠረ ምእራባዊ መነጽር አውልቆ መጣል እንደሚያሻ ይገልጻሉ፡፡ እኒህ አፍሪካውያንና አፍሪካ አሜሪካውያን ምሁራን በትውፊት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር የበለጸገ ስነ ቃል፣ ባሕላዊ፣ ማሕበራዊና ግብረ ገባዊ እሴቶች ያሏቸው ማሕበረሰቦች የነበሯት አፍሪካ ባልካበቻቸው ግንቦችና ባልጠረበቻቸው ሐውልቶች፣ ባልገነባቻቸው ሕንጻዎች ልትሸማቀቅ፣ ራሷን እንደኋላቀር ቆጥራ በድንጋይ ላይ ድንጋይ ላነባበረችው አውሮፓ ልትሰግድ እንደማይገባ፤ ባንጻሩ በመጠቀው ማሕበራዊ እሴቷ ልትኮራና አፍሪካዊ የስልጣኔ እይታ ልታዳብር እንደሚገባ ይሞግታሉ፡፡ እዚህ ላይ ታዲያ ስለ አፍሮ ሴንትሪክ ቲዮሪም ሆነ ጽንሰ ሐሳቡን ስለሚያራምዱ ምሁራን መጥቀሳችን አስተሳሰቡን ደግፈን ለማስተጋባት ሳይሆን የአንድን ሕብረተሰብ መበልጸግ/መሰልጠን/ ለመገምገም የሚቀመጡት ቁሳዊ ስኬትን መሰረት ያደረጉት መስፈርቶች አንደምናስበው በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው እንዳልሆኑና ይልቁን የአንድ ጎራ እይታዎች ብቻ መሆናቸውን ለማስመር ነው፡፡

እነዚህ የዚህ ‹ዘመናዊ› ስርአት ሐያስያን የሆኑት ምሁራን ታዲያ የብልጽግና መገለጫ አድርገን እየተመለከትነው የመጣነውን ቁሳዊነትን በመንቀፍ ብቻ አይወሰኑም፡፡ ከዚህ አልፈው ከፊታችን ቴክኖሎጂ አንጥፎልናል በምንለው ወርቃማ የስኬት ጎዳና ላይ የጥፋት ጭለማና የውድቀት ጭጋግ እንዳጠላ ጭምር በጽኑ ያምናሉ፡፡ ነገር ግን በራችንን በማንኳኳት ላይ ነው ስለሚሉት አይቀሬ ጥፋትና ማሕበራዊ መንኮታኮት (Social Cataclysm) የሚያሰሙት ይህ ስጋት ታላላቅ ከተሞችን ባጨናነቁ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ተከልሎ፣ እንደንፋስ በሚከንፉት መኪኖችና ባቡሮች ጩኸት ውስጥ ሰጥሞ፣ በሚዲያዎች አለማቋረጥ በሚስተጋቡ ዘመናዊ ሙዚቃዎችና የመዝናኛ ዝግጅቶች ተውጦ ሰሚ ጆሮ አጥቷል፡፡

በዘመኑ ትውልድ በተለይም በወጣቱ ማሕበረሰብ ላይ የሚስተዋለው ስርአት አልበኝነት፣ ግለኝነት፣ አመጻና ጠብ፣ ከፍተኛ የሱስ ተጠቂነት፣ የግብረሰዶም መስፋፋት፣ ለማሕበረሰባዊና ግለሰባዊ የስነ ምግባር እሴቶች ደንታ  የሌለው… ለገንዘብ ሕሊናውን የሸጠና… ለቀኑ ብቻ የሚኖር ሰው ቁጥር መበራከት፣ የውርጃ የፍቺ እንዲሁም የሴትና የወንድ አዳሪነት ቁጥር ማሻቀብ… ወዘተ እኒህ ወገኖች ላለንበት ዝቅጠት እንደ ማስረጃ የሚያቀርቡዋቸው ጠቋሚ መለኪያዎች ናቸው፡፡ ሰዎች በአንዱ ጎን ቁሳዊ ፍላጎቶቻቸውን ሊያሟሉ በሚችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ቢከበቡም ፤ ነገር ግን በሌላው ጎን ሕሊናቸውን አጥተው እንስሳዊ ኑሮን ከተላመዱ እየተጓዙበት ያለውን መንገድ በርግጥ የስልጣኔ፣ የብልጽግናና የስኬት ነው ልንለው እንዴት እንችላለን? … ይጠይቃሉ የ‹ዓለም-ዘምናለች› አስተሳሰብ ተቃዋሚ የሆኑት እነዚህ ምሁራን፡፡

እነዚህ ከሚነጉደው ጋር አብረው ከመንጎድ ይልቅ እየገሰገስንበት ያለውን ጎዳና ቆም ብለው ለማጤን የሚደፍሩ ወገኖች ታድያ የአሁኑን ዘመን ትውልድ በታሪክ አድማስ-ማዶ ተሰናብተነው ከመጣነውና በአመዛኙ ‹ኋላቀር› የሚል ታርጋ ከለጠፍንበት ካለፈው ትውልድ ጋር በማነጻጸር እየተመለከትነው ያለነው ለውጥ የእድገት ይሁን የዝቅጠት እንድንመረምር ይጋብዙናል፡፡ አገርን፣ ባንዲራን፣ እምነትንና… መሰል የማሕበራዊ እሴቶችን ሕልውና ለማስጠበቅ ሕይወቱን ሳይቀር ለመክፈል የማያቅማማ ትውልድ፤ ቢር ለእውነት ዘብ በመቆም ቢት ደግሞ እምነትን ሳያስደፍሩ የጀግና ሞት ለመሞት ይናፈቅ የነበረበት ዘመን ፤ ከግል ምቾቱ ይልቅ ለሀገራዊና ሃይማኖታዊ ራእዮች ይተጋ የነበረ ማሕበረሰብ…  አልፎ …  ስስትና ራስ ወዳድነት ያሳወረው… ከቁሳዊ ፍላጎቱ አርቆና አሻግሮ ማየት የተሳነው… የሚሞትለት ቀርቶ የሚኖርለት ዘላቂ አላማ የሌለው… ነገር ግን በድንቃድንቅ የቴክኖሎጂ ግኝቶች የተከበበ ትውልድ የተተካበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡

ይህ ገለጻ በእርግጥ ያለንበትን ትውልድ ሁኔታ በትክክል ያሳያልን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚሉት የጨለምተኝነት አመለካከት ውጤት ይሆን?

በመቀጠል አይኖቻችን እንዲገለጡ… የተዘፈቅንበትን አዘቅት ጥልቀት በቅጡ እንድንረዳ… እንዴት እንዲህ ወዳለ ክፉ ማጥ ውስጥ ልንገባ እንደበቃን እንድንገነዘብና… አልፎም ‹ምን ይበጃል›ን አስከትለን መፍትሔ ለማግኘት እንድንንቀሳቀስ በፈርጅ  በፈርጁ የገባንበትን ማሕበራዊ ምስቅልቅል በመረጃ አስደግፈን እንቃኛለን… ማስተዋሉን ያድለን ይከታተሉን፡፡




በአገራችን ኢትዮጵያ ትምህርት የቀመሱና ኑሯቸውን በከተሞች ያደረጉ ወላጆች ልጆቻቸው የምእራቡን አለም ፊልሞችና ዘፈኖችን እንዲመለከቱ ሲፈቅዱ ማየት የተለመደ ነው… ድርጊቱን የስልጡንነት መገለጫ አድርገው የሚቆጥሩም አይታጡም፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ወላጆች ይህን የሚያደርጉት ልጆቻቸው አለም አቀፋዊ ቋንቋ የሆነውን እንግሊዝኛን አቀላጥፈው ሲናገሩ ለማየት ካላቸው ጉጉት የመነጨ ነው፡፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችና መንፈሳውያን ከሆኑ ወላጆች መካከል እንኳ ሳይቀር ልጆቻቸው በቲቪ ሲተላለፍ ልክ እንዳዩት አስመስለው የእንግሊዝኛ ሙዚቃን ለማቀንቀን ሲኮላተፉ በሚመለከቱበት ወቅት በፈገግታ ማለፍ የሚቀናቸው አሉ፡፡ መጥፎ አርአያ ከሆኑ እኩዮቻቸው ተጽእኖ ለማራቅ በማሰብ ልጆቻቸውን ከቤት እንዳይወጡ የሚከላከሉ… በቀን ለ24 ሰአታት ያለማቋረጥ የሆሊዉድ ፊልሞችን የሚያስተላልፍ ዲሽ ለመትከል ግን ለአፍታ እንኳ የማያቅማሙ ወላጆችም ጥቂቶች አይደሉም፡፡ በነሱ እይታ በቴሌቪዥኖች የሚተላለፉት የመዝናኛ ስርጭቶች እዚህ ግባ የሚባል ጉዳት አያስከትሉም፡፡

በርካታ መካከለኛ ገቢ ያላቸው ወላጆች ገቢያቸውን ለማሳደግ ከስራ ሰአት በተጨማሪ ከልጆቻቸው ጋር ሊያሳልፉት በሚገባቸው ጊዜ ሳይቀር ሲባክኑና ደፋ ቀና ሲሉ የሚውሉ ናቸው፡፡ በመሆኑም በስራ መደራረብና በጊዜ ማጣት የተወጠሩት ወላጆች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቴሌቪዥንን ፋታ የምትሰጣቸው ሞግዚት አድርገው ከመቀበልም አልፈው የወላጅ ብቸኛ መብትና ሐላፊነት የሆነውን ልጆችን የማስተማርና የመገሰጽ ተግባርን ሳይቀር ለፊልሞችና ለዘፈኖች አሳልፈው ሲያስረክቡ ይታያል፡፡ የሚዲያዎችን በተለይም በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ምእራባዊ ቃናን የተላበሱ ፕሮግራሞችን ጎጂነት በመጠኑም ቢሆን የተገነዘቡ ወላጆች እንኳ ቴሌቪዥን የልጆቻቸውን ቀልብ ገዝቶ በመያዝ እነርሱን ፋታ እንዲያገኙ ስለሚያግዛቸው እልፍ ሲሉ የሚያዩዋቸውን መልካም ያልሆኑ ድርጊቶች እንኳ አይተው እንዳላዩ ቸል ለማለት አያቅማሙም፡፡

ነገር ግን የሕልውናችን ፈርጦች የሆኑ ልጆቻችንን አስረክበናት እየሄድን ያለነውና የሳሎኖቻችን ሞገስ ያደረግናት አዲሷ ሞግዚት በርግጥ የምትታመንና ለአደራ የምትበቃ ናትን? ብዙዎቻችን እንደምናምነውስ የቴሌቪዥን አሉታዊ ተጽእኖ ዘላቂ ጉዳት የማያደርስ ቀላል ጉዳይ ነውን? ከዚህ በታች በመረጃ አስደግፈን እንደምንመለከተው መልሱ ከምንገምተው ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡

በሊችተር፣ ሊችተርና ሮትማን የተከናወነና ለ4 አስርት አመታት በዘለቀው የቴሌቪዥን ተጽእኖ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የጥናት ሪፖርት እንደሚያመለክተው በአማካይ በሰአት እስከ 50 ወንጀሎችና ከደርዘን በላይ የሚደርሱ የነፍስ ግድያዎች በምእራባውያን ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ይታያሉ፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት አንድ ሰው የ17 አመት እድሜ ላይ ሲደርስ ከ800 ሺ እስከ 1.5 ሚሊዮን የሚደርሱ የጭካኔ ድርጊቶችና ከሩብ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ነፍስ ግድያዎችን ይመለከታል ማለት ነው፡፡

ከ1955 ዓ.ም አንስቶ ባሉት አመታት የፊልም ገጸ ባሕርያት በገሀዱ አለም ከሚሆነው አንድ ሺ እጥፍ በላቀ ሁኔታ በቴሌቪዥን ስክሪኖች ሲገደሉ ይታያሉ፡፡ በፊልሞች የሚታየው ግድያ በገሀዱ አለም ቢፈጸም የሀገራችን ሕዝብ በስምንት ቀናት ውስጥ ያልቅ እንደነበር ማስተዋል ጉዳዩ ምን ያህል አንገብጋቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ያሳያል፡፡

ላለፉት 7 አስርት አመታት ያለማቋረጥ በአሜሪካ ሕዝብ ላይ የወረደው የፊልሞች፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና የዘፈን አልበሞች ጎርፍ ለማያባራ የዝሙት ፣ የጭካኔ ድርጊትና ጥንቆላ ሱስ ዳርጓቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም በ21ኛው መ.ከ.ዘ. መባቻ አገሪቱና (ወደምትገሰግስበት ገደል በጭፍን የሚከተላት የተቀረው ዓለም) ለማመን በሚያዳግት ሁኔታ አቻ ወደሌለው የጥፋትና የጭካኔ ማጥ ውስጥ ለመዘፈቅ በቅተዋል፡፡

ታዋቂው ጋዜጠኛ ስቲቭ አለን ለስኬትና ዝና ባበቁት የሚዲያ ተቋማት ላይ ጣቱን በመቀሰር በሚያስተላልፏቸው ፕሮግራሞች ላይ የተቃውሞ ድምጹን ያሰማል፤ ‹‹ቴሌቪዥን ሕጻናትን ወደ ሞራል ዝቅጠት እየመራ ነው›› ይላል ሚስተር አለን፡፡ የሚዲያ ከበርቴው ቴድ ተርነርም በተመሳሳይ ፊልሞች የጭካኔ ተግባራትን  እንደሚቀሰቅሱ አይክድም፡፡

‹‹ጆሮ ሰጥተን ያደመጥነው (በጄ በለን የተከታተልነው) ነገር ሁሉ ተጽእኖ እንደሚያሳድርብን የታወቀ ነው… እኒህ (በአመጻ/ጭካኔ ድርጊቶች የተሞሉ) ፊልሞችና የቲቪ ፕሮግራሞችም ተጽእኖ ያሳድሩብናል፡፡ ቤተሰብህ ጽኑ መሰረት የሌለው ከሆነ ደግሞ (የሚዲያ ውጤቶች) የሚያሳድሩብህ ተጽእኖ በዚያው ልክ ይጨምራል… በከተሞቻችን የሚኖሩ ቤተሰቦች ከአቅማቸው በላይ የሆኑ ከባባድ ችግሮች ተጋርጦባቸዋል - በሕይወት ዘመናቸው የቤተሰብ ፍቅር ያላገኙና ብስጭትና በብሶት የተሞሉ  ሰዎች በጭካኔ ድርጊቶች የተሞሉትን ፕሮግራሞች እንዲመለከቱት ካደረክ ውጤቱ እሳት ላይ ነዳጅ የመጨመር ያህል ይሆናል፡፡››
ኤል ኤ ታይምስ 4/3/94 ካሌንደር ኮሌክሽን

ከመጠን በላይ በጭካኔ ድርጊቶች፣ አሳፋሪ የዝሙት ተግባራት እና ጸያፍ ስድቦች የተሞሉ የቲቪ ፕሮግራሞችን በመመልከት ሱስ በርካቶች መለከፋቸው በራሱ አሳሳቢ ቢሆንም ችግሩ ግን በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ከጥፋት ልኡካኑ ወገን የሆነው ቴድ ተርነር በግልጽ እንዳመነው በጭካኔና ጎጂ ተግባራት የተሞሉት የመዝናኛ ፕሮግራሞች በተመልካቾቻቸው ላይ ተጨባጭ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እያመጡ ሲሆን እያስከተሉት ያለው ጉዳትም በበርካታ የማሕበራዊ ሕይወት ገጽታዎች ላይ በግልጽ እየታየ ይገኛል፡፡

የሬዲዮ ፕሮግራሞች አዘጋጅና የፊልም ሐያሲ የሆነው ማይክል ሜድቬድ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በገሀዱ አለም ላይ እየተበራከቱ ለመጡት የጭካኔና የአመጻ ድርጊቶች ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እንዲህ ያጋልጣል፡፡

‹‹በ1982 የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ የጤና ዘረፍ ጠቅላይ ጽ/ቤት ባወጣው 5 ዶሴ ሙሉ መረጃ የያዘ ሪፖርት ለተራዘመ ጊዜ የጭካኔ ድርጊት የተሞሉ የቴሌቪዥን ዝግጅቶችን መመልከት ለአመጻና ጭካኔ ተግባራት እንደሚገፋፋ በማያወላዳና በሳይንሳዊ መረጃ በተደገፈ ሁኔታ ደምድሟል፡፡ የኤቢሲ ቴሌቪዥን ግን ለዚህ ሪፖርት ባወጣው ኢፋዊ ምላሽ ‹የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በገሀዱ አለም በሰዎች ጠባይ ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ የሚያስረግጥ አንዳችም ሳይንሳዊ ማስረጃ አላገኘንም› ብሏል፡፡ የኤቢሲ ቴሌቪዥን በርግጥ ይህን የሚያምን ከሆነ ምርቶቻቸውን ለሚያስተዋውቁ ድርጅቶች ካሳ ሊከፍል ይገባዋል፤ ምክንያቱም የቴሌቪዥን ስርጭቶች በሰዎች ጠባይ ላይ አንዳችም ተጽእኖ የማያሳድሩ ከሆነ ታዲያ ምርት ማስተዋወቂያ የአየር ሰአት ለምን ይሸጣሉ?››
ማይክል ሜድቬድ፣ የፊልም ሐያሲና የሬድዮ ፕሮግራሞች አዘጋጅ

ናሽናል ኢንስቲትዩት ኦፍ ሜንታል ሔልዝ የተሰኘ ተቋም በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች የሚተላለፉ በጭካኔ ድርጊት የተሞሉ ፊልሞችና በገሀዱ አለም የሚታዩ የአመጻ ተግባራት ተመጋጋቢ መሆናቸውን ባካሄዳቸው ከአንድ ሺ የሚበልጡ ጥናቶች አረጋግጧል፡፡ የነሱ ማስጠንቀቂያ ግን በአሜሪካ ብቻ 50 000 የሚደርሱ ቴሌቪዥኖች በየቀኑ ከመሸጥ አላገዳቸውም፡፡

ይህን ተከትሎም የፊልሞች ሰለባ የሆኑ በርካታ ወጣቶች አቅላቸውን እየሳቱና እንስሳዊ ባሕርይን እየተላበሱ ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ አጥኚዎች የኮምፒውተር ቀመር ተጠቅመው በነደፉት መላምታዊ ሞዴል ላይ በመመስረት በቀጣይ ጥቂት አመታት ከፍተኛ የሆነ የወንጀል ማእበል እንደሚመጣ ሙያዊ ትንታኔያቸውን ይሰጣሉ፤ የጥናት ውጤታቸውን ይበልጥ አሳሳቢ የሚያደርገው ከወንጀል ፈጻሚዎቹ አብዛሃኛዎቹ ወንበዴዎችና ስርአት አልበኞች ሳይሆኑ ቀጪ ያጡና ፊልም ላይ ያዩትን ትወና በገሀዱ አለም ከመድገም ወደኋላ የማይሉ ለጋ ታዳጊዎች መሆናቸው ነው፡፡

መቀመጫውን በኖርዝ ዌስት ዩኒቨርስቲ ያደረገው የወንጀል ምርመራ ሳይንስ ዲፓርትመንት ባለሙያ የሆነው ጄምስ ፎክስ ታዳጊዎች ከአዋቂ ሰዎች በበለጠ አደገኞችና የወንጀል ድርጊቶች ለመፈጸም የተጋለጡ መሆናቸውን ከነምክንያቱ እንዲህ ያስቀምጣል፡-

‹‹… በዘመናችን ሰው መግደል በቀደሙት ዘመናት እንደነበረው ነውርና የማይታሰብ አይደለም፡፡ ይህ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ የቴሌቪዥን ተጽእኖ ነው፡፡ አሁን ሕጻናትና (ታዳጊዎች) ሞትና ነፍስ ግድያን መመልከት ተላምደውታል፡፡ ፊልሞችን ተከራይተው ሲያበቁ የሚወዷቸውን የፊልም ክፍሎች (በተለይ በጭካኔ የተሞሉትን) ይመርጡና ደግመው ደጋግመው ይመለከቱታል፡፡ ስለ ጾታዊ ግንኙነት አንዳችም ግንዛቤ ያልነበረው አንድ ታዳጊ ለመጀመሪያ ጊዜ እንስሳዊ በሆነ ሁኔታ ሴቶች በጉልበት ሲደፈሩ ፊልም ላይ ሲመለከት ሰቅጣጩ ትእይንት ምን አይነት ተጽእኖ ሊያስከትልበት እንደሚችል መገመት ትችላለህ? በጣም አስከፊ ምስል ነው… ሕጻናት ደግሞ እጅጉን ለተጽእኖ የተጋለጡ ናቸው፡፡››
ሚዲያ ዋይዝ፣ ቴድ ባኤህር፣ ገጽ 107

ይህን ሁሉ ግምት ውስጥ ስናስገባ… ከ22 እስከ 34 በመቶ የሚሆኑ ጭካኔ የተመላባቸውን ወንጀሎች በመፈጸማቸው ወሕኒ የወረዱ ወጣት ታራሚዎች ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ ያዩዋቸውን የወንጀል አፈጻጸም ዘዴዎች ሆን ብለው መኮረጃቸውን እንዳመኑ የኤቢሲ ቴሌቪዥን በቅርቡ መዘገቡ እምብዛም አይደንቀንም፡፡

ይቆየን

        


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር።